ታሪኮች ስለ የሰብአውያውያን ምላሽ
ሳኡዲአረቢያን መሰናበቻው ቀነ ገደብ ሲቃረብ፣ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል
"ጥቃት ሊደርስባቸው እንደሚችል እያወቁ ብዙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት ለመመለስ ፍላጎት አለማሳየታቸው ያስደነግጣል።"
ኢትዮጵያ ‹ታይቶ ከማይታወቀው› የኢኮኖሚ ዕድገቷ በተፃራሪ ረኀብ ተጋርጦባታል
"ከኢትዮጵያ ውስጥ በተገኘ መረጃ መሠረት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች “ረኀብ፣ ችጋር ወይም ሞት” የሚሉ ቃላቶችን በምግብ ጥያቄዎቻቸው ውስጥ እንዳያካትቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡"
እ.ኤ.አ.2012፤ የፍራንኮፎኖች አብዮት እና ማኅበራዊ ለውጥ ዓመት፡- ክፍል 1
2012 አልቋል፤ እናም ለፍራንኮፎን (የፈረንሳይ ቅኝ [የነበሩ]) አገራት የተረጋጋ 2013 በጉጉት ይጠብቃሉ፡፡ በ2012 በማሊ፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ኮንጎ) እና በሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ የትጥቅ ትግል ተካሂዷል፡፡ በሴኔጋል፣ ኩዊቤክ እና ፈረንሳይ ደግሞ ምርጫ ተካሂዷል፡፡ በቻድ፣ ማዳጋስካር እና ቶጎ ደግሞ ለውጥን የሚጠይቁ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ በርካታ ክርክሮች ስደትን፣ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውሶችን እና እኩል የጋብቻ መብቶችን በተመለከተ ተደርገዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ የሆኑት ዓበይት ለውጦችን ለማምጣት ሲሆን መረጃ በመለዋወጥ ዘዴ ነው፡፡
በሴኔጋል ቆዳን ‹‹ሙሉ በሙሉ ነጭ›› የሚያደርገው ክሬም ቁጣ ቀሰቀሰ
በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ቆዳን ማቅላት የተለመደ እና በህግም የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ቆዳን ለማቅላት ጥቅም ላይ የሚውሉ ክሬሞች አጠቃቀም ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ በፊት ላይ ምልክት መተው፣...