ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ፤ መለስ ዜናዊ ከመቃብር ውስጥ ትዊት እያደረጉ ነው

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት፣ የሰኞ ዕለት የመንግስት ኃላፊዎች ማረጋገጫ በታንዛኒያ የሚገኙ የማሕበራዊ አውታር ተጠቃሚዎችን አነቃንቋል፡፡ በተለይ የአቶ መለስ ትዊተር አካውንት ነው ከሚባለው መልስ ማግኘት ከተጀመረ በኋላ ነገርዬው ተጋግሎ ነበር፡፡

ነገሩ ወዲህ ነው፣ የታንዛኒያ ፓርላማ አባል ዢቶ ዙቤሪ ካብዌ የሚከተለውን በትዊተር ላይ ጻፉ፡-

@zittokabwe: በጠቅላይ ሚኒስትር #መለስ ዜናዊ ሞት ለ#ኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማኝ ሐዘን ጥልቅ ነው፡፡ ስለዴሞክራሲያዊት አቢሲኒያ ዕድገት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ሱዛን ማሺቤ ‏መልስ ሰጠች:

@iMashibe: @zittokabwe አሁን እውነት ሆነ ማለት ነው? Cc @SwahiliStreet

እናም ስዋሂሊ ስትሪት መደምደሚያ ሰጠ:

@iMashibe በኢቴቪ ተነግሯል. አሁን ተረጋግጧል @zittokabwe

ቻምቢ ቻቻጌ ከተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ (UNECA) ‘የመለስ ዜናዊ ስንብት ለአፍሪካ ወጣት መሪዎች‘ (በእንግሊዝኛ) የሚል ጦማር ጽፎ በኑቬምበር 16፣ 2006 በሌሎች ተጽፎ የነበረ ጽሑፍ በትዊተር አጋራ፡፡

ከዚያ በኋላ ድንገት@PMMelesZenawi (መለስ ዜናዊ) ጣልቃ ገቡ፤ ከሞት በኋላ ለታንዛኒያው የፓርላማ አባል ዢቶ ካብዌ መልስ መስጠት ጀመሩ፡

@PMMelesZenawi: @zittokabwe እባክዎ ከኔ የተሻለ ይሁኑ፡፡ እዚህ ቀልድ የለም፤ ዋጋዬን ልከፍል እየተዘጋጀሁ ነው http://www.ethiopianreview.net/index/?p=42267

መለስ ዜናዊ ‏@PMMelesZenawi – ከሞት በኋላ. ምንጭ: ከትዊተር ላይ የተወሰደ

ይህ 29,000 ላለው ለዢቶ ካብዌ የተጻፈ ትዊት መወያያ ርዕስ ከፍቷል፡፡ ግምቱ ‏@PMMelesZenawi በተቀናቃኛቸው ተጠልፎ ይሆን የሚል ነበር፡፡

@zittokabwe: @hmgeleka ይህ አካውንት እውነተኛ ወይም የቅርብ ጊዜ አይመስለኝም @pmmeleszenawi

ዢቶ ዙብሪ ካብዌ ይህንን ገምተው ቀጠሉ፡

@zittokabwe: @AnnieTANZANIA በ@PMMelesZenawi ትዊት የተደረገልኝ እውነተኛ አይደለም፡፡ ተዉት በቃ፣ አካውንቱ በተቀናቃኛቸው ተጠልፏል፡፡

ኦማር ኢሊያስ መልስ ሰጠ:

@omarilyas: ይህ አካውንት መጀመሪያውንም የውሸት ነበር፡፡ @PMMelesZenawi – ልክ እንደ @Julius_S_Malema @zittokabwe ሁሉ አስመስሎ ለቀልድ የተሰራ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በመለስ ዜናዊ ብሔራዊ ውርስ ዙሪያ ሙግቱ ችሎታቸውን ከማድነቅ ጀምሮ እስከ መለስ ዜናዊ ዴሞክራት አይደሉም የሚለው መደምደሚያ ድረስ ተጋግሎ ቀጥሏል፡-

@Htunga: @zittokabwe መለስ ግን የምር ማን ነው? ኢትዮጵያውያኖች እየተራቡ እና በጭነት መኪናዎች ላይ ታፍነው እየሞቱ አያለሁ፡፡ በ2010 በመሳሪያ ሲጨፈጨፉም አይቻለሁ፡፡

@zittokabwe: @Htunga በኔሬሬ ጊዜ ታንዛኒያዎችስ እየተራቡና እየሞቱ አልነበረም? ነገር ግን በመርሆቹ መሰረት እናከብረዋለን፡፡ መለስም ያው ነው፡፡

@zittokabwe: @PMMelesZenawi ከስህተተታቸው ባሻገር #መለስ ዜናዊ የኔ አርአያ ሆነው ይቀጥላሉ፡፡  ነፃነትን መልሶ የማግኘት መብት አለህ #ደርግ ወይም ኢሳይያስ

የውሸቱ  (ምናልባትም የተጠለፈው) የ@PMMelesZenawi የትዊተር አካውንት፣ ከላይ ያየነውን ክርክር ከማስነሳቱም በላይ ብዙ የአፍሪካ መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች የትዊተር አካውንታቸውን እውነተኝነት አለማረጋገጣቸውን እንደጥያቄ አስነስቷል፡፡

ከዚህ በፊት እንደተነገረው፣ ትዊተር እንዲህ ዓይነት አካውንቶችን ማረጋገጫ እንዲያስቀምጥ ሲጠየቅ ወይ ለረዥም ጊዜ መልስ ሳይሰጥ ይቆያል አሊያም ደግሞ ከናካቴው መልስ ሳይሰጥ ይቀራል፡፡

በታንዛንያ ከፍተኛ ዝነኝነት ያገኘው ትዊተር አመለካከቶችን እና ክርክሮችን ያስተናግዳል፣ ለሰበር ዜናዎችም እንደማስተላለፊያ ምንጭ እየሆነ ነው፡፡ በተቃራኒው ግን፣ ትዊተር ልክ አሁን በ@PMMelesZenawi አካውንት እንደሆነው ሁሉ በቀላሉ ሊጭበረበሩበት ይችላል፡፡ የምንጮችን እውነተኝነት በተመለከተ መደነጋገር እና ጥርጣሬን ይይዛል፡፡

ሌሎች የውሸት፣ ምናልባት የተጠለፉ ወይም ደግሞ ለቀልድ በውሸት የተፈጠሩ የአፍሪካ ትዊተር ማንነቶች ውስጥ እነዚህኞቹ ይገኛሉ:@Hailemdesalegne, @Julius_S_Malema, @kabwezitto, @alfredmutua እና @MwaiKibaki

መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ. ከ ከ1991 እስከ 1995 የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት እና በ1995 በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

 

2 አስተያየቶች

 • Hi
  please focus about Haw Ethiopian avoid poverty,Haw can protest the enemy of our unity,
  Haw can use our countries row material,Haw can defeat corruption especially the delegated person of our country & greedy person,Haw can expand modernization & the like….. just i comment you for necessary topic.Other stick is nutting use fore our country.
  Thank you.
  faithfully Misrak.

 • mahteme

  እውነት ከሆነ ጭፍን አስተያየት እና ጥላቻ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ብሎም ኋላ ቀርነት ነው፡፡ ስለዚህ የሚድያ አካላት ሆኑ የመረጃ መረቦች ከ አድሎ ነፃ የሆነ ታማኝነት የሰፈነበት ዘገባ ማስተላለፍ ያላቸውን ክብር ያስጨምራል፡፡
  በመሰረቱ የመረጃ መረቦች ገሚሱ ህዝብ ወዶቸው ሌላው ጠልቷቸው የሚቀጥሉ ከሆኑ እነዚህ ስኬታማ አደሉም ፡፡ ምክንያቱም ማንኛውም መረጃ አስተላላፊን ማንም ሊጠላው አይገባምና ፡፡

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

 • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
 • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.