ታሪኮች ስለ የዜጎች መገናኛ ብዙሐን ከ ሚያዝያ, 2013
ኢራን፤ እንደወንድ እየሆንክ፣ እንደሴት ልበስ
ቀይ ቀሚስ ሻርፕ እና ዓይነ እርግብ ያደረገ አንድ ሰው በማሪቫን ከተማ መንገዶች ኩርዲስታን ግዛት ኢራን ውስጥ በፀጥታ አካላት እየታጀበ እንዲጓዝ ተደረገ፡፡ በቤት ውስጥ ፀብ ምክንያት ጥፋተኛ የተባሉ ሦስት ሰዎች በከተማው መሐል የሴት ቀሚስ አድርገው እንዲጓዙ የግዛቲቱ ፍርድ ቤት ፈርዶባቸዋል፡፡ የቅጣቱ ዓይነት ለብዙዎች ግልጽ ባይሆንም በርካቶች ግን በቅጣቱ እንዲቆጡ አነሳስቷል፡፡
ጅቡቲ፤ ‘ዲሞክራሲያዊ’ ምርጫን ተከትሎ የመጣው እስር
ትንሽ አገር ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ እጅግ በጣም ስትራቴጂክ አገር በሆነችው ጅቡቲ የየካቲት 15፣ 2005 አገር አቀፋዊ ምርጫን ተከትሎ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ፡፡ በምርጫው ‹የሕዝቦች አንድነት ለዕድገት› (People's Rally for Progress) የተሰኛው ፓርቲ በድጋሚ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡመር ጉሌህ ጅቡቲን እ.ኤ.አ ከ1999 ጀምሮ የመሩ ሲሆን በምርጫውም የ80 በመቶ መራጮች ድምፅ ቢያገኙም በከፍተኛ ሁኔታ በማጭበርበር ተጠርጥረዋል፡፡ እስሩ የመጣውም በዚሁ ማጭበርበር ጉዳይ [fr] ላይ ዜጎች ሰልፍ በመውጣታቸው ነው፡፡ እንደየጅቡቲ ሰብኣዊ መብት ሊግ እና የዓለምአቀፍ ሰብኣዊ መብት ፌደሬሽን ከሆነ 90 ሰዎች በአሰቃቂነቱ በሚታወቀው ጋቦዴ ማዕከላዊ እስር ቤት ታጉረዋል፡፡ እስሩ ይህ ጽሑፍ እስከተጻፈበት ሚያዚያ 20005 ድረስ ቀጥሏል፡፡