ከፍተኛ ስርጭት ያገኘው አንድ ጥቁር ሰው በሴት ፍቅረኛው ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ገብቶ “ታጥቦ” ሲወጣ መልከመልካም፣ ነጭ ቆዳ ያለው ቻይናዊ ሰው የሆነ፣ የማጠቢያ ኬሚካል ማስታወቂያ ከቻይና ውጪ ያሉ ሰዎችን በዘረኛነቱ አስቆጥቶ ሰንብቷል፡፡
የማጠቢያ ኬሚካል አምራቹ ኩባንያ፣ ኪያኦቢ ወዲያው ይቅርታ ጠይቆ ማስታወቂያውን አንስቷል፡፡ ሆኖም የይቅርታ ንግግሩ የውጭ ተቺዎን ከሚገባው በላይ በማካበድ ወቅሷል፡፡ ብዙ የቻይና ዜጎችም በኢንተርኔት ላይ ማስታወቂያው የባሕል ልዩነትን ከማሳየቱ በቀር ምንም ዘረኝነት የለውም፤ የቻይና ሕዝብ በጥቁር ሕዝብ ላይ ዘረኛ ሊሆን አይችልም በማለት ኩባንያውን ደግፈውታል፡፡
在国外,可能是会被认为种族歧视,但是在中国,可能就不是这样,只是一则广告而已!这是每个国家的文化不同,所以会有不同的看法!
ከቻይና ውጪ፣ ሰዎች ይህን ማስታወቂያ እንደዘረኝነት ሊያዩት ይችላሉ፡፡ በቻይና ግን የተለየ ነው፡፡ በቃ ማስታወቂያ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም አገር የራሱ ባሕል አለው፤ አመለካከቶችም ይለያያሉ፡፡
可以再拍一个浑身毛茸茸的白人塞进洗衣机洗一洗。告诉美国人,我们不仅歧视黑人,也歧视白人,你满意了吧。
ኩባንያው ፀጉራም ነጭ ሰውዬ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ሲገባ መሥራት ይችላል፡፡ አሜሪካኖቹን ነጭ እና ጥቁሮችን እንደምናገል ንገሯቸው፡፡ ይህ ያረካችኋል?
没觉得有什么问题,请不要把种族歧视政治正确强行引进中国
ማስታወቂያው ችግር የለበትም፤ የፖለቲካ ትክክለኝነትን ጉዳይ በዘረኝነት ሥም እባካችሁ ወደቻይና አታምጡብን፡፡
黄种人没有搞过黑人奴隶制,没搞过强迫黑人奴隶劳动,没搞过大规模贩卖黑奴,也没有三K党,更没有种族隔离制度。所以,冤有头债有主,白人歧视黑人才是种族主义,黄人歧视黑人不过是文化差异。 白人才是天然种族主义者。
ቢጫ ቆዳ ያላቸው ሕዝቦች፣ ጥቁር ቆዳ ያላቸውን ሕዝቦች ቅኝ ገዝተው አያውቁም፤ ለጉልበት ሥራ አላስገደዷቸውም፤ በክፍት ገበያ አልሸጧቸውም፡፡ ኩ ክላክስ ክላን ወይም የዘር ክፍፍል እኛ ጋር የለም፡፡ እውነተኛ ጠላታችሁን እዛው ፈልጉ፡፡ ዘረኝነት ነጮች ጥቁሮችን ሲያገሏቸው ብቻ ነው፡፡ ቢጫ ቆዳ ያላቸው ጥቁር ቆዳ ያላቸውን ካገለሉ የባሕል ልዩነት ነው፡፡ ነጮች ናቸው ዘረኛ ሆነው የሚወለዱት፡፡
የፕሬስ አቤቱታውን ጎርፍ ለማስቆም፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሕዝብ ግንኙነት ሁዋ ቹኒንግ ማስታወቂያ ጠቅላላ ሁኔታውን የሚገልጽ ሳይሆን የተለየ ክስተት እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረው፤ ቻይኖች “ከአፍሪካ አገሮች ጋር መልካም ወንድሞች” ናቸው ብለዋል፡፡
ምንም እንኳን ማስታወቂያው ብቸኛ አጋጣሚ ቢሆንም ቻይኖች ለአፍሪካውያን “መልካም ወንድሞች” ናቸው በሚል ዘረኝነቱን እንዳለ መካዱ ግን ትክክል አይደለም በማለት ሁለት የአንትሮፖሎጂ (የባሕል ጥናት) ተማሪዎች ተሟግተዋል፡፡
ነገር ግን፣ ይህ ዓይነቱ ዘረኝነት ከመለመዱ የተነሳ ቻይኖች ማስተዋል እንዳይችሉ ሆነዋል፡፡
የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ፣ እ.ኤ.አ. በ1949 ሥልጣን ከያዘ በኋላ “ከተጨቆኑ የአፍሪካ ወንድሞቻቸው” ጋር በምዕራባውያን ኢምፔሪያሊዝም ላይ ለመተባበር ሞክረዋል፡፡ የቻይና ባለሥልጣናት “ወንድሞች” የሚለውን ቃል፣ አሁን “ለአንድ ወገብ አንድ ቀበቶ” የሚሉትን ተክተው የቻይናን ንግድ ከዩሮዢያ እና ምሥራቅ አፍሪካ ጋር ለማስተሳሰር ይጠቀሙበት ነበር፡፡
ይሁን እንጂ፣ ቻይና በኢኮኖሚ ማደግ ስትጀምር እና ገበያዋን ከፍታ ብሔርተኝነቷን ስታዘምን በጥቁሮች ላይ ያለው ዘረኝነትም ጨምሯል በማለት ተማሪዎቹ ጽፈዋል፡፡ በ1980ቹ፣ በቻይና ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ጥቁሮች ላይ ያነጣጠሩ በርካታ ገጠመኞች እንደነበሩ ገልጸዋል:
80年代的中國在今天令許多人心生嚮往,然而那個時代也有它被遺忘的黑暗一面。其中一例,便是驅趕非洲學生的校園運動。對「劣等民族」的偏見,加上對非洲人獲得留學生優惠的不滿,對愛滋病傳播的恐懼,和保護本民族「純正性」的呼籲一起,激起了綿延80年代的中非學生衝突。
1979年7月3日,上海的一名馬里學生被中國學生毆打,並因為膚色較淺而被後者一邊喊着「太淺了」,一邊不斷潑墨水。雙方在宿舍門口爆發鬥毆,導致50名外國學生和24名中國學生受傷。在此之後,一百多名非洲學生聚集到天安門廣場遊行,呼籲停止送非洲留學生到中國,因為中國「反非洲傾向非常嚴重」。而中國政府僅承諾加強上海學生的「國際主義」教育,否認事件與種族歧視相關。
1979年後,中非學生之間的衝突不但沒有停止,反而繼續擴大。1979到1989年的10年間,南京、合肥和杭州等地,陸續有反黑人事件發生,每次均有數百人涉及。如1988年12月29日,華中科技大學的300名中國學生向留學生宿舍扔石頭,並砸傷了一名斯里蘭卡學生。中國學生給校方寫信,要求驅逐非洲學生。因為「非洲學生和中國女生的交往破壞了中國社會的穩定」。類似這些事件,往往以女性和非洲黑人交往為導火索。與非洲學生交往的中國女生,也被污名化成了「漢奸」和「妓女」。
ብዙ ሰዎች የ1980ዎችን መልካም ገጽታ ብቻ ያስታውሱና መጥፎውን ይዘነጋሉ፡፡ አንዱ ምሳሌ ጥቁር ተማሪዎች ላይ የተደረጉ የካምፓስ ዘመቻዎች ናቸው፡፡ በ1980ዎቹ በቻይኖች እና በአፍሪካውያን ተማሪዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት መነሾው አፍሪካውያን ተማሪዎች በቻይኖቹ “ንዑስ ዘር” የሚለው እና የኤችአይቪ ስርጭትን ለመግታት የቻይናን ዘር ንፅሕና ለመጠበቅ የሚደረግ ፍረጃ ስለነበር ነው፡፡
በጁላይ 3፣ 1979 አንድ የማሊ ተማሪ በቻይና ተማሪዎች ቡድን ድብደባ ደርሶበታል፡፡ ቻይናውያን ተማሪዎቹ ቆዳው ስስ ነው ብለው ላዩ ላይ ቀለም አፍስሰውበታል፡፡ ግጭቱ ከተማሪዎቹ ሆስቴል ውጭ ሆኖ በቡድን ፀብ 50 የውጭ ተማሪዎች እና 24 ቻይኖች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በኋላ ላይ፣ አፍሪካውያን ተማሪዎቹ ወደታይናንሜን አደባባይ ሠልፍ በማድረግ ቻይናውያን ፀረ-አፍሪካዊነት ስሜት ስላላቸው የአፍሪካ መንግሥታት ተማሪዎችን ወደቻይና መላክ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡ የቻይና ባለሥልጣናት የሻንጋይ ተማሪዎች ትምህርት “ዓለማቀፋዊነትን” እንደሚያሻሽሉ ቃል በመግባት ክስተቱ የዘረኝነት መሆኑን ክደዋል፡፡
እ.አ.አ. ከ1979 በኋላ በቻናውያን እና አፍሪካውያን መካከል ያለው ግጭት አልቆመም፡፡ ከዚያ ጀምሮ እስከ እ.ኤ.አ. 1989 ድረስ፣ እንደ ናንጂንግ፣ ሄፌይ፣ እና ሃንዦው ባሉት ከተሞች ውስጥ ተመሳሳይ ነገር ተከስቷል፡፡ በየገዚው በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በዚህ ግጭት ውስጥ ይሳተፋሉ፡፡ ለምሳሌ በዲሴምበር 29፣ 1988 ዉሀን ውስጥ ያሉ 300 ቻይናውያን የሁዦንግ ዩንቨርስቲ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተማሪዎች በውጭ አገር ተማሪዎች ላይ ድንጋይ በመወርወር ከስሪላንካ የመጣ ተማሪ ጎድተዋል፡፡ ብሎም፣ ተማሪዎቹ ለዩንቨርስቲው በጻፉት ደብዳቤ አፍሪካዊ ተማሪዎች እንዲባረሩ ሲጠይቁ “በአፍሪካውያን እና በቻይናውያን ሴቶች መካከል ያለው የፍቅር ግንኙነት የቻይናን ኅብረተሰብ ቀውስ ውስጥ እየከተተው እንደሆነ” በምክንያት ገልጸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ነገሮች ብዙ ጊዜ የሚቀሰቀሱት በቻይና ሴቶች እና በአፍሪካ ወንዶች መካከል የፍቅር ግንኙነት ሲፈጠር ነው፡፡ ሴቶቹ “የሀን ቻይና ጠላቶች” ወይም “ሸርሙጦች” እየተባሉ ይሰደባሉ፡፡
የቻይና ባለሥልጣናት ከ1989ኙ የታይናንሜን አደባባይ የዴሞክራሲ ወዳድ ተማሪዎች ንቅናቄ በኋላ ቁጥጥሩን ስላጠበቁት፣ በየዩንቨርስቲዎቹ የሚደረገው የዘረኝነት ዘመቻም በዚያው ቆመ፡፡ ነገር ግን የአደባባይ ዘረኝነቱን ማፈኑ፣ ዘረኝነትን ከቻይና አላጠፋውም፡፡ ደራሲዎቹ እንደሚከራከሩት፣
然而枱面上種族歧視的消失,讓公開的反思變得更不可見。中國的種族觀念,不但沒有得到指出和討論,反而變本加厲地發展成了對「劣等民族」的鄙夷。
በአደባባይ የማግለሉ ነገር መቆሙ ቻይናውያን በዘር ላይ የተመሠረቱ ፍረጃዎች ላይ ክርክር እና ውይይት ሚያደርጉባቸው ሕዝባዊ ዕድሎችን አቋርጧል፡፡ እነዚህ “ንዑስ” የሚሉት ዘር ላይ የተመሠረቱ ፍረጃዎች ተለመዱ እና ቀጠሉ፡፡
በተጨማሪም ኢንተርኔት ይህንን ዘረኝነትን እንደኖርማል የመቁጠሩን ነገር አባብሶታል:
中國網民們,則激進地傳播反黑文章,把子虛烏有的黑人移民視為中國21世紀最大的危險——甚至上升到「亡國滅種」。在「小粉紅」發源的「晉江論壇網友交流區」裏,年輕女性為主的網民經常討論廣州「黑人圍城」的主題,熱度也不下政治討論。
中國民族主義也和種族階序的想象結合在一起。著名的民族主義動漫《那年那兔那些事》,就在第二季中用動物形象描述了非洲人——好吃懶做愚蠢不堪的河馬。中國援非的歷史也被簡化成了「第一世界不和我們玩」的無奈。而性和帶着生殖意味的種族想像,也仍然是排斥黑人的核心焦點。在百度貼吧,微信朋友圈裏傳播的反黑言論,乃至今天這則廣告中,黑人都像是目的不純,只想睡中國女人的渣滓;與黑人交往的中國女性被污名化為「重口味」或者「窮,沒受過教育」。
ቻይናውያን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ፀረ-ጥቁር አስተያየታቸውን በፅንፈኝነት ያንፀባርቃሉ፡፡ በ21ኛው ክፍለዘመን የአፍሪካውያን ወደቻይና መፍለስ ትልቁ ፈተናቸው እንደሆነ እና “ለቻይና ዘር እና ለአገሪቱ የሕይወትና የሞት” ጉዳይ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ዢንያን የተባለው እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ደጋፊዎች የኢንተርኔት መድረክ ላይ ጉዋንግዡ (የተባለው እና ብዙ አፍሪካውያን የሚገኙበት) ከተማ በጥቁር ሰዎች “መያዙ” በወጣት ሴት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የሞቀ ውይይት ከሚደረግባቸው ርዕሰነገሮች ዋነኛው ነው፡፡
የቻይና ብሔርተኝነት የተገነባው በዘር ክፍፍል ነው፡፡ ብሔራዊው ካርቱን ይር ሄር አፌር አፍሪካውያንን ለሁለት ተከታታይ ጊዜያት የመሰላቸው እንደ ሰነፍ እና ደደብ በሚቆጠረው እንስሳ ጉማሬ ነው፡፡ ለአፍሪካ የሚሰጠው የቻይና ዕርዳታም ቢሆን “አንደኛው ዓለም ከኛ ጋር ለመጫወት ስላልፈቀደ” የተወሰደ የመጨረሻ እርምጃ ነው፡፡ ወሲብ እና መዋለድ ነው የፀረ-ጥቁር ስሜቱ መገለጫ፡፡ ባይዱ በተባለው ማኅበራዊ ሚዲያ የውይይት ክበቦች ውስጥ ጥቁሮች የሚቆጠሩት ደረጃቸው የወረዱ ከቻይና ሴቶች ጋር ወሲብ ከመፈፀም በስተቀር ሌላ ዓላማ እንደሌላቸው ፍጡሮች ነው፡፡ ጥቁር ወንዶችን የሚያወጡ ወንዶች “የማይሆን ምርጫ” ወይም “ድሃ እና ያልተማሩ” እንደሆኑ ነው የሚቆጠሩት፡፡
ከ1980ዎቹ ጀምሮ ያቆጠቆጠው የቻይና ሕዝባዊ ባሕልም የቻይኖች “ቢጫነት” ለአንፃራዊው የሳይንስ እና ዘመነኝነት ልህቀታቸው አስተዋፅዖ እንዳደረገ ነው የሚያምነው፡፡ “ሪቨር ኢሌጂ” የተባለው የቻይና ዘጋቢ ፊልም ለምሳሌ ቢጫው ወንዝ የቻይናዎችን የረጋ እና ዝግ ሥልጣኔ፣ ሰማያዊው ወንዝ ደግሞ የምዕራባውያንን “ዴሞክራሲያዊ እና ክፍት” ሥልጣኔ ወክሏል በማለት ደራሲዎቹ ጽፈዋል፡፡
እነዚህ ሁሉ ለዛሬው በቻይና በጥቁሮች ላይ ለሚደርሰው ዘረኝነት የራሳቸውን ድርሻ ተጫውተዋል ይላሉ:
而到了「走向中華民族偉大復興」的今天,之前還是階級兄弟的亞非拉同胞已經被拋諸腦後,黃種人略差於白種人的自我歧視也被放棄,中國人開始要求和白人平起平坐。這一切如兩個世紀以前的白人們一樣,依然要騎在黑人的頭上來完成。
ዛሬ፣ አገሪቱ “የቻይና ታላቁ ብሔራዊ ዳግም ማንሰራራት”ን እየተቃረበች ባለችበት ጊዜ፣ የአፍሪካውያን ወንድሞች ታሪክ አልፎ፣ ቢጫ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ከነጭ ቆዳ ካላቸው ሰዎች አንፃር የሚሰማቸው የበታችነት ስሜት ተረስቷል፡፡ ቻይኖች ከነጮች ዕኩል ሕዝቦች መሆን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ልክ እንደነጮች ሁሉ፣ ከፍ ያለ ደረጃን መጎናፀፍ የሚፈልጉት ጥቁሮች ላይ በመቆም ነው፡፡