ታሪኮች ስለ 'የዓለም ድምጾች' አድቮኬሲ

ታንዛኒያዊው ፌስቡክ ላይ ፕሬዜዳንቱን ‘በመሳደቡ’ የሦስት ዓመታት እስር ይጠብቀዋል፡፡

  14 ሰኔ 2016

በታንዛኒያ የሳይበር ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ተቃዋሚዎች መንግስት ስልጣኑን የመስመር ላይ አራማጆችን ወይንም የማኀበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ለማጥቃት ሊጠቀምበት ይችላል የሚል ስጋታቸውን ቢያሰሙም ተግባር ላይ ውሎ ሰለባዎችን ወደወህኒ እያወረደ ነው፡፡

ለዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ለሀምሌ 24 በተዘጋጀው ትዊተር ማራቶን ላይ በመካፈል አጋርነቶዎን በተግባር ያሳዩ::

  30 ሐምሌ 2014

በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::

የትርጉም መርሐ ግብር፤ ዓለምአቀፍ የበየነ መረብ ነጻነትን ጥበቃ መግለጫ

ለተከታዮቹ ሰባት ቀናት የዓለም ድምፆች የቋንቋ በጎ ፈቃደኞች፤   ህዝባዊ የመስመር ላይ የድጋፍ ፊርማን ይተረጉማሉ፡፡ ፊርማው በመጪው ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ህብረት (አይቲዩ) ጉባኤ ላይ የመስመር ላይ ሰብዓዊ መብት ጥበቃን የሚደግፍና የአይቲዩ...