ታሪኮች ስለ የንግግር ነፃነት ከ ሕዳር, 2012

ኢትዮጵያ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባል ለመሆን ትመጥናለች?

  16 ሕዳር 2012

በህዳር 12 2012 እ.ኤ.አ. የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት ሆነው ከተመረጡ አራት የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡ ለመጪዎቹ ሶስት አመታት የተመረጡ ሌሎች ሀገራት አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ኮትዲቯር፣ ኢስቶኒያ፣ ጋቦን ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ ፣ ጃፓን፣ ካዛኪስታን፣ ኬንያ ሞንቴኔግሮ፣ ፓኪስታን፣ የኮሪያ ሪፐብሊክ፣ ሴራሊዮን፣ የተባበሩት አረብ ኢመሬት፣ አሜሪካና ቬንዙዌላ ናቸው፡፡

‘ለሙሰኛ ባለስልጣን ምንም ምሕረት የለም’

  13 ሕዳር 2012

የጨፌ ኦሮሚያ የዜና ምንጮቻችን ለአዲስ ነገር እንዳስታወቁት አቶ አባዱላ ገመዳ ከጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ጋር የነበራቸው የሰመረ ግንኙነት ከተበላሸ (ፖለቲካዊ ጠቀሜታቸው ዝቅ ካለ) በኋላ ላለፉት በርካታ ዓመታት በእርሳቸው ሥም፣ በቤተሰቦቻቸውና በወዳጅ ዘመዶቻቸው አካባቢ ያከማቹትን ሃብት በጥሬ ገንዘብ፣ በአይነትና በንብረት በታማኝ የኦህዴድ ፓርቲ አባላትና በደህንነት ሠራተኞች ሲሰባሰብ ነበር፡፡ . . .”