ጥቅምት 25፣ 2005 ሳኡዲ አረቢያ በሕገወጥ ስደተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች፡፡ ሳኡዲአረቢያ 7 ሚሊዮን የሚሆኑ የውጭ ዜጋ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን አስጠልላለች ተብሎ ይታመናል፡፡ የሳኡዲ አረቢያ መንግሥት ለሕገወጥ ስደተኞች የዘጠኝ ወር የእፎይታ (amnesty) ጊዜ በሚያዝያ ወር 2005 ሕጋዊ ዕውቅና እንዲያገኙ አሊያም አገሪቷን እንዲለቁ ሰጥቶ ነበር፡፡
ከሰሃራ በታች የምትገኘዋ የኢትዮጵያ ስደተኞች በዚህ የመንግሥት እርምጃ በፅኑ ከተቸገሩት ውስጥ ይመደባሉ፣ ይህም ዓመፅ እና ብጥብጥ አስከትሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በሳኡዲአረቢያ በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩትን ሰዎች በሳኡዲ ፖሊሶች አንድ ኢትዮጵያዊ መገደሉ ከተነገረ በኋላ ወደአገራቸው መመለስ ጀምሯል፡፡
በተለያዩ የዜና እና የማኅበራዊ አውታሮች እንደተገለጸው ከሆነ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም የሳኡዲ አረቢያን ሕገወጥ ስደተኞችን የማስወጣት መብት ቢያምኑም የኃይል አጠቃቀማቸው እና ሴቶች ላይ የደረሰው የመድፈር ድርጊትን አውግዘዋል፡፡
ከታች የሚታየው ቪዲዮ በአምሃሪክትዩብ የተለጠፈ ሲሆን ከሳኡዲ አረቢያ የሕገወጥ ስደተኞችን መመለስ ያሳያል፡-
MoveOn.org የተባለ ድረገጽ ላይ ፊርማ የማሰባሰብ ሥራ የተጀመረ ሲሆን ለተባበሩት መንግሥታት እና እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ላሉ የሰብኣዊ መብቶች ድርጅቶች በሳኡዲ አረቢያ ስለኢትዮጵያውያን ስደተኞች አያያዝ ለማሳወቅ ታቅዷል፡፡
ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በበይነመረብ #SomeoneTellSaudiArabia የሚል ኃይለ ቃል በመጠቀም በሳኡዲ አረቢያ ያለውን የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አያያዝ አውግዘዋል፡፡
ማሕሌት (@Mahlet_S) ስደተኞች ወንጀለኞች ሳይሆኑ ሥራ ፈላጊዎች መሆናቸውን አስታውሳለች፡-
#SomeoneTellSaudiArabia ስደተኞች አገራቸው የገቡት ሥራ ፍለጋ እና ለእንጀራ እንጂ ወንጀለኛ አለመሆናቸውን ለሳኡዲአረቢያ ሊነገራት ይገባል፡፡
— Mahlet (@Mahlet_S) November 11, 2013
አዲስ ስታንዳርደ (@addisstandard) የተሰኘ ወርሓዊ የኢትዮጵያ መጽሔት ደግሞ፡-
#SomeoneTellSaudiArabia ሰው መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ከሃይማኖታዊ ቀናተኛነት ይልቅ ሰብኣዊ ሞራል ይጠይቃል፡፡
— Addis Standard (@addisstandard) November 12, 2013
አንዳንዶች ደግሞ በኢትዮጵያ እና ኢስላም መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት አስታውሰዋል፡፡ ሐፍሳ መሐመድ (@hafsamohamed1) የሚከተለውን ጠቁሟል፡-
#SomeoneTellSaudiArabia ነብዩ መሐመድ (ሰዐወ)ተከታዮቻቸው ኢትዮጵያን እንዳያስከፉ ተናግረዋል፡፡ እነርሱ ግን ዘነጉት፡፡ #Ethiopia. pic.twitter.com/XxZocICmPr
— Hafsa Mohamed (@hafsamohamed1) November 12, 2013
ካሊ (@KaliDaisyy) የጻፈው:-
#SomeoneTellSaudiArabia ኢትዮጵያ ከመካ ለመጡት እና በቁራይሽ ጎሳ ለተከሰሱት የሙስሊም ስደተኞች እጆቿን ዘርግታ ነበር፤ እና አሁን እነርሱ ይገድሉናል?
— Kali (@KaliDaisyy) November 12, 2013
የሥነ ልቦና ባለሙያው አንቶኒዮ ሙላቱ (@AntonZfirst) በነብዩ መሐመድ ስለኢትዮጵያ የተሰጠውን ምክር ማጣቀስ መርጧል፡-
1/ #SomeonetellSaudiArabia ነብዩ መሐመድ እንዳሉት ‹‹ከፈለጋችሁ ወደኢትዮጵያ ሂዱ፡፡ እዚያ ማንንም የማይጎዳ ንጉሥ አለ፡፡››
— Antonio Mulatu (@AntonZfirst) November 12, 2013
በኢትዮጵያ እና በሙስሊሞች መካከል ያለው ግንኙነት የሚጀምረው ኢትዮጵያ በመካ ገዢዎች ተሰደው ለመጡት ሙስሊሞች ሠላማዊ መሸሸጊያ ስትሰጥ ነው፡፡ ቢላል ኢብን አል ሐበሽ ከቀደምት የመሐመድ ተከታዮች አንዱ እና የመጀመሪያ ሙኧዚን (የአዛን ዜማ አሰሚ) ሲሆን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
በኢስላም አራተኛ ቅዱስ ከተማ የምትባለዋ ሐረር ከተማ በኢትዮጵያ ነው የምትገኘው፤ 82 መስኪዶች፣ ሦስቱ ከ10ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ያሉ ሲሆን 102 መስገጃዎችም አሏት፡፡
ኢትዮጵያ ከዚህም በተጨማሪ በእስልምና ታሪክ የመጀመሪያው ሒጅራ (የሙስሊሞች ስደት ከክስ ሽሽት) የተካሄደባት አገር ናት፡፡
በሌላ በኩል አኑፍ (@anoofesh) ከሪያድ፣ ሳኡዲ አረቢያ የኢትዮጵያዊ ስደተኞች በሳኡዲ አረቢያ እና የያኔዎቹ የሳኡዲ አረቢያ እና ሙስሊም ስደተኞች በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ልዩነት በተመለከተ ልዩነቱን ተናግሯል፡-
@KaliDaisyy ሙስሊሞች ስደተኞች ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩት በሕገ ወጥ መንገድ አልነበረም 🙂
— anoof (@anoofesh) November 12, 2013
መላክ መኮንን (@melak_m) ያንን በተመለከተ፡-
#SomeoneTellSaudiArabia: ሕገ ወጥ ስደትን መከላከል ይቻላል፤ ነገር ግን በመደብደብ፣ በመግደልና በማሰር አይደለም!
— Melak Mekonen (@melak_m) November 12, 2013
የእንግሊዙ ሪስፔክት ፓርቲ ሊ ጃስፐር (@LeeJasper) ደግሞ የኢትዮጵያውያን ስደተኞቹን ጉዳይ በእስራኤል ይዞታ ካሉት ፍልስጤማውያን ጋር አነጻጽራዋለች፡-
#SomeoneTellSaudiArabia that their racist treatment of #Ethiopians is in many ways just as bad as #Israeli treatment of #Palestinians.
— Lee Jasper (@LeeJasper) November 12, 2013
የجبرتينهو (@iabj) አስተያየት ደግሞ፡-
#SomeoneTellSaudiArabia የውጭ ዜጎች ባርያዎች አይደሉም፣ ድህነትም እንከን አይደለም፡
— جبرتينهو (@iabj) November 12, 2013
በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ የሰብኣዊ መብት ባለሙያው ይሄነው ዋለልኝ (@YeheneWalilegne) የሳኡዲ አረቢያን ለተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብት ቆንስላ እጩ ሆና መቅረብ ተቃውሟል፡-
#SomeoneTellSaudiArabia #UNGA የተባበሩት መንግሥታት የሳኡዲ አረቢያን የሰብኣዊ መብት ቆንስላው ሆና መታጨት ውድቅ ሊያደርጉት ይገባል፡፡ አለዚያ የመንግሥታቱ እና የቆንስላው ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡
— Yehenew Walilegne (@YeheneWalilegne) November 12, 2013
ሕዳር 3፣ 2006 ግን ሳኡዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ራሺያ እና ኩባ የሰብኣዊ መብት ቆንስላውን መቀመጫዎች ማሸነፍ ችለዋል፡
አኑፍም ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ብሏል፡-
@KaliDaisyy ምን ያህል ክፉ እንደሆንን እና እንደተበሳጫችሁብን ልትነግሩን ብቻ ትፈልጋላችሁ፡፡ ብዙዎቻችሁ ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንኳን አታውቁም፡፡ #SomeoneTellSaudiArabia
— anoof (@anoofesh) November 12, 2013