ታሪኮች ስለ የንግግር ነፃነት

የሱዳን የዴሞክራሲ ፀደይ ማለቂያ ወደሌለው አስቀያሚ የበጋ ንዳድ እየተቀየረ ነው

The Bridge  16 ሰኔ 2019

"ትልቁ ፍራቻ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ በዝምታ እየተመለከተው ሳለ፣ ዳርፉር የተከሰተው ዓይነት ደም አፋሳሽ ወታደራዊ እርምጃ እንዳይወሰድ ነው። የዳርፉርን ጭፍጨፋ የፈፀሙ ሰዎች አሁንም ኀላፊነት ይዘዋል፤ እኛ ደግሞ ከአሁኑ ፊታችንን ከሱዳን አዙረናል።"

የኦሮሞ ሙዚቀኞችን የማፈን አሳፋሪ ገመና

  8 ጥር 2016

የመንግሥት ሳንሱርን ለመስበር አማራጭ ይዞ የመጣውን ኢንተርኔት በመጠቀም፣ በዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ዩቱዩብ እና ፌስቡክ ላይ በተደረገ ቆጠራ ብቻ ከ300 በላይ ፖለቲካ ነክ ዘፈኖች ከ2006 ወዲህ የተለቀቁ መሆኑ የፖለቲካ ዘፈኖች መነሳሳት አለ ብሎ ለማለት ያስችላል፡፡

ለዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ለሀምሌ 24 በተዘጋጀው ትዊተር ማራቶን ላይ በመካፈል አጋርነቶዎን በተግባር ያሳዩ::

  30 ሐምሌ 2014

በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::

ቋንቋዎች ነጻ ናቸው? የዓለም አቀፉን የአፍመፍቻ ቋንቋ የሚመለከቱ ሐሳቦች

  19 የካቲት 2014

ዛሬ የዓለምአቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን ነው፡፡ ቀኑ በUNESCO አባል አገራት የቋንቋ እና ባሕል ልዩነቶችን እና ብዝኃቋንቋዊነትን ለማበረታታት ይከበራል፡፡ ዕለቱ በተለይም በባንግላዴሽ እ.ኤ.አ. ከ1952 ጀምሮ ‹ኤኩሼ የካቲት› በመባል የሚታወቀው የቋንቋዎች ንቅናቄ ቀንን ዕውቅና ለመስጠት ነው፡፡ ዕለቱ የካቲት 14 (ፌብሩዋሪ 21) ተደርጎ የተመረጠው በባንግላዴሽ (የዛኔዋ ምስራቅ ፓኪስታን) በዕለቱ እ.ኤ.አ. በ1952 በዳካ...

የ‘ወንድም ጋሼ’ አፍሪካዋ ቤቲ ላይ የባሕል እሴት ጥያቄ ተቀሰቀሰባት

  9 ሰኔ 2013

የ‘ወንድም ጋሼ’ አፍሪካ (Big Brother Africa) የተሰኘው የእውነተኛ የኤቴሌቪዥን ትዕይንት የዘንድሮው (እ.ኤ.አ. 2013) ኢትዮጵያዊት ተሳታፊዋ መምህርት ቤቲ (Betty) ከሴራሊዮናዊው ተሳታፊ ቦልት (Bolt) ጋር ወሲብ ፈፅማለች የሚለው ዜና ከወጣ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በሁለት ወገን የጦፈ የባሕል እና የሞራል ጥያቄዎችን በማንሳት እየተሟጎቱ ነው፡፡