የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር ተመዘበረ

የተመዘበረው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር እራሳቸውን  ራሳቸውን አርቲን ሐከርስ ብለው በሚጠሩ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ  መካነ ድሮች ሲመዘበሩ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ ብቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፐሬሽንየኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ  ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሌሎች መካነ ድሮች ተመዝብረዋል፡፡

 

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በማኀበራዊ ሚዲያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሶልያና ሽመልስ (@Soliyee10m) እንዲህ ስትል ተወተች፡፡

 

 Check Ethiopian Civil Service College website ecsc.edu.et ባልታወቁ ሃይሎች ሃክ የተደረገበት ሁኔታ ነው ያለው ኢንሳዎች የእኛን ጦማሮች ተወት አድርጉና ስራችሁን በስርዓት ስሩ!!

 

 ደ ብርሃን ሚዲያ በፌስ ቡክ ገጹ የሚከተለውን አስፍሯል፡፡ [EN]

 ፊሊፕ ኤን ሃዋርድ “ዘ ኦሪጅን ኦፍ ዲክታተርሺፕ ኤንድ ዴሞክራሲ፡ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኤንድ ፓለቲካል ኢስላም” በተሰኘው መጽሐፉ  የኢትዮጵያ መንግስትን የመስመር ላይ ኑባሬ “ቀሽም” ሲል ይገልጸዋል፡፡አሁን ደግሞ እነዚህ መካነ ድሮች ( የመንግስት እና የግል ) ተመዝብረዋል፡፡

የዓለም ድምጾች ጦማሪው አቤል አስራት ደግሞ እንዲህ ሲል ምዝበራውን አበረታቷል፡፡

 ጎሽ እነርሱን ብቻ ማን አጋጅ እና መዝባሪ አደረጋቸው

 

 ማህሌት ሰለሞን በበኩሏ እነዚህን መካነ ድሮች የመጠበቅ ኃላፊነት ያለውን መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ደብረጽዮንን ከእንቅልፍ ይቀሰቅሱ ዘንድ ወዳጆቿን በመጠየቅ ተሳልቃለች፡፡

 

የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በመካነ ድሩ “የመረጃ እና የተግባቦት ቴክኖሎጂን ለመታደግ የተወለደ” ቢልም የኮሌጁን እና ሌሎች እርሱን መሰል መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን መካናት መጠበቅ አልቻለም፡፡ከዚህ ይልቅ በመንግስት ላይ ሰላ ትችት የሚያቀርቡ መካነ ድሮች እና ጦማሮችን አድኖ በማገድ ይታወቃል፡፡ አዲሱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴርም ይህ የእቀባ ተግባር እንደሚቀጥል በቅርቡ ለአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል፡፡

2 አስተያየቶች

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.