ኢትዮጵያውያኖች የማሞኛ (አፕሪል ዘ ፉል) ቀንን በትዊተር ላይ በመንግሥት በሚተዳደረው የአገር ውስጥ ብቸኛ የቴሌቭዥን ጣቢያቸው (ኢቴቪ) ባስመሰሏቸው የውሸት አርዕስተ ዜኛዎች እንደንፁህ የወንዝ ወራጅ ውሃ በሚንኮለኮል ትዊቶች አጥለቅልቀውት እየተሳለቁ ቀኑን አክብረዋል፡፡ #ETvDay የሚል ሃሽ ታግ በመጠቀም የመረብዜጎች ‹365 ቀን ውሸቶችን የሚናገረውን› የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ወቅሰዋል፡፡
ከታች በምትመለከቱት ምስል ነው ሁሉም ነገር የተጀመረው፡-
ኢቴቪ የተባበሩት መንግሥታት ቀናልት ዝርዝር ውስጥ መግባት ቻለ:: ኢቴቭን በራሱ ስታይል:: ስዕሉ በ@jomanex pic.twitter.com/8hMK76uWS8
— BefeQadu Z Hailu™ (@befeqe) March 31, 2014
Jomanex እንዲህ አለ፡-
አፕሪል ዘፉል የፈረንጅ ነው ኢቲቪ ግን <<የኛ>> ነው፡፡ ከስተማይዜሽን #EtvDay
— Jomanex Kassaye (@jomanex) April 1, 2014
Soli የሚቀጥለው ዓመት (በ2007) የሚካሄው ብሔራዊ ምርጫ ላይ እንዲህ ቀለደች፡-
መጪው የ2015 ብሔራዊ ምርጫ ፍታዊ፣ ነፃ እና ዲሞክራሲያዊ ነው፡፡ #ETVday. #Ethiopia
— Soli ሶሊ (@Soli_GM) April 1, 2014
በ1997 የተደረገው የኢትዮጵያ ምርጫ በአወዛጋቢ ሁኔታ የጎዳና ላይ ነውጦች ተከስተውበት ነበር የተጠናቀቀው፡፡ 193 ሰዎች በመንግሥት ታጣቂዎች ሲገደሉ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ለእስር ተዳርገው ነበር፡፡ ከአምስት ዓመት በኋላ እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገው ምርጫ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በዝረራ አሸንፏል፣ ከፓርላማ 99.6 መቀመጫዎችን በመያዝ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን ውጤት ውድቅ ያደረጉ ሲሆን አለም አቀፍ ታዛቢዎችም ምርጫው ዓለም አቀፋዊ መስፈርቶች በታች እንደነበር መስክረዋል፡፡
ይህ ሁሉ ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግስታት እ.ኤ.አ በ2000 ካስቀመጧቸው የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች መካከል ኢትዮጵያ አንዱን ከግቡ ዓመት ቀድማ በክብረወሰን ታሳካለች፡-
“ኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ከምዕተ አመቱ ግብ ቀድማ እንደምታሳካ አንዳንድ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለፁ” #ETvDay (Photo Arsi/Ethiopia – 2013) pic.twitter.com/GZ7iF9JvFx
— Zelalem Kibret (@zelalemkibret) April 1, 2014
#Etvday በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ከ20 ቀናት በላይ የመጠጥ ውሃ ማግኘት ባይችሉም፥ ልማታዊው መንግስታችን ያለ መጠጥ ውሃ እንዴት መኖር እንደሚቻል አስቀድሞ ስልጠና ስለሰጠን ተጎጂ አልሆንም ሲሉ ገለፁ።
— Tewodros Belay (@tewodros_belay) April 1, 2014
የዩክሬይን የዚያ አካባቢ ነዋሪዎች ወደራሽያ ለመቀጠል በትልቅ ድምፅ በወሰኑበት የክራይሜያን ሪፈረንደም ጉዳይ ደግሞ፡-
ሩሲያ ክሬሚያን የራሰዋ ግዛት ማድረግ ፤ ኢትዮጵያን ከእድገትና ትራንስፎርሜሽን እንደማያደናቅፋት አንዳንድ የአዳማ ነዎሪዎች ተናገሩ #ETvDay
— Yassin Nuru (@yassinahmed1) April 1, 2014
ማሕሌት ዜናን በሁለት ከፈለችው፡-
አንደኛው ዜና ነው፤ ሁለተኛው የኢቴቪ ዜና ነው፡፡ #ETvDay
— Mahlet (@Mahlet_S) April 1, 2014
በፍቃዱም አከለበት:-
የዓለም ሕዝብ በሁለት ይከፈላል፤ ኢቴቪ በየቀኑ የሚያይ እና እግዜር ያተረፈው። #ETvDay
— BefeQadu Z Hailu™ (@befeqe) April 1, 2014
‹የ13 ወር ፀጋ› የሚለውን የቀድሞ የኢትዮጵያ ቱሪዝም መፈክር በመጠቀም ሳለህ እንዲህ አለ፡-
የ13 ወር ፀጋ እና 13 ወር ውሸት የመንግሥት ውሸት በመንግሥት በሚተዳደር የቴሌቭዥን ጣቢያ #ETvDay = የማሞኛ ቀን @BBCAfrica @AJStream
— saleh (@2zworld) April 1, 2014
ኢቴቪ በዓመት ስንት ቀን ነው ያለው?፡-
ዛሬ የኢቴቪ ቀን ነው እያሉ ለሚያከብሩ ተሟጋቾች ኢቴቪ በሰጠው ምላሽ በዓመት ውስጥ የኢቴቪ ቀን ያልሆነው አፕሪል ዘ ፉል ብቻ እንደሆነ ገለፀ፡፡ #April1
— Bon Bon (@BonayaBonso) April 1, 2014
ኦሮሞ ኔትዎርክ እንዲህ ተመኘ፡-
ዛሬ ከኢቴቪ ጋዜጠኞች የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ እሩምታ እጠብቃለሁ፡፡ #ETvDay #13monthsofEtvlies
— Oromo Network (@Oromo_NT) April 1, 2014
የተቀሩትን የ#ETvDay ትዊቶች እዚህ እያነበባችሁ እንድትዝናኑ ተጋብዛችኋል፡፡