ታሪኮች ስለ ጤና
በኬኒያ ቴሌቭዥን የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የሃይማኖት ተቋማትን አስቆጣ
በቅርቡ ለህዝብ አገልግሎት ይውል ዘንድ HIV እና ተዛማጅ በሽታዎችን ለመከላከል የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን ማስቆጣቱን ተከትሎ በመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፍ ታገዷል፡፡ ማስታቂያው አንዲት ባለትዳር ሴት ባለቤቷ ከትዳር ውጪ በሚያደርጋቸው የግብረስጋ ግንኙነቶች ኮንዶም እንዲጠቀም ምክር ስትሰጠው የሚያሳይ ሲሆን ማስታወቂያው የኬኒያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዩኤስ ኤድ እና ዩኬ ኤድ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለት የተዘጋጀ ነው፡፡
በሴኔጋል ቆዳን ‹‹ሙሉ በሙሉ ነጭ›› የሚያደርገው ክሬም ቁጣ ቀሰቀሰ
በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ቆዳን ማቅላት የተለመደ እና በህግም የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ቆዳን ለማቅላት ጥቅም ላይ የሚውሉ ክሬሞች አጠቃቀም ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ በፊት ላይ ምልክት መተው፣...