ታሪኮች ስለ እንግሊዝኛ
የኦሮሞ ሙዚቀኞችን የማፈን አሳፋሪ ገመና
የመንግሥት ሳንሱርን ለመስበር አማራጭ ይዞ የመጣውን ኢንተርኔት በመጠቀም፣ በዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ዩቱዩብ እና ፌስቡክ ላይ በተደረገ ቆጠራ ብቻ ከ300 በላይ ፖለቲካ ነክ ዘፈኖች ከ2006 ወዲህ የተለቀቁ መሆኑ የፖለቲካ ዘፈኖች መነሳሳት አለ ብሎ ለማለት ያስችላል፡፡
ኢትዮጵያ ‹ታይቶ ከማይታወቀው› የኢኮኖሚ ዕድገቷ በተፃራሪ ረኀብ ተጋርጦባታል
"ከኢትዮጵያ ውስጥ በተገኘ መረጃ መሠረት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች “ረኀብ፣ ችጋር ወይም ሞት” የሚሉ ቃላቶችን በምግብ ጥያቄዎቻቸው ውስጥ እንዳያካትቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡"
ተማሪዎች የዋና ከተማዋን የመስፋፋት ዕቅድ ለምን ይቃወማሉ?
"በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል፣ ኑሯቸውን የሚያጠፋ እና ማንነታቸውን የሚያንኳስሰውን ይህንን ዕቅድ ይዞ መቀጠል በጣም የሚያሳዝን ነው የሚሆነው፡፡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ተማሪዎች ለገበሬዎቹ ጥቅም ሲሉ ነው ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ያስቀመጡት"
ኢትዮጵያውያኖች የብሔራዊ ቴሌቪዥናቸውን ‹ውሸቶች› በኤፕሪል ዘ ፉል ቀን አፌዙበት
ኢትዮጵያውያኖች የማሞኛ (አፕሪል ዘ ፉል) ቀንን በትዊተር ላይ በመንግሥት በሚተዳደረው የአገር ውስጥ ብቸኛ የቴሌቭዥን ጣቢያቸው (ኢቴቪ) ባስመሰሏቸው የውሸት አርዕስተ ዜኛዎች እንደንፁህ የወንዝ ወራጅ ውሃ በሚንኮለኮል ትዊቶች አጥለቅልቀውት እየተሳለቁ ቀኑን አክብረዋል፡፡
ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ በእስር 1000 ቀን ሞላት
መጋቢት 7/2006 ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የታሰረችበት 1000ኛ ቀን ነው፡፡ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ተብላ የአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ከተበየነባት ጥር 2004 ጀምሮ በእስር ላይ ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያውያን #SomeoneTellSaudiArabia በሚል ስደተኞች ላይ የደረሰውን እርምጃ ተቃወሙ
ጥቅምት 25፣ 2005 ሳኡዲ አረቢያ በሕገወጥ ስደተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች፡፡ ሳኡዲአረቢያ 7 ሚሊዮን የሚሆኑ የውጭ ዜጋ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን አስጠልላለች ተብሎ ይታመናል፡፡
ቪዲዮ፤ “ኖ ዉማን፣ ኖ ድራይቭ” ሳኡዲ አረቢያን አደመቃት
ዛሬ፣ ጥቅምት 16፣ 2006 ለሳኡዲ አራማጆች በኪንግደሙ ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የተጣለባቸው ማዕቀብ ላይ ለማመጽ የመረጡት ቀን ነበር። የማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች በአገሪቷ ውስጥ መኪና እየነዱ ስለታዩት ሴቶች ቁጥር መጨመር በስፋት እያወሩ ሳሉ፣ ተወዳጁ፣ የቦብ ማርሌይ “ኖ ዉማን፣ ኖ ክራይ” የተሰኘ ዜማ ሴቶችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸውን ለመንፈግ የወጣ የወግ አጥባቂ ስርዓተ ፆታ...
ጅቡቲ፤ ‘ዲሞክራሲያዊ’ ምርጫን ተከትሎ የመጣው እስር
ትንሽ አገር ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ እጅግ በጣም ስትራቴጂክ አገር በሆነችው ጅቡቲ የየካቲት 15፣ 2005 አገር አቀፋዊ ምርጫን ተከትሎ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ፡፡ በምርጫው ‹የሕዝቦች አንድነት ለዕድገት› (People's Rally for Progress) የተሰኛው ፓርቲ በድጋሚ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡመር ጉሌህ ጅቡቲን እ.ኤ.አ ከ1999 ጀምሮ የመሩ ሲሆን በምርጫውም የ80 በመቶ መራጮች ድምፅ ቢያገኙም በከፍተኛ ሁኔታ በማጭበርበር ተጠርጥረዋል፡፡ እስሩ የመጣውም በዚሁ ማጭበርበር ጉዳይ [fr] ላይ ዜጎች ሰልፍ በመውጣታቸው ነው፡፡ እንደየጅቡቲ ሰብኣዊ መብት ሊግ እና የዓለምአቀፍ ሰብኣዊ መብት ፌደሬሽን ከሆነ 90 ሰዎች በአሰቃቂነቱ በሚታወቀው ጋቦዴ ማዕከላዊ እስር ቤት ታጉረዋል፡፡ እስሩ ይህ ጽሑፍ እስከተጻፈበት ሚያዚያ 20005 ድረስ ቀጥሏል፡፡
በኬኒያ ቴሌቭዥን የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የሃይማኖት ተቋማትን አስቆጣ
በቅርቡ ለህዝብ አገልግሎት ይውል ዘንድ HIV እና ተዛማጅ በሽታዎችን ለመከላከል የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን ማስቆጣቱን ተከትሎ በመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፍ ታገዷል፡፡ ማስታቂያው አንዲት ባለትዳር ሴት ባለቤቷ ከትዳር ውጪ በሚያደርጋቸው የግብረስጋ ግንኙነቶች ኮንዶም እንዲጠቀም ምክር ስትሰጠው የሚያሳይ ሲሆን ማስታወቂያው የኬኒያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዩኤስ ኤድ እና ዩኬ ኤድ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለት የተዘጋጀ ነው፡፡
የ2013ቱን የአፍሪካ አገራት ዋንጫ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ባንዲራ ውልብልቢት እያደመቁት ነው
በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከባለፈው ዓመት የ2012 የአፍሪካ አገራት ዋንጫ ሻምፒዮን ጋር በኔልስፕሩት፣ ደቡብአፍሪካ ያደረገውን ከባድ ግጥሚያ በድምቀት እያከበሩ ነው፡፡ ከኢትዮጵያውያኑ ውብ አጨዋወት እና ከረዥም ጊዜ መጥፋት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ከታየው ድንቅ የተጫዋቾች ችሎታ ባሻገር፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከኳሱ ጎንለጎን ማዕከላዊ የውይይት አጀንዳ ለመሆን በቅቶ ነበር፡፡ በስታዲየሙ ጨዋታውን ለመመልከት የገቡት ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ጽሑፎችን እና ባንዲራዎችን ሲያውለበልቡ ታይተዋል፡፡