ቭየትናም ውስጥ የወጣው አዲሱ የመረጃ መረብ ደህንነት ህግ፣ ጥብቅ የድረ-ገጽ ቁጥጥር በሰፋ መልኩ ለማድረግ፣ ግላዊ ምስጢሮችን ለሚመዘብሩ የመረጃ ልውውጦችና የተከለከሉ መልዕክቶችን ለሚያሰራጩና ለሚያትሙ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ግለሰቦች የሚቀርበውን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማቋረጥ የሚያስችል ሰፊ ዕድልን ፈጥሯል፡፡
ተቺዎች ይህ ህግ ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብትን በከፋ መልኩ እንደሚደፈጥጥ ፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ይናገራሉ፡፡
አናሳ የሆኑ የተቃውሞ ድምፆች ከጥቂት የህግ ባለሙያዎችና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቢያሰሙም፣ ህጉ ግን በሃገሪቱ የህዝብ ደህንነት ሚኒስቴር ተረቅቆ፣ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የተሰበሰበው ብሄራዊ ሸንጎ ረቂቅ ህጉን ለቀጣይ ሂደት አስተላልፎታል፡፡ ህጉ ተፈፃሚ የሚሆነው ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡
በተጨማሪም፣ ህጉ አስገዳጅ ቅድመ-ሁኔታዎችን ለውጭ ሃገር የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አስቀምጧል፡፡ ቻይና 2017 ላይ ያወጣችው የመረጃ መረብ ደህንነት ህግ ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ የቭየትናም አዲሱ ህግ የኢንተርኔት አገልግሎትን የሚያቀርቡ ኩባንያዎች የስራ መረጃዎቻቸውን በሃገር ውስጥ እንዲያከማቹና ዋና ፅህፈት ቤታቸውን ወይም ወኪል ቢሯቸውን እዛው ቭየትናም ውስጥ እንዲከፍቱ ያስገድዳል፡፡
ህጉ ውስጥ የተጠቀሰው አንቀፅ 26 የውጭ ሃገር የቴክኖሎጂ ተቋማት እንዲህ እንዲያደርጉ ያዝዛል፣
“establish mechanisms to verify information when users register their digital accounts”;
“provide user information to the specialized task force for cyber security protection under the Ministry of Public Security upon receiving written requests”;
“erase information, prevent the sharing of information that has content” prohibited by the Vietnamese government “within 24 hours of receiving a request” from the Ministry of Information and Communications or Ministry of Public Security; and
“not provide or stop providing services on telecommunication networks, Internet, and value-added services for organizations and individuals that publish on cyberspace” content prohibited by the Vietnamese government.
“ደንበኞች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ውስጥ የራሳቸውን አካውንት በሚከፍቱበት ወቅት፣ ስለእነርሱ የተገለፀ መረጃ ካለ ለማጣራት የሚያስችል አሰራር መዘርጋት አለባቸው፡፡
“በህዝብ ደህንነት ሚኒስቴር ስር የተቋቋመው የመረጃ መረብ ጥበቃ ልዩ ግብረ-ሃይል፣ የደንበኞችን መረጃ ከፈለገና በፅሁፍ ካመለከተ፣ መረጃውን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
“በቭየትናም መንግስት የተከለከሉ መልዕክቶች እንዳይሰራጩ፣ ተሰራጭተው ከተገኙም ወዲያውኑ- በ24 ሰዓት ውስጥ ማፈን አለባቸው፤ ከመረጃና ኮሙዩኒኬሽንስ ሚኒስቴርና ከህዝብ ደህንነት ሚኒስቴር ትዕዛዝ ከተሰጠ፡፡ እና፣
“ድር-አምባ ውስጥ በመንግስት የተከለከሉ መልዕክቶችን ለሚያሰራጩ ግለሰቦች ወይንም ድርጅቶች የሚያቀርቡትን የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ የኢንተርኔትና ዕሴት የተጨመረባቸው ሌሎች አገልግሎቶችን ማቋረጥ ወይንም እስከመጨረሻው ማቆም አለባቸው፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች በህጉ ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንድ አንቀፆች ባለስልጣናት አክቲቪስቶችንና የመንግስት ተቃዋሚዎችን ለማሰር እንደሚጠቀሙባቸው አረጋግጧል ፣
Prohibiting “the use of cyberspace” to “prepare, post, and spread information” that “has the content of propaganda opposing the State of the Socialist Republic of Vietnam,” or “offends the nation, the national flag, the national emblem, the national anthem, great people, leaders, notable people, and national heroes” (Articles 8 and 15);
Prohibiting the use of cyberspace “to organize, carry out, collude, urge, buy off, dupe, entice, train, or coach people to oppose the State of the Socialist Republic of Vietnam,” or “to distort history, deny revolutionary achievements, [or] undermine national solidarity” (Article 8);
Prohibiting propaganda against the Socialist Republic of Vietnam, including “psychological warfare,” “defamatory propaganda against the people’s administration,” “false information intended to seriously harm human dignity or honor or cause damage” – but no requirement that the person putting forward the information has to know it is false;
“…information that propagandizes, urges, campaigns, incites, threatens, causes division, [or] entices people to gather and cause disruption” (Articles 8 and 15).
ድር-አምባን ለመገደብ ያስፈለገው “የቭየትናም ሶሻሊስት ሪፖብሊክ መንግስትን የሚቃወም መልዕክት በማንኛውም አካል እንዳይዘጋጅ፣ እንዳይታተምና እንዳይስራጭ” ወይም “ሃገሪቱን፣ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማን፣ ብሄራዊ አርማን፣ ብሄራዊ መዝሙርን፣ ታላቁን ህዝብ፣ መሪዎችንና የሃገር ባለውለታዎችን የሚዳፈር መልዕክት እንዳይሰራጭ ነው፡፡” (አንቀፅ 8 እና 15)
ድር-አምባን ለመገደብ ያስፈለገው “ህዝቡ የቭየትናምን ሶሻሊስት ሪፖብሊክ ተደራጅቶ፣ ቆርጦ፣ ተነሳስቶ፣ ተስማምቶ፣ ተማልሎ፣ በቀላሉ ተታልሎ፣ ሰልጥኖ እንዳይቃወም ነው፡፡” ወይም “ታሪክ፣ አብዮታዊ ድሎች (ወይም) ሃገራዊ አንድነት እንዳይኮስሱ ነው፡፡” (አንቀፅ 8)
የቭየትናም ሶሻሊስት ሪፖብሊክ ላይ የሚሰነዘሩ “ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶችን”፣ “በህዝቡ ይሁንታ የተመሰረተው ህዝባዊ አስተዳደር ላይ የሚቃጣውን ስም-አጥፊ ፕሮፖጋንዳ”ና “የሰውነትን ክብር ለማዝቀጥ ወይም ለማጥፋት የሚሰራጩ የውሸት መረጃዎችን” ለመገደብ ነው፤ ነገር ግን አንድ ሰው ያሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን ሊረዳ የሚችልበት ሁኔታ አልተፈጠረም፡፡
“…ህዝብን በጋራ ለግጭት የሚያነሳሳ፣ ክፍፍልን የሚፈጥር፣ የሚቀሰቀስ፣ ሽብር የሚነዛ፣ የሚያሰጋና የሚ’ነዛ መረጃ፡፡” (አንቀፅ 8 እና 15)
የቭየትናም ኮሙዩኒስት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ነጉየን ፉ ትሮንግ፣ ይህ ህግ ለቭየትናም ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ሲናገሩ፣
There are people who take advantage of the Internet to instigate protests and disruptive behavior aimed at overthrowing the government. We need this law to protect this regime.
መንግስትን በሃይል ለመጣልና አመፅ ለመቀስቀስ ኢንተርኔትን እንደዋነኛ መሳሪያ የሚጠቀሙ ወገኖች አሉ፡፡ እኛ ይህን ህግ የምንፈልገው መንግስት ከጥቃት መጠበቅ ስላለበት ነው፡፡
መንግስት ህጉ በርካታ ቴክኖሎጂ-ነክ ስራዎችን እንደሚፈጥር ና የዲጂታል ኢኮኖሚውንም እንደሚያበረታታ ይናገራል፡፡ የእስያ ኢንተርኔት ጥምረት ግን ከመንግስት ጋር የሚቃረን ዕይታ አለው፣
…these provisions will result in severe limitations on Vietnam’s digital economy, dampening the foreign investment climate and hurting opportunities for local businesses and SMEs to flourish inside and beyond Vietnam.
የህጉ አንቀፆች በቭየትናም የዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ፤ የውጭ ኢንቨሰትመንት በከፋ ደረጃ እንዲቀንስ ያደርጋሉ፡፡ ለሃገር ውስጥ የንግድ ተቋማት ምቹ ዕድል እንዳይኖርም ያደርጋሉ፡፡ እናም፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከቭየትናም ውጭም ሆነ እዛው- ሃገር ውስጥ እንዳያድጉ እክል ይፈጥራሉ፡፡
ባለስልጣናቱ እንደተናገሩት የውጭ ሃገር ኩባንያዎች- ጎግልንና ፌስቡክን ጨምሮ፣ አዲሱ ህግ ላይ ቅሬታቸውን አላቀረቡም ፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ ኩባንያዎቹ ለሰብዓዊ መብቶች መጠበቅ ያላቸውን ታማኝነት በማስታወስ፣
Your company has a responsibility to respect the right to privacy and freedom of expression. This responsibility exists over and above domestic legal requirements.
Amnesty International calls on your company to challenge the draft law and make known to the Vietnamese government your company’s principled opposition to implementing any requests or directives which violate fundamental human rights.
ድርጅቶቹ ምስጢር የመጠበቅና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የማሰከበር ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህ ሃላፊነትም ከሃገር ውስጥ አፋኝ ህጎች በላይ ነው፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ድርጅቶቹ ተረቅቆ የፀደቀውን ህግ እንዲቃወሙና የቭየትናም መንግስት የሚያቀርበውን ማንኛውንም ሰብዓዊ መብትን የሚጥስ ጥያቄ ወይንም ትዕዛዝ እንዲቃወሙ ጥሪ ያቀርባል፡፡
በእስያ የተ.መ.ድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ስለህጉ ያለውን አስተያየት እንደሚከተለው ገልጧል፣
#VIETNAM: @OHCHRASIA is concerned that this law may be used to further crack down on dissenting voices in the country. We encourage the Government of Viet Nam to provide an enabling environment where freedom of expression, both online and offline, is protected.
— UN Human Rights Asia (@OHCHRAsia) June 14, 2018
#ቭየትናም፤ የመረጃ ደህንነት ህጉ ለባለስልጣናት የቴክኖሎጂ ተቋማት ላይ የጠለቀ ተፅዕኖ እንዲያሳርፉና አገልግሎት ሰጪዎች የስራ መረጃዎቻቸውን- የደንበኛ ግላዊ መረጃን ጨምሮ- አንዲያስረክቡ፣ አዲስ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡
#ቭየትናም፤ ኮሚሽነሩ(@OHCHRASIA) ይህ ህግ ተቃዋሚ ድምፆችን በይበልጥ እንዳያዳፍን ይሰጋል፡፡ የቭየትናም መንግስት- በመደበኛም ሆነ በኢ-መደበኛ መልኩ- ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን እንዲጠብቅ ያበረታታል፡፡
በህጉ ላይ የሚደረጉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች
ሰኔ 10 በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቭየትናማውያን በመላ ሃገሪቱ ሁለቱን የህግ ረቂቆችን- ማለትም የመረጃ መረብ ደህንነት የህግ ረቂቅ (እስከአሁን ድረስ እየተረቀቀ ያለ፡)ና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን የሚመለከት ህግ (SEZ)፣ ሂደታዊ የሆነ አሰራር ሲሆን፣ ገበያ፣ ኢንቨስትመንትና የመረጃ ግንኙነቶችን የሚያሳጣ ህግ ነው፡፡
ተቃዋሚዎቹ በአብዛኛው ያተኮሩት ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ህግ ላይ ነው፡፡ እንደተቃዋሚዎች አባባል፣ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ህግ የሃገሪቱን ሃብቶች በቻይና እንዲበዘበዙ ዕድልን ይፈጥራል፡፡ ቢሆንም ፣ አክትቪስቶቹ የመረጃ ደህንነት ህግ ወደቀጣዩ ሂደት ማለፉን ተከትሎ፣ የተቀናጀ ተቃውሞ እያካሄዱ ነው፡፡
Mass protests have taken place in Ho Chi Minh City, Nha Trang and Hanoi against the draft laws on special admin-econ zones and on cyber security. Soon dispersed by police, some reported arrests #Vietnam #protest #politics pic.twitter.com/rMRIn6Zrqt
— Nga Pham (@ngaphambbc) June 10, 2018
በተረቀቁት ህጎች ላይ- በመረጃ ደህንነት ህግና በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ህግ ላይ ያተኮሩ፣ ጠንካራ የተቃውሞ ሰልፎች በሆ ቺ ሚኒህ፣ በነሃ ትራንግና በሃኖይ ተካሂደዋል፡፡ ሰልፎቹ በፖሊስ ተበትነዋል፤ አንዳንድ ወገኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰልፈኞች እንዳሉ ገልፀዋል፡፡ #ቭየትናም#አመጽ#politics
አክትቪስቶች እንደገመቱት ከሆነ፣ ከመቶ በላይ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከእነርሱ ውስጥም የአሜሪካ ዜግነት ያለው ዊልያም ንጉየን አንዱ ነው፡፡
ሰኔ 11 ላይ 74 የህግ ባለሙያዎች ለፓርላማው የመረጃ ደህንነት ረቂቅ ህጉ ላይ የሚታዩትን ክፍተቶች ጠቁመው፣ ህገ-መንግስቱ ውስጥ የተጠቀሱትን የሰብዓዊ መብት አንቀፆችን እንደሚፃረር አስምረው፣ ፊርማ አሰባስበው ጥያቄያቸውን አስገብተዋል፡፡ ከጥያቄዎቻቸው ጋር አያይዘው ያስገቡት ፊርማ በኢንተርኔት አማካኝነት ከ40,000 በላይ ዜጎች የተሰበሰበ ነው፤ ረቂቅ ህጉን ፓርላማው እንዳያፀድቀው ተማፅነዋል፡፡
ይህ ሁሉ ተቃውሞ ከህዝቡ ቢቀርብም፣ ብሄራዊ ሸንጎው የመረጃ ደህንነት ረቂቅ ህጉን በ423 ድጋፍ፣ በ15 ተቃውሞና በ28 ድምፀ-ታቅቦ፣ ሰኔ 12 ላይ ወደቀጣዩ ሂደት አሳልፎታል፡፡
ዳኛ ንጉየን ላን ሄዩ ባለስልጣናት የትኛው ድርጅት በድረ-ገፁ ላይ ህገ-ወጥ መልዕክትን እንዳካተተ ለይተው የሚያቀርቡበት አሰራር ለፍርድ ቤቶች እንዲሰጥ ይፈልጋሉ ፡፡
“ቭየትናም ቱደይ” እንደዘገበው በህግ አውጪው አካል ውስጥ እየታየ ያለው ተቃውሞ፣ ረቂቅ ህጉ ምን ያህል አነጋጋሪና ከፋፋይ እንደሆነ ያሳያል ፡፡
The sign of some dissent in the National Assembly is an indication of how controversial the new law is seen.
Even such limited opposition is extremely rare in a body normally seen as a rubber stamp legislature that is selected, directed and manipulated by the Communist party and its affiliate organisations.
በብሄራዊ ሸንጎው ውስጥ የታዬው ጥቂት የተቃውሞ ምልክት፣ የአዲሱ ህግ አወዛጋቢነትን ያሳያል፡፡
በኮሙዩኒስት ፓርቲውና ደጋፊዎቹ የተመሰረተና የሚመራ፣ እንደተላላኪ የሚቆጠር ተቋም ውስጥ እንዲህ ዓይነት ተቃውሞ የሚስተዋለው ከስንት አንዴ ነው፡፡
“እስያን ቱደይ” ባሳተመው ርዕሰ-አንቀፅ ላይ የቭየትናም መንግስትዕውነተኛ ፍላጎት ላይ በጉልህ አስምሮበታል ፣
Despite the government’s claims, control is at the heart of the new legislation.
With Vietnamese offices, the government could pressure companies to administer stricter censorship. They could also pressure them into revealing individual dissident identities.
Data localisation will erode user anonymity and pose a threat to government critics.
እንደመንግስት ማብራሪያ ከሆነ፣ ጥብቅ ቁጥጥር የአዲሱ ህግ ዋና ሃሳብ ነው፡፡
መንግስት በቭየትናም ቢሯቸውን የከፈቱ ኩባንያዎች ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ይገፋፋል፤ የተቃዋሚ ሰዎችን ግላዊ ምስጢሮች ለመንግስት እንዲያስረክቡ ይገደዳሉ፡፡
በሃገር ውስጥ ብቻ መረጃ የመለዋወጥ ሂደት የተጠቃሚውን አይታወቄነትን የሚሸረሽርና የመንግስት ተቃዋሚዎችን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡
የመረጃ መረብ ደህንነት ህጉ ወደቀጣይ ሂደት ከመተላለፉ በፊት፣ ቭየትናም የተለያዩ አወዛጋቢ ህጎችን በመጠቀም ፣ “ፀረ-መንግስት ፕሮፖጋንዳ”ን ያሰራጩ ግለሰቦችን እንደምታስር ይታወቃል፡፡ አዲሱ ህግ፣ ምንም እንኳ ከዓመት በኋላ ስራ ላይ የሚውል ቢሆንም፣ ኢንተርኔትን በመጠቀም ስለሃይማኖት ነፃነት፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ዴሞክራሲያዊ ለውጦች፣ ሲቪል መብቶችና ሰላማዊ ትግል የሚሟገቱ ቡድኖችን ወይንም ግለሰቦችን ለመጠነ-ሰፊ ጥቃት ያጋልጣል ፡፡