ታሪኮች ስለ ብሔር እና ዘር
የምሥራቁ ኢትዮጵያ ግጭት ዝርዝር ሁኔታ
በቅርብ ግዜ የተከሰተው ግጭት በኢትዮጵያ ለደርዘኖች ሞት፣ ከሺሕዎች ስደት መንስዔ ሆኗል። የግጭቱ መነሾ አሁንም የውኃ እና የደረቅ መሬት ሀብት ጉዳይ ነው።
ለምን አንዳንድ ቻይኖች በኪያኦቢ የማጠቢያ ኬሚካል ማስታወቂያ ውስጥ ያለው ዘረኝነት አልታያቸውም?
"ቻይኖች ከነጮች ዕኩል ሕዝቦች መሆን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ልክ እንደነጮች ሁሉ፣ ከፍ ያለ ደረጃን መጎናፀፍ የሚፈልጉት ጥቁሮች ላይ በመቆም ነው"
የኦሮሞ ሙዚቀኞችን የማፈን አሳፋሪ ገመና
የመንግሥት ሳንሱርን ለመስበር አማራጭ ይዞ የመጣውን ኢንተርኔት በመጠቀም፣ በዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ዩቱዩብ እና ፌስቡክ ላይ በተደረገ ቆጠራ ብቻ ከ300 በላይ ፖለቲካ ነክ ዘፈኖች ከ2006 ወዲህ የተለቀቁ መሆኑ የፖለቲካ ዘፈኖች መነሳሳት አለ ብሎ ለማለት ያስችላል፡፡
የ2013ቱን የአፍሪካ አገራት ዋንጫ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ባንዲራ ውልብልቢት እያደመቁት ነው
በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከባለፈው ዓመት የ2012 የአፍሪካ አገራት ዋንጫ ሻምፒዮን ጋር በኔልስፕሩት፣ ደቡብአፍሪካ ያደረገውን ከባድ ግጥሚያ በድምቀት እያከበሩ ነው፡፡ ከኢትዮጵያውያኑ ውብ አጨዋወት እና ከረዥም ጊዜ መጥፋት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ከታየው ድንቅ የተጫዋቾች ችሎታ ባሻገር፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከኳሱ ጎንለጎን ማዕከላዊ የውይይት አጀንዳ ለመሆን በቅቶ ነበር፡፡ በስታዲየሙ ጨዋታውን ለመመልከት የገቡት ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ጽሑፎችን እና ባንዲራዎችን ሲያውለበልቡ ታይተዋል፡፡
በሴኔጋል ቆዳን ‹‹ሙሉ በሙሉ ነጭ›› የሚያደርገው ክሬም ቁጣ ቀሰቀሰ
በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ቆዳን ማቅላት የተለመደ እና በህግም የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ቆዳን ለማቅላት ጥቅም ላይ የሚውሉ ክሬሞች አጠቃቀም ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ በፊት ላይ ምልክት መተው፣...