ቻይና፤ የሳንሱር ማሽኗ ለፀረ-ጃፓን እንቅስቃሴ ሲባል ቆመ?

በቻይና እና በጃፓን መካከል የዲያኦዩ (ወይም በሌላ ስሙ ሰንካኩ) ደሴት ባለቤትነት ይገባኛል ሲያይል፣ በቻይና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ከ80 በላይ በሚሆኑ ከተሞች መጠነ ሰፊ ፀረ-ጃፓን ሰልፎች ተካሂደዋልል፡፡

አንዳንዶቹ ሰልፎች ወደብጥብጥ ተሸጋግረዋል፤ ነውጠኞቹ በጃፓን ስታይል የተሰሩ ምግብ ቤቶችን፣ የመገበያያ አዳራሾችን እና ሱቆችን አጥቅተዋል፣  እንዲያውም አንዳንዶቹ የጃፓን መኪናዎችን ለማቃጠል ሞክረዋል፡፡ የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎች የቅርብ ክትትል በሚደረግበት እና የመንግስት ደህንነት ኃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ በሚተገበርበት አገር፣ ብዙዎች ይህን ያህል አመጽ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ተገርመዋል፡፡

መስከረም 5/2005 በሻንግሻ ከተማ አማጻዎቹ የጃፓን ሱቆችን እንዴት እንደዘረፉ እና እንዳጠቁ ለመመልከት የሚከተለውን ቪዲዮ ማየት ይቻላል፡፡

የአመጻዎች መቀነባበር

ብዙ የመረብ ዜጎች (netizens) አመጾቹ የተቀነባበሩት QQ በተባሉ ቡድኖች ሲሆን ዌቦ በተባለ እና ማሕበራዊ አውታር ሳይሆን ‹‹የግል›› መረጃ መለዋወጫ ነው፡፡ ሲና ዌቦ ይላል ማርስ [zh]:

Protesters set fire to a car in Xian. Photos from Free more news.

አማጺዎቹ ዢያን ውስጥ መኪና ሲያቃጥሉ፡፡ ፎቶ ከ Free more news.

微博仅是一个相对小众的平台,君不见各种QQ群、QQ空间上病毒式传播的反日宣传,那里的受众才是上街打砸抢的主力军。

ዌቦ ዝነኛ ‹ፕላትፎርም› አይደለም፡፡ የፀረ-ጃፓኑ ፕሮፓጋንዳ በQQ ቡድኖች እና በQQ ማስተላለፊያ አማካይነት እንደቫይረስ ነው የሚሰራጨው፡፡  አማጺዎቹ የተቆሰቆሱት በዚህ ‹ፕላትፎርም› ነው፡፡

ዌቦን በተጨማሪም፣ ተጠቃሚው የሆነ ኢከኖሚስት እንዳረጋገጠው [zh] የመንግስት ሰራተኞችም አመጹን ለማቀጣጠል እየተጠቀሙበት ይገኛል፡-

今天吃饭时一朋友说连续2天看到同学QQ群中发布几日几点到哪里集合反日,用词几乎一字不改。我赶紧问发布的这两个同学在哪儿就职。答曰一个在地税局,另一位在某军工央企驻当地的研究所。

አንድ ጓደኛዬ እና እኔ፣ ሁለታችንም ከተለያዩ ድሮ ኮሌጅ አብረውን ከተማሩ ሰዎች በተመሳሳይ የምግብ ሰዓት በQQ የአመጽ ጥሪ ጥሪ ደረሰን፡፡ መልዕክቱን ስለላኩት ልጆች ስጠይቀው፣ አንዱ ገቢዎች ቢሮ፣ ሌላኛው ደግሞ በሚሊቴሪ ኮርፖሬሽን የምርምር ማዕከል ውስጥ ነው የሚሰሩት

ዚ ቦስተን ሆኖ ወሳኝ ጥያቄ አንስቷል [zh]፡-

我非常疑惑,深圳这么多人上街反日,难道QQ软件里的三个监控外挂都因为爱国而暂停工作了吗?

እንዴት እነዚህ ሁሉ ፀረ-ጃፓን አማጺዎች በሼንዢን ሊኖሩ ቻሉ? በQQ ውስጥ ያለው ሦስት ድርብ የቁጥጥር መረብስ የት ገባ? ለአገር ጥቅም ሲባሉ እነዚህ ሁሉ ገደቦች ተነሱ?

በርግጥም ባለፉት ሁለት ቀናት፣ እንደ “ንቅናቄ/ትግል” (游行) ያሉ ቃላት በማሕበራዊ አውታሮች ‹ፕላትፎርም› ላይ ተፈልገው የማይገኙ ቢሆንም “ፀረ-ጃፓን አመጽ” የሚለው ሐረግ ግን አልታገደም፡፡ እንደ “ዲያኦዩ ደሴት”፣ “ዲያኦዩን ተከላከል”፣ “አመጽ” እና “ግጭት” የመሳሰሉት ቃላት ግን በመፈለጊያው የጦፈ ዝርዝር ላይ ይገኛሉ፡፡

ከታች የሚታየው “ፀረ-ጃፓን አመጽ” (反日示威) ለሚለው ፍለጋ የተገኘው ውጤት ነው፡-

ከትዕይንቱ በስተጀርባ?

ሁ ዚሜ አግራሞት የሚያጭሩ[zh] ተከታታይ ጥያቄዎችን ‹ከትዕይንቱ በስተጀርባ ማን አለ› በማለት ያነሳል፡-

越来越觉得这事不对劲:1,四五十个城市同时起动;2,人数不多,但破坏力大,几乎全部中青年男性,集结后立即打砸,目标感强;3,防暴警察的执法不作为步调统一;4,各路喇叭媒体和官博忙不迭对打砸暴行定性为爱国行为的过激表现;5,显示打砸暴徒的微博被极快删帖。这是不是一场根本与人民无关的有组织的暴行?

የሆነ ችግር አለ፡፡ 1ኛ. ከ40-50 ከተሞች በአንድ ግዜ እያመጹ ነው፤  2ኛ. ተሳታፊዎቹ በጣም ብዙ አይደሉም ነገር ግን ጥፋታቸው የጎላ ነው፤ ብዙዎቹ ታዳጊ ወንዶች ሲሆኑ አንድ ዒላማ ለማጥቃት በአንድነት ነው የሚዘምቱበት፤ 3ኛ.አድማ በታኞች አልተዘጋጁም፤ 4ኛ. በመንግስት ይዞታ ያለው እና የአገሪቱ አስተያየት መሪ ተደርጎ የሚወሰደው መገናኛ ብዙሐን ክስተቱን እንደ ምክንያታዊ የአገር ጥቅም ጥያቄ ወስዶታል፤ 5ኛ. ጥፋት አዘል አመጾችን የሚያሳዩ ጥቃቅን ጦማሮች ሳይቀሩ ተወግደዋል፡፡ ይህ የተቀነባበረ አመጽ ከሕዝቡ ጋር ምንም ግንኙነት ላይኖረው ይችል ይሆን እያልኩ እያሰብኩ ነው?

አንዳንድ ጦማሪዎች አመጹ ከመጪው የ18ኛው የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ብሔራዊ ኮንግረስ ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ጠርጥረዋል፡፡ ሌሎች የዜና ወኪሎች ቀድሞውንም የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴ (የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አመራር) አባላት ቁጥር ከ9 መቀመጫዎች ወደ 7 እንደሚቀንስና የፖለቲካ እና የሕግ ጉዳዮች ኮሚቴው ከዋና አመራርነት እንደሚወገድ ዘግበዋል፡፡

ኮሚቴው የተዋቀረው የሕዝብ ደህንነት፣ የሕግ አፈፃፀም እና ፍትሐዊነት በቻይና ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት ሲሆን፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት “ሰላምና መረጋጋትን” የማስፈን ኃላፊነት  ነበረበት፡፡ ይህ ዓይነቱ ተግባር የቀድሞው ቾንግቂንግ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ እና ከሕዝብ ደህንነት ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ቦ ዢላይ እና የአሁኑ የፖለቲካ እና የሕግ ጉዳዮች ኮሚቴ ጸሐፊ ዦው ዮንገካንግ ስህተት ተደርጎ ነው የሚቆጠረው፡፡

ዜቦ ላይ የተገኙ ትንታነዎች ከታች ተቀምጠዋል [zh]፡-

唐吏宋:宣传口子和政法口子在某位大神的指点之下搞出了这么一些卵子。这就是他们想要的结果。然后就有借口进行以后一系列行动了。那个时候就又有得玩了。这才是他们的目的。他们是导演。你们甘愿当演员。受害者和受益者是谁麻烦动个脑子这样的剧本每个朝代都有上演。难道我们也要经历一次么?

ታንግ ሶንግ ሒስቶሪ፡- የፕሮፓጋንዳ ባለስልጣናት እና የፖለቲካ እና የሕግ ጉዳዮች ኮሚቴ በሆነ ትዕዛዝ አብረው እየሰሩ ነው፡፡ እነርሱ የሚፈልጉት ለአደረጉት ነገር ይቅርታ እንዲጠየቁ ነው፡፡ ከዚያ፣ ቲያትሩን ድጋሚ ያስኬዱታል፡፡ ይኸው ነው ሕልማቸው፡፡ እነርሱ አዛጋጆቹ ናቸው እናንተ ደግሞ ፈቃደኛ ተዋናዮች፡፡ እባካችሁ ተጠቂዎቹ እነማን እንደሆኑና እነማን እንደሚጠቀሙ አስቡ? ታሪክ በየዘመናቱ ራሱን እየደገመ ነው፡፡ አሁንም ደግመን ልናልፍበት ይገባናል?

全能RVP:为何台湾香港没有发生反日打砸抢?只有一个原因,就是共军自导自演+共军洗脑导致!~

RVP፡- ለምንድን ነው በታይዋን እና ሆንግ ኮንግ አመጻዊ ድርጊት የሌለው? አንድ ምክንያት ብቻ ነው ያለው፣ ኮሙኒስቶቹ ሁሉንም ድርጊት በራስመር ትወና እየተጫወቱት ነው፡፡

常啸九天:您老还看不出来吗?这就是借反日之名发泄对政府的不满,其背后可能有“毛左”的操纵。当局内外交困了!

ጮክ ብለህ አልቅስ እንዲህ አለ፡- አይታያችሁም? የፀረ-ጀፓኑን አመጽ ሕዝቡ በመንግስታችን ላይ ያለውን ቁጭት እንዲወጣበት እያደረጉ ነው፡፡ የማኦዎች ግራ ክንፍ ምናልባትም ከበስተጀርባ ይኖራል፡፡ ማዕከላዊው ባለስልጣን በውስጣዊውም ውጪያውውም ውጥረት መሃል ተገኝቷል፡፡

ምክንያታዊ ድምጾች

የተበሳጩ አገርወዳዶች በየጎዳናው ሲያምጹ፣ ቲ ሊፍ ኔሽን እንደጠቆመው [zh]፣ ደህነኞቹ አሳቢዎች በመስመር ላይ ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ነው፡፡ ከታች ያሉት ምክንያታዊ ከሚባሉት ውስጥ የመረጥኩላችሁ ጥቂቶቹ ናቸው፡-

WeMarketing:通过这次反日打砸抢,对中国又有了新的认识,虽然已经是2012,但历史可以轻易重演,今天是以反日为名,以后可能会以反资本家,或者反外籍为名,只要你所在的人群是需要被打倒的那个,你的个人财产就可能被人不用负责的毁掉,你的人身安全就无法受保证。义和团、红卫兵、爱国贼,一代传一代。

ዊማርኬቲንግ፡- በዚህ አመጽ አዘል አመጽ ስለቻይና ጥቂት አውቃለሁ፡፡ አሁን በ2012 ላይ ነን፣ ታሪክ ግን እራሱን ይደጋግማል፡፡ አሁን በፀረ-ጃፓን ስም ነው፣ ቀጥሎ በፀረ-ካፒታሊስ፣ ወይም በፀረ-የውጭ ዜጎች፡፡ ዒላማ ውስጥ ከገቡ ቡድኖች መካከል ከሆናችሁ፣ ንብረታችሁን እና የገዛ ራሳችሁን ማዳን አትችሉም፡፡ ቡጢኛ አማጺዎችቀያይ ዘበኞች፣ አርበኛ አጋሰሶች፣ እያለ አንዱ ትውልድ ሌላኛውን ይተካል፡፡

城市茅屋:历史上的义和团和红卫兵都是先被人当枪使,然后再被人当替罪羊,千万不要成为粪青!打砸抢谁获利啊?动动脑子吧!

ኸት ኢን ዘ ሲቲ፡- በታሪክ፣ ቡጢኛው እና ቀይ ዘበኛው እንደመሳሪያ ካገለገሉ በኋላ እንደጠፉ ፍየሎች ተቆጠሩ፡፡ የተናደዳችሁ ወጣቶች ሆይ አትቀላቀሏቸው፡፡ ከነዚህ አመጾች ማን ያተርፋል? እባካችሁ አእምሯችሁን ተጠቀሙ፡፡

乐嘉:日本的高明在于用中国的7平方公里不经意间居然撬动起整个中国大陆960万平方公里疯狂的自残而我们中的很多人还以为自己是英雄。老娘问我打仗咋办,我说不怕打仗怕文革。

ሌጃ፡- ጃፓኖቹ ብልሖች ናቸው፡፡ 7 ኪሎሜትር ስኩዌር መሬት በመጠቀም 960 ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር የአሸባሪዎች መሬት ላይ የሰፈሩትን ሁሉ ያሳብዳሉ፡፡ አንዳንዶቻችን አሁንም ጀግኖች እንደሆኑ ሁሉ ይሰማናል፡፡ እናቴ ጦርነቱ ቢጀመር ምን ሊከሰት እንደሚችል ትጠይቀኛለች? እኔ ስለጦርነት አልፈራም፣ የምፈራው ስለባሕል አብዮቱ ነው አልኳት፡፡

አመጹ እንደተጧጧፈ፣ አድማ በታኝ ፖሊሶች ጠንካራ እርምጃ ወሰዱ፡፡ ምንም እንኳን፣ ሙከን ክስተት ክብረበዓል መስከረም 8/2005 ቢሆንም ፀረ-ጃፓን እንደተሟሟቀ ጥቂት ቀናት ሊቀጥል ይችላል፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.