See all those languages up there? We translate Global Voices stories to make the world's citizen media available to everyone.

ተሳተፉ

እንደአንባቢም ሆነ እንደአስተዋጽዖ አበርካች ‘የዓለም ድምጾች’ ማኅበረሰብ አካል መሆን  በጣም የሚያረካ ልምድ ነው፡፡ ስለ ‘የዓለም ድምጾች’ ተጨማሪ መረጃ እንዲኖራችሁ፣ እባካችሁ የተደጋጋሚ ጥያቄዎችና መልሶቻችንን ተመልከቱ፡፡

ለመሳተፍ የሚያስችሉ ጥቂት መንገዶችን እዚህ ዘርዝረናል:

አገናኞቹኑን ተከትላችሁ እዩ

እያደገ የመጣውን የዜጎች መገናኛ ብዙሐን ለመርዳት ምርጡ መንገድ በጦማሮቻችን ላይ አገናኝ የምናስቀምጥላቸውን እና የምንጠቅሳቸውን ጦማሮች እና ድረአምባዎች መመልከት ነው፡፡ አገናኞቹን ተከተሉ፣ አስተያየታችሁን አስፍሩ እና ጦማሪዎቹን ከተለያዩ ቦታዎች እያነበባችኋቸው እንደሆነ አሳውቋቸው፡፡

እራሳችሁ ጦማሪዎች ከሆናችሁም፣ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ያሉ ሌሎች ጦማሮችን ምልከታ እየተመለከታችሁ አስተያየታችሁን እንድታንፀባርቁ እንጋብዛችኋለን፡፡ ከተለመደው የመገናኛ ብዙሐን ወጣ ያለ ነገር ሞክሩ፡፡ የዓለም ውይይት የሚጀምረው ከእናንተ ነው!

ደንበኛ ሁኑ

ከኛ ጋር ሁሌም ተገናኙ!

  • ለየዕለት ጽሑፎቻችን ደንበኛ ለመሆን በኢሜይል ተከታተሉን፣
  • ትዊተር ገጻችን ተከታይ ሁኑ፣
  • ፌስቡክ ላይም አብራችሁን ሁኑ፡፡

ለግሱ

ልገሳ ለማድረግ አቅማችሁ ከፈቀደ፣ መጠኑ የቱንም ያህል ቢሆን እናመሰግናለን፡፡ ለስራችን ለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ እናመሰግናለን፡፡

ሐሳብ አዋጡ

የክልሉ እና ቋንቋ አርታኢዎቻችን ለማንኛውም ሐሳብ እና አስተያየታችሁ ምስጋናቸው የላቀ ነው፡፡ ግባችን በዓለም ዙሪያ ብዙም ተሰሚነት የሌላቸውን የዜጎች መገናኛ ብዙሐንን እንዲሰሙ ማድረግ ነው፡፡

ምናልባትም፣ ልናገናኘው የሚገባን ጦማር ወይም ድረአምባ ካወቃችሁ (የራሳችሁም ቢሆን?) እባካችሁ  አገናኙን ላኩልን፡፡ በተጨማሪም በማን እና ስለምን እንደሚጻፍ ንገሩን፡፡

አርታኢዎቹን ለማግኘት፣ አግኙን የሚለው ቅጽ ላይ አገራችሁን በመምረጥ ኢሜይል ጻፉ፡፡

የዓለም ድምጾችን ግዙ

‘የዓለም ድምጾች’ን ከወደዳችሁት፣ የሚያምሩ ቲሸርቶቻችንን ወይም ባለኮፍያ ሹራቦቻችንን ለብሶ ከማሳየት በላይ የበለጠ ቀላል መንገድ የለም፡፡

RedBubble.com ላይ ግዚ መፈፀም ትችላላችሁ፡፡

ቲሸርቶ በተለያየ ቀለም፣ ቅርፅ እና ሳይዝ ቀርበዋል፡፡ በጥሩ ዋጋ ለደንበኞች የሚያደርሱ እና በጥራት የሚያትሙ አቅራቢዎችን መርጠናል፡፡

በነዚህ ሽያጮች የምናተርፈው ምንም ገንዘብ የለም፡፡ ስለዚህ የመግዛት ግዴታ የለባችሁም፡፡ በርግጥ፣ ‘የዓለም ድምጾች’ ላይ የምንሰራውን ሥራ ለመደገፍ ስጦታ ካቀረባችሁልን፣ በደስታ እንቀበላለን!

ጸሐፊ ሁኑ

‘የዓለም ድምጾች’ በዓለም ዙሪያ ያሉ ዕለታዊ ውይይቶችን አጠቃልሎ ለማቅረብ የሚተማመነው በበጎ ፈቃደኛ ጸሐፊዎቹ ነው፡፡  በተለመደው መገናኛ ብዙሐን ትኩረት ስለተነፈገው አገር ወይም ጉዳይ እየጦመራችሁ ነው? በጡመራ መድረኮች ላይ ያሉ ውይይቶችን በአገራችሁ ወይም በቅጡ በምታውቁት አገር ውስጥ ስለሚካሄዱ ጉዳዮች እየተከታተላችሁ ነው?

የምንሰጠው ሽፋን እንዲያድግ ከፈለጋችሁ፣ እባካችሁ ከታች ያለውን አገናኝ ጠቅ በማድረግ የሚመጣውን ቅጽ ሙሉልን፡፡

‘የዓለም ድምጾች’ ጸሐፊ ለመሆን አመልክቱ »

በማስተርጎም እርዱን

‘የዓለም ድምጾች’ ታሪኮች ብዙውን ጊዜ በሊንጓ አስተርጓሚዎቻችን አማካይነት ወደብዙ ቋንቋዎች ይተረጎማሉ፡፡ ለምሳሌ ስፓኒሽ፣ ቻይኒዝ፣ ፍሬንች፣ አራቢክ እና ሌሎችንም ቋንቋዎች ዝርዝር ከላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡  እናንተም እንደ በጎ ፈቃደኛ አስተርጓሚ ወይም ማረጋገጫ ንባብ (proofreader) ላይ ልትረዱን ትችላላችሁ፡፡

የእናንተ ቋንቋ ከዝርዝሩ ውስጥ ከሌለ፣ የራሳችሁን ቡድን በመመስረት የራሳችሁን ቋንቋ አካታችሁ መጀመር ትችላላችሁ፡፡

የሊንጓ አስተርጓሚ/ማረጋገጫ ንባብ ለማድረግ አመልክቱ »

በፕሮጀክቶቻችን ተሳትፎ አድርጉ

‘የዓለም ድምጾች’ የናንተን እርዳታ የሚሹ የተለያዩ ተከታታይ ፕሮጀክቶች አሉት፡፡  እስኪ ተመልከቷቸው!

የእኛን ባጅ እና ዜና በጦማራችሁ ላይ ጨምሩ

በዓለም ዙሪያ ያሉ ጦማሪዎች  — እባካቸሁ ከ‘የዓለም ድምጾች’ ጋር ተገናኙ! እናንተ ከደገፋችሁን ጦማራችሁ ላይ የእኛን ባጅ በመለጠፍ አሳዩ (እንዴት ለሚለው ከታች ተመልከቱ)፡፡

RSS feeds ላይም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ (ለምሳሌ ብትጨምሩን “ኢትዮጵያ እና “ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት”) ደስተኞች ነን፡፡ “

'የዓለም ድምጾች' - ዓለም እያወራ ነው፣ እርስዎስ ያደምጣሉ?
'የዓለም ድምጾች' - ዓለም እያወራ ነው፣ እርስዎስ ያደምጣሉ?
'የዓለም ድምጾች' - ዓለም እያወራ ነው፣ እርስዎስ ያደምጣሉ?