መጋቢት 7/2006 ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የታሰረችበት 1000ኛ ቀን ነው፡፡ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ተብላ የአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ከተበየነባት ጥር 2004 ጀምሮ በእስር ላይ ትገኛለች፡፡

ታሳሪዋ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ:: ፎቶው በፌስቡክ ርዕዮት ዓለሙ እንድትፈታ ከሚወተውት ገጽ የተወሰደ ነው፡፡
ርዕዮት ዓለሙ፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር ስትሆን፣ የUNESCO-ጉሌርሞ ካኖ የዓለም የፕሬስ ነጻነት ሽልማት፣ የሔልማን/ሐሜት ሽልማት፣ እና የዓለም አቀፍ ሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን በድፍረት የጋዜጠኝነት ሽልማት አሸናፊ ናት፡፡
እንደ የጋዜጠኞች ጠባቂ ኮሚቴው (CPJ) መረጃ፣ ርዕዮት ዓለሙን እና እስክንድር ነጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት 11 ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪዎችን ከ2003 ጀምሮ በፀረ-ሽብርተኝነት ስም አስሯል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የሶማሌ ብሔር አማፂ ቡድኖችን ደግፋችኋል በሚል 11 ዓመት እስር የተፈረደባቸው ሁለት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች (አሁን በይቅርታ ተፈትተዋል) ይገኙበታል፡፡
በዚህ ጦማር ላይ፣ ጦማሪ በፍቃዱ ዘ ኃይሉ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችን ፈተና ጽፏል፡-
የእስር ጥቅሙ ጥፋተኞችን ማረም ከሆነ ንባብ እና ትምህርት ይህንን ግብ ለማሳካት መሣሪያዎች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ግን ሁለቱም ተፈቅደዋል፣ ነገር ግን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ለተፈረደባቸው ጋዜጠኞች በቃላሉ የሚፈቀዱ ነገሮች አይደሉም፡፡
እነዚህ እስረኞች መጽሐፍ ማስገባት አይፈቀድላቸውም፡፡ እስክንድር እንደሚለው ‹‹በተለይ ‹ኢትዮጵያ› እና ‹ታሪክ› የሚሉ ሁለት ቃላትን አንድ ላይ የያዙ ቃላት እንዲገቡ አይፈቀድም፡፡›› እነ ርዕዮት፣ እነ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም የታሰሩበት ክፍል ውስጥም እንዲያው ነው፡፡
የአገር ውስጥ ነጻ ጋዜጦች እና መጽሔቶችም እንዲሁ እንዲገቡ አይፈቀድም፡፡ እስክንድር ይህን ሲያብራራልኝ ሌላው ቀርቶ የዜና ቲቪ ቻናሎች እነ ቢቢሲ እና አልጄዚራ እሱ እና ሌሎችም የታሰሩበት ዞን ውስጥ አይፈቀዱም፡፡
ርዕዮት ዓለሙ፣ ከእስርቤቱ አለቆች ጋር ባደረገችው ብርቱ ትግል እና ሚዲያዎች ጉዳዩን ካወሩበት በኋላ የርቀት ትምህርት እንድትማር ተፈቅዶላታል፡፡ ነገር ግን ከኮሌጇ ቀጥታ ከሚላኩላት መጽሐፎች በቀር ማጠናከሪያ መጽሐፍት እንዲገባላት አልተፈቀደላትም፡፡
የትዊተር ተጠቃሚዎች #ReeyotAlemu የሚለውን ሀሽታግ በመጠቀም ለታሰረችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል፡፡ ከታች ጥቂቶቹን ትዊቶች እንመልከት፡-
ዓለም ስለርሷ ይጨነቃል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ብዙ ዘመቻ ማየት እፈልጋለሁ፡፡! MT”@LisaMisol: #Ethiopiaዊቷ ጋዜጠኛ #ርዕዮት ዓለሙ በእስር 1000ኛ ቀኗ፡፡
— vineetkhare (@vineetkhare) March 16, 2014
#የኢሕአዴግ መንግሥት ድክመቱ እና ድንጉጥነቱ እንደርዕዮት ዓለሙ ባሉ ጋዜጠኞች ይጋለጣል፡፡ ትፈታ!
— MediaET (@MediaETHIOPIA) March 16, 2014
#ርዕዮት ዓለሙ: ለምንድን ነው የ3ተኛው ዓለም አምባገነኖች ከሞት ይልቅ ጋዜጠኞችን የሚፈሩት? የድክመት ምልክት ነው፡፡ ሐሳብ እና የሐሳብ ሰዎችን መፍራት!
— MediaET (@MediaETHIOPIA) March 16, 2014
ጋዜጠኛ ዛሬ በእስር ቤት 1000 ቀን ሞላት፡፡ ቤተሰቦቿ እንዳይጎበኟት ታግዳለች፡፡ @SJLambrinidis – ለምንድን ነው እነ @EU_Ashton ዝም የሚሉት?
— Ana Gomes, MEP (@AnaGomesMEP) March 16, 2014
መጋቢት 7 #ርዕዮት ዓለሙ ከታሰረች 1000 ቀን ሞላት፡፡ ይህም የሚያሳየው ኢትዮጵያ የምትመራው በአምባገነንነት፣ በኢፍትሐዊነት እና በጭቆና መሆኑን ነው፡፡ @AnaGomesMEP @amnesty
— EPHREM SHAUL (@eph_sh) March 15, 2014
ጋዜጠኝነት ሽብርተኝነት አይደለም፡፡ ሽልማት አሸናፊዋ #ርዕዮት ዓለሙ ትፈታ፡፡ የሕክምና አገልግሎት እንድታገኝ ይፈቀድላት፡፡ #health #women pic.twitter.com/UyzmniGrb6
— alex (@alexbiruk) March 16, 2014
2 አስተያየቶች
ሰዉ ለሀገሩ ሲል ፈተናዉ ብዙ ነዉ። የታገለ ያሸንፋል በርቱ ሁላችንም አንድ ነን።
በርቱ ታግለን እናሸንፋለን። መብታችን ይረጋገጣል ለጊዜው እኛ ካልደከምን ማን አለ?