‘ለሙሰኛ ባለስልጣን ምንም ምሕረት የለም’

ስራ አስፈፃሚ አካላት ችግራቸውን ማስተካከል የማይችሉ ማንኛውም ባለስልጣናት እንዲያባርር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ግፊት ያደርጋል፡፡”

 

ይህንን የተናገሩት የኦሮሚያ ክልልና የኦህዴድ- ኢህአዴግ ፓርቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ አባ ዱላ ገመዳ  በአሁን ሰዓት ደግሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናቸው፡፡ይሁንና አቶ አባ ዱላ ገመዳ ራሳቸው በኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚታወቁት በከፍተኛ ሙሰኝነታቸው ሲሆን በአዲስ አበባ

ዙሪያ ያሉ መሬቶችን ለባለሀብቶች በሕገ ወጥ መንገድ አከፋፍለዋል ተብለውም ይታማሉ፡፡ ባንድ ወቅት  እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸውን በሙስና ምክንያት በመንግሥት መነጠቃቸውን  በኢትዮጵያ እንዳይነብብ የታገደው የአዲስ ነገር ጋዜጣ መካነ ድር እንዲህ ዘግቦ ነበር፡፡

የኦሮሚያ ክልልና የኦህዴድ- ኢህአዴግ ፓርቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ አባ ዱላ ገመዳ በአዲስ አበባ ቦሌ ወሎ ሰፈር አካባቢ ያስገነቡት ባለ አራት ፎቅ መኖሪያ ቤታቸውን በሙ ስና ምክንያት በመንግሥት መነጠቃቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ጸረሙስና ኮሚሽን በቅርቡ ክስ ሊመሰርትባቸው በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ የዜና ምንጮቻችን ለአዲስ ነገር እንዳስታወቁት አቶ አባዱላ ገመዳ ከጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ጋር የነበራቸው የሰመረ ግንኙነት ከተበላሸ (ፖለቲካዊ ጠቀሜታቸው ዝቅ ካለ) በኋላ ላለፉት በርካታ ዓመታት በእርሳቸው ሥም፣ በቤተሰቦቻቸውና በወዳጅ ዘመዶቻቸው አካባቢ ያከማቹትን ሃብት በጥሬ ገንዘብ፣ በአይነትና በንብረት በታማኝ የኦህዴድ ፓርቲ አባላትና በደህንነት ሠራተኞች ሲሰባሰብ ነበር፡፡ . . .”

የዚህ የባለስልጣኑ ስላቅ ያስገረመው ዘላለም ክብረት እንዲሁ ሊተውው አልፈገለም፡፡ይህንን ዜና የዘገበውን የኢዜጋ መካነ ድር ለወዳጀቹ በማጋራት ተሳለቀ፡፡

Zelalem Malcolm Kibret  አባዱላ  ለሙሰኛ ባለስልጣናት ምህረት የለንም አሉ ህምምም . . . ‘ለገጣፎን’ ባሰብናት ጊዜ አለቀስን

🙁

 ሶልያና ሽመልስ ተቀበለችው፡፡


Soli Yana
 ሰበታን እና ሱሉልታንስ ቢሆን?????

ከዚህ ቀደም ናዝሬት  ላይ ያስገነቡትን ትልቅ ቪላ መኖሪያ ቤት ከትግል ያደናቅፈኛል በማለት በግል ተነሳሽነት ለኦህዴድ ፓርቲ መስጠታቸውን ያስታወሰው ደግሞ ኪሩቤል ተሾመ ነው፡፡[EN]

Kirubel Teshome What about the Vila they gave to their ENAT party ?

 

 ለእናት ፓርቲያቸው የሰጡት ቪላስ?

 

የባለስልጣናቱ አይን ያወጣ ድፍረት ያደከመው የሚመስለው አብይ ተክለማርያም  የተሳልቆውን መጠን መለካት መርጠ፡፡[EN]

Abiye Teklemariam The parody has reached its climax.

 

ማስመሰሉ ጥግ ላይ ደርሷል፡፡

እንደ ምህረት ስብሃት  ግን የቀለደ አልተገኘም [EN]

 Mihret M Sibhat In other news, Satan has declared “no more sinning”.

 

በሌላ ዜና፣  ሰይጣን “ከአሁን በኋላ ሐጥያትን የሚያደርግ የለም” ሲል አወጀ፡፡

 

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.