‘የዓለም ድምጾች’ ማኒፌስቶ

በነፃነት በመናገር እናምናለን፤ የመናገርን ነፃነት ለመጠበቅ — እና የመስማትንም መብት፡፡ በንግግር ማስተላለፊያ መሳሪያዎች ሁሉንአቀፍ ተዳራሽነት እናምናለን፡፡

ለዚህም፣ መናገር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ሐሳቡን የሚገልጽበት መንገድ እንዲኖረው እንፈልጋለን — እናም ይህንን ንግግር መስማት ለሚፈልገው ደግሞ የሚሰማበትን መንገድ፡፡

ለአዳዲስ መሳሪያዎች/መንገዶች ምስጋና ይግባቸው፣ ንግግር/ሐሳብ በአታሚዎች እና አሰራጪዎች ቁጥጥር ስር የሚወድቅበት ዘመን አልፏል፡፡ አሁን፣ ማንኛውም ሰው የፕሬስ አቅም ማዳበር ይችላል፡፡ ሁሉም ሰው የግል ታሪኩን ለዓለም ማድረስ ይችላል፡፡

ሕዝቦችን በሚከፋፍሉ ባሰላጤዎች መካከል ከፍተኛ የእርስበእርስ መግባባት ላይ መድረስ እንዲችሉ የግንኙነት ድልድይ መገንባት እንፈልጋለን፡፡ በጋራ የተሻለ ነገር በመስራት፣ በበለጠ በኃይል መተግበር እንፈልጋለን፡፡

በቀጥተኛ ግንኙነት ጉልበት/ኃይለኝነት እናምናለን፡፡ ከተለያየ ዓለም በመጡ በግለሰቦች መካከል የሚመሰረተው ግንኙነት የግል፣ የፖለቲካ እና የኃይልም ነው፡፡  ድንበር ተሻጋሪ ውይይት ለነፃ፣ ሚዛናዊ፣ የበለፀገ እና ቀጣይ ነጋችን ወሳኝ እንደሆነ እናምናለን – ለሁሉም የፕላኔታችን ዜጎች፡፡

እንደግለሰቦች እየሰራንና እየተናገርን ሳለ፣ የጋራ ፍላጎትና ዓላማችንን ለይተን ማራመድም እንፈልጋለን፡፡ አንዳችን ለሌላችን የክብር፣ የመተጋገዝ፣ የመማማር እና የመደማመጥን  ልምድ እንቀስማለን

እኛ ‘የዓለም ድምጾች’ ነን፡፡