ታሪኮች ስለ የንግግር ነፃነት ከ ጥቅምት, 2012
ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያውያን የቡድናቸውን ማሸነፍ በጉጉት እየተጠባበቁ ነው
ምንም እንኳን የእግርኳስ ውጤት በአብዛኛው በጨዋታዎች እለት በሚፈጠሩ ክስተቶች ላይ ጥገኛ ቢሆንም ታሪክ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ያደላል። የሱዳን ብሄራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች በአንዱም ያላሸነፈ ሲሆን በአጠቃላይ ሁለቱ ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጓቸው ሶስት የማጣሪያ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ሶስቱንም ጨዋታዎች አሸንፋ ሰባት ጎሎችን ተጋጣሚዋ ሱዳን ላይ ስታስቆጥር፤ የተቆጠረባት አንድ ጎል ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር ተመዘበረ
በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር እራሳቸውን ራሳቸውን አርቲን ሐከርስ ብለው በሚጠሩ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ መካነ ድሮች ሲመዘበሩ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ ብቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፐሬሽን፣ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሌሎች መካነ ድሮች ተመዝብረዋል፡፡ ይህን ተከትሎ...