ሊባኖሳዊው ጋዜጠኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ፌስቡክ ላይ “ስለዘለፈ” በሌለበት የእስር ቅጣት ተፈርዶበታል

ከፋኢዳ የፌስቡክ ገፅ የተገኘ የራሱ- የፋኢዳ ኢታኒ ምስል፤ ፎቶ በዋሲም ናቡሊሲ

ሊባኖሳዊው ጋዜጠኛ ፌስቡክ ላይ በለጠፈው ፅሁፍ የውጭና የፍልሰተኞች ጉዳይ ሚኒስትርን- ጊብራን ባሲልን ስም የማጠልሸት ወንጀል ስለፈፀመ፣ በሌለበት ተከስሶ ነበር፡፡

ምዕራባዊ ሊባኖስ፣ ባብዳ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ፍርድ ቤት፣ ሰኔ 29፣ 2018 ፋኢዳ ኢታኒ ላይ የአራት ዓመት እስራትና 10 ሚሊየን የሊባኖስ ሊራ (ወደ6660 ዶላር የሚጠጋ፡፡) የገንዘብ መቀጮ በይኖበታል፡

ፈኢዳ ኢታኒ፣ የሶሪያና የስደተኞች ጉዳይ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው፡፡

ፌስቡክ ላይ የለጠፈው ፅሁፍ፣ ሊባኖስ ውስጥ በፖለቲካውም ሆነ በወታደራዊ እንቅስቃሴ፣ ጠንካራ የሆኑ አካላት ላይ ወሰብሰብ ያለ ተቃውሞ እንዲቀርብባቸው አነሳስቷል፡፡ ኢታኒ ባለፈው ዓመት አርሳል ውስጥ የሊባኖስ ጦር ካምፕ ውስጥ ለተጠለሉ- ለብዙ ሶሪያዊያን ሞት ምክንያት የሆነ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ፣ አጠንከሮ ተቃውሞ ነበር፡፡

ኢታኒ ስለሊባኖሳዊው የፖለቲካ ድርጅትና ወታደራዊ ቡድን- ሂዝቦላህ ያለውን አቋም ማንፀባረቁን ቀጠለ፤ ሂዝቦላህ ወደሶሪያ ገብቶ፣ ከአል-አሳድ አገዛዝ ጋር አብሮ በመቆም የሚያደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በይፋ ተቃውሟል፡፡

ከዚህ በኋላ፣ የፕሬዝደንቱና የጦር ሰራዊቱ ጠበቃዎች፣ ኢታኒ ላይ የክስ ዶሴ ከፈቱ፡፡ በአናቱም፣ ከሂዝቦላህ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች፣ ቀጥተኛ ዛቻ ለእርሱ መላክ ጀመሩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ፣ ኢታኒ ሃገሩን ጥሎ ወደብሪታንያ ተሰደደ፡፡

ኢታኒ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ለሚታተመው የሊባኖስ ጋዜጣ L'Orient le Jour እንዳብራራው ፣ በሊባኖስ ፕሬዝደንትና በጦር ሰራዊቱ የተከፈተው ክስ ተቋርጦ፣ ጊብራን ባሲል ባቀረቡት ክስ ተተክቷል፣

Je ne sais pas comment la première action judiciaire a disparu, ni ce qui a été concocté dans ce cadre entre les services de renseignements de l’armée et le président de la République, ou encore le Hezbollah (également visé par le post, et dont les intimidations contre M. Itani sont derrière son départ pour Londres, NDLR). Il semble toutefois que Gebran Bassil se soit porté volontaire pour intenter une action à leur place.

የመጀመሪያው የሕግ እርምጃ እንዴት ሊቋረጥ እንደቻለ አልገባኝም፤ በወታደራዊ ደህንነትና የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ወይም በሂዝቦላህ የተጠነሰሰውን ክስ ማለቴ ነው፡፡ ቢሆንም፣ ጊብራን ባሲል የእነርሱን ፈለግ ለመከተል ያሰቡ ይመስላሉ፡፡

ኢታኒ የክስ ወረቀት እንዳልደረሰውና ጉዳዩን ከሚዲያዎች እንደሰማ ተናግሯል ፡፡ በንግግር ነፃነት ዙሪያ ለሚሰራው- ለማሃራት ፋውንዴሽን አንደገለፀው፣ ከሚዲያ የሰማውን ጨምሮ፣ ዘጠኝ ክሶች ሚኒስትር ባሲል፣ እርሱ ላይ አቅርበዋል፡፡

ፈኢዳ ኢታኒ ፌስቡክና ትዊተር ላይ የዳኛውን ውሳኔ በብርቱ እንደሚቃወም ገልጧል፡፡ የእስር ውሳኔውን በማስመልከት የፃፈው ፅሁፍ ላይም፣ ‹‹ተጨማሪ አፈናና ተጨማሪ ውንብድና›› ሲል ተችቷል፡፡

ኢታኒ ላይ የተጣለውን ቅጣት፣ አንዳንድ የሊባኖስና ዓለም-አቀፍ ተቋማት በመቃወም፣ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

በሂዩማን ራይትስ ዎች የሊባኖስ ጉዳይ አጥኚ የሆኑት ባሳም ካዋጃ ለጋዜጠኞች በላኩት የኢሜል መልዕክት፣ አንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፣

Sentencing a journalist to four months in prison for a critical Facebook post is an outrageous attack on free speech that lays bare the lack of meaningful protections for freedom of expression in Lebanon. Lebanon’s new parliament should act quickly to abolish laws that criminalize defamation, which are disproportionate, unnecessary, and violate international human rights law.

አንድ ጋዜጠኛ ፌስቡክ ላይ በፃፈው ተቺ ፅሁፍ ምክንያት ለአራት ወራት እንዲታሰር መፍረድ፣ የንግግር ነፃነት ላይ የተፈፀመ ድፍረት፣ አንዲሁም ሊባኖስ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ትርጉም ባለው ሁኔታ እንደማይጠበቅ ያጋለጠ ነው፡፡ የሊባኖስ አዲሱ ፓርላማ ዓለም-አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕግጋትን የሚጥሱትን፣ አላስፈላጊዎቹንና ኢ-ፍትሃዊዎቹን የስም ማጥፋት ወንጀልን ለመቅረፍ የወጡትን ሕጎች በአስቸኳይ መሰረዝ አለበት፡፡

የሊባኖስ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስም ማጥፋትን እንደወንጀል የሚቆጥርና በፕሬዝደንቱ፣ በባንዲራውና በሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት መሳለቅ ላይ ልዩ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው፡፡ የሃገሪቱ ወታደራዊ ሕግ ‹‹በባንዲራው ወይም በሰራዊቱ መቀለድ››ን እንደወንጀል ይቆጥራል፡፡ የተዘረዘሩት ወንጀሎችን መፈፀም፣ የገንዘብ ቅጣትና እስር ያስፈርዳል፤ ለጋዜጠኝነት ስራ ልዩ ከለላ አልተሰጠም፡፡

ፍሪደምሃውስ 2016 ላይ ስለሊባኖስ ባወጣው ዘገባ መሰረት፣

Lebanese journalists complain that media laws are chaotic, contradictory, and ambiguously worded. Provisions concerning the media, which justify the prosecution of journalists, can be found in the penal code, the Publications Law, the 1994 Audiovisual Media Law, and the military justice code.

ሊባኖሳዊያን ጋዜጠኞች የሚዲያ ሕጎቹ እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ፣ ምስቅልቅላቸው የወጣና በአሻሚ ቃላት የተሞሉ መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡ ጋዜጠኞችን ለመክሰስ የሚውሉ፣ ስለሚዲያ የሚያወሩ አንቀፆች፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ውስጥ አሉ፤ የህትመት ሕግ፣ 1994 ላይ የወጣው- የኦዲዮቪዥዋል ሚዲያ ሕግና ወታደራዊ ሕጉ ከዚሁ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

ሊባኖስ ውስጥ የንግግር ነፃነት ላይ ጫና መፈጠር

በሊባኖስ የሕግ ሁኔታ ውስጥ ጋዜጠኞች ላይ ክሶች መቅረባቸው፣ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ ግን ክሶች ተደጋግመው ጋዜጠኞች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዎችና አስተያየት ሰጪዎች ላይ እየቀረቡ ነው፡፡

የቴሌቪዥን የኮሜዲ ፕሮግራም የሚያቀርበው፣ ሂሻም ሃዳድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ- ሳዕድ ሃረሪና በሳዑዲው ንጉስ መሃመድ ቤን ሰልማን ላይ በመቀለዱ ምክንያት፤ ጥር 24፣ 2018 ላይ ተከስሷል፡፡

Lebanon Debate የጉምሩክ ዲሬክተሩን ስም በማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ፣ መጋቢት፣ 2018 ላይ ለስድስት ወራት እንዲታሰርና 10 ሚሊየን የሊባኖስ ሊራ እንዲቀጣ ተፈርዶበታል፡፡

ሊባኖሳዊው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ማርሴል ጋኔም አንግዳ አድርጎ ያቀረባቸው፣ ፕሬዝደንት ኡውንና ሚኒስትር ባሲልን ‹‹የሂዝቦላህን የሽብር እንቅስቃሴ ይደግፋሉ›› ብለው የተቹ- ሁለት የሳዑዲ ጋዜጠኞች ላይ የቀረበውን ክስ ከተከላከለ በኋላ፣ ሕጋዊነትን በመፃረር ክስ እንደገና ተከስሷል፡፡ ጋኔም ላይ የቀረበው ከስ ቆይቶ ውድቅ ተደርጓል፡፡

L'Orient Le Jour ጋዜጣ በቀረበ ፅሁፍ ማርሴል ጋኔም ‹‹ገዢው ቡድን ሽብርተኝነትን ወይም እስራኤልን በመፋለም ስም›› ጋዜጠኞችን እንደሚያስርና እንደሚወነጅል ተናግሯል፡፡

የሚዲያ ሰዎች ላይ የስም ማጥፋት ክሶችን የሚያቀርቡት መንግስታዊ ፍርድ ቤቶች ብቻ አይደሉም፡፡ ጥር 10፣ 2018 ላይ የለየለት ጨካኝ እንደሆነ የሚገለጽለት ወታደራዊ ፍረድ ቤት፤ ሊባኖሳዊቷ ጋዜጠኛና አጥኚ ሃኒን ጋዳር 2014 አሜሪካ ውስጥ የተካሄደ ስብሰባ በመገኘት፣ የሊባኖስን ጦር ስም በማጥፋቷ፣ በሌለችበት ፈርዶባት ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

ይህ ከሆነ ከአስር ቀናት በኋላ፣ ወታደራዊ ደህንነቱ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ የሆነው፣ ኦቫዳ ዩሱፍ ፌስቡክ ላይ በፃፈው ፅሁፍ ሰበብ፣ ከስሶት ነበር፡፡ዩሱፍ ለሂዩማን ራይትስ ዎች እንደተናገረው ለአራት ቀናት በጦርና በፖሊስ ሰራዊት አማካኝነት ታስሮ ነበር፡፡

ለሚዲያና የንግግር ነፃነት የሚታገለው፣ ማሃራት ፋውንዴሽን ለሊባኖስ የሕግ ሃላፊዎች፣ ባለስልጣናትን የመተቸት መብት እንዲያስከብሩ ጥሪ አቅርቧል

 تطالب “مهارات” المجلس النيابي الجديد بالتسريع لإقرار الاصلاحات التي تقدمت به مهارات مع النائب غسان مخيبر وأبرزها الغاء عقوبة الحبس ومنع التوقيف الاحتياطي عن كل من يعبر عن رأيه بأي وسيلة ضمنها الانترنت وتوسيع مفهوم نقد الشخص العام.

ማሃራት አዲሱ ፓርላማ በተከበሩ ጋሰን ሙካቢር የቀረበውን- ማንም ሰው ኢንተርኔትና ተዛማጅ መድረኮች ላይ ሃሳቡን ስለገለፀ ብቻ የሚታሰርበትን ሁኔታ አንዳይኖር የሚያደርግ የሕግ ማሻሻያ ሃሳብ ተቀብሎ፣ በአፋጣኝ እንዲያጸድቅ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በአሁኑ ሰዓት እየተደረጉ ያሉት ጥረቶች፣ ሃገሪቷ ውስጥ ዕውነተኛ ለውጥን ያመጡ እንደሆነ፣ በጊዜ ሂደት ውስጥ የምንመለከት ይሆናል፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.