ታሪኮች ስለ ቴክኖሎጂ

የNSA ስለላን በተመለከተ ካርቱኖች ይላኩና፣ 1000 ዶላር ይሸለሙ

ዘ ዌብ ዊ ወንት ካርቱኒስቶችን፣ የዲዛይን ፈጣሪዎችን እና አርቲስቶችን መልሰን የምንታገልበት ቀን በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 11፣ 2014 የበይነመረብ ስለላን እና የግለሰብ ደኅንነት መብትን በተመለከተ ወጥ የካርቱኖች ውድድር ውስጥ እንዲሳተፉ እየጋበዘ ነው፡፡ ካርቱኖቹ በNSA (የአሜሪካው ብሔራዊ ደኅንነት ኤጀንሴ) ዙሪያ መረጃ ማስጨበጥ የሚችሉ እና በጥቅሉ ለሚደረጉ የበይነመረብ ስለላዎች ተጠያቂነትን የሚፈልጉ ሆነው...

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር ተመዘበረ

  1 ጥቅምት 2012

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር እራሳቸውን  ራሳቸውን አርቲን ሐከርስ ብለው በሚጠሩ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ  መካነ ድሮች ሲመዘበሩ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ ብቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፐሬሽን፣ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ  ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሌሎች መካነ ድሮች ተመዝብረዋል፡፡   ይህን ተከትሎ...

ኢራን ጎግል እና ጂሜል እንዳይታዩ አገደች

እገዳው የተላለፈበተት ምክንያት ህዝቡ ብዙዎች እንደ ስድብ ቃል የሚያዩት በዩቱዩብ የሚገኘውን ጸረ እስላም ፊልም እንዲቃወሙ ነው (ዩቲዩብ የጎግል ንብረት ነው)፡፡ ኮራማባዲ “የወንጀል ይዘት ያላቸው ቅጽበቶች ድንጋጌ ኮሚሽን” ቁልፍ አባል ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እንዳንዶች የጎግል መታገድ እውነተኛው ምክንያት ከመስከረም 22 ጀምሮ ስራ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀውን እስካሁን ግን ብቅ ያላለውን የኢራናውያን ብሔራዊ በየነ መረብ የበለጠ ለማስተዋወቅ ነው ሲሉ ከወዲሁ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ፤ መለስ ዜናዊ ከመቃብር ውስጥ ትዊት እያደረጉ ነው

  9 መስከረም 2012

"ከዚያ በኋላ ድንገት@PMMelesZenawi (መለስ ዜናዊ) ጣልቃ ገቡ፤ ከሞት በኋላ ለታንዛኒያው የፓርላማ አባል ዢቶ ካብዌ መልስ መስጠት ጀመሩ:: @PMMelesZenawi: @zittokabwe እባክዎ ከኔ የተሻለ ይሁኑ፡፡ እዚህ ቀልድ የለም፤ ዋጋዬን ልከፍል እየተዘጋጀሁ ነው" የሚለው መልስ በታንዛኒያ ከፍተኛ ውይይት ፈጠረ::