ኬንያ፤ ራሳቸውን ገንዘብ-ይገዛናል ብለው ያሉ ቡድኖች ‘የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮችን ለሀብታሞች’ አቀረቡ

የካምፓስ ቀውጢ-ችኮች ለሀብታሞች (Campus Divas For Rich Men) ከ26 ዓመት በታች የሆኑ የኬንያ የዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎችን በማንኛውም ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሀብታሞች ‘ለማጣበስ’ የተፈጠረ የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡ ገጹ የተጠቀመበት መሪ ቃል “ገንዘብ-ይገዛናል” የሚል ነው፡፡

ኪስ 100፣ ሀት 96 እና ክላሲክ 105 በተሰኙ የኬንያ ሬድዮ ጣቢያዎች እና በተለይ ደግሞ በስታንዳርድ ጋዜጣዴይሊ ኔሽን  እና የኬንያ ኬቲኤን እና ኬ24 ቴሌቪዥኖች ሰፊ ሽፋን ከተሰጠው በኋላ የመረብዜጎች (netizens) የሚከተሉትን ‹ሀሽታጎች› ፈጥረው በትዊተር እና ፌስቡክ ላይ አስተያየቶችን አስፍረዋል፡- #campusdivasforirchmen፣ #HakunaKituUtafanya (ምንም ማድረግ አይቻልም)፣ #CandidatesBetterThanRomney፣  #TeamMafisi [teamhyena]፣  #wordszawazito [wordoftherich]፣  #Kiss100 እና #KOT፡፡

Picture of Facebook Page of Campus Divas for Rich men. Photo by asselo.wordpress.com

የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች ስዕል፤ ፎቶው የ asselo.wordpress.com ነው፡፡

ሌሎች የመረብዜጎች ጉዳዩን የራሳቸው ጦማሮች እና ዩቱዩብ ላይ በማዛወር በከፍተኛ ሁኔታ ወግ በሚያጠብቅ ማኅበረሰብ ውስጥ የተከፈተውን ይህንን ገጽ በማውገዝ እና በመደገፍ ሥራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ስለገጹ የተነሳው ሙግት የማኅበራዊ አውታሮች ቁጥጥር፣ የኤችአይቪ/ኤድስ፣ ሃይማኖት እና አፍሪካዊ ልምዶች፣ የኬንያውያን ወጣቶች ዕድል፣ ድህነት፣ ብልሹነት እና የአቻ ግፊት በኬንያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ያለው ጦስ ለውይይት እንዲነሱ አድርጓል፡፡

እን ኬንያንፎረም፡-

በጁላይ 3/2012 የተፈጠረው ገጽ ከአሁኑ 50,684 ወዳጆች (‘likes’) እና 65,830 ስለገጹ እያወሩ ያሉ ጎብኝዎችን አግኝቷል፡፡

ኬንያንሊስት የተሰኘ/ች ኬንያዊ ጦማሪም ለመጠቆም እንደሞከረው/ችው፡-

የገጹ ፈጣሪ የተጠቀማቸው ምስሎች ከበይነመረብ ላይ የተለቀሙ ስዕሎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ታስቦ ነበር፣ በኪስ 100 ሬዲዮ ይደውሉ የነበሩ ሰዎች ግን አንዳንዶቹን ሴቶች በጓደኝነት ያውቋቸው እንደነበር በመናገራቸው እውነትነቱ ተረጋግጧል፡፡

ሰሎሞንሪሽ ግን ገጹ አሁንም ቢሆን በአንዳንድ ሸረኛ የመረብዜጎች የተፈጠረና በኬንያዊ ወጣት ተማሪዎች ላይ የሚያላግጥ የውሸት ገጽ ነው፡፡ ይህ/ች ጦማሪ እንደሚለው/ትለው፡-

ምርመራዬ እንደሚያረጋግጠው፣ ይሄ ገጽ እና ሌሎችም እንዲህ ያሉት ገንዘብ ማግኘት በሚፈልጉ ሸረኞች የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ኅብረት ይፈጥሩና ሀብታሞችን ከካምፓስ ሴቶች ጋር በማገናኘት ገንዘብ ይቀበላሉ፡፡ ሌሎችም ስለ መቃጠር (dating) እና ወሲብ የሚያወሩ ገጾችን አይቻለሁ፡፡ እናም በሚያፈሯቸው ብዙ ወዳጆች ገጹ ላይ ማስታወቂያ እያስቀመጡ ገንዘብ ይቀበላሉ፡፡ ሸረኞቹ የገጾቹ አስተዳዳሪዎች ለጀብዱ/ታይታ የተዘጋጁ ወጣት ተማሪዎችን ያታልሏቸውና ለፆታዊ ጥቃት፣ ለተላላፊ በሽታዎች እና መታገት ጭምር ያጋልጧቸዋል፡፡

ስለገጹ የተጧጧፈው ውይይት ገጹን የሚቃወሙት የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች ተቃዋሚ የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ እንዲከፍቱ አስገድዷቸዋል፡፡

ኬንያ-ፖስት በሚል የሚጠራ/ትጠራ ኬንያዊ በጦማሩ/ሯ፡-

ሁለተኛው ቡድን (የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች ተቃዋሚ) በመጀመሪያው ቡድን ተቃራኒ መርሕ ይሠራል፡፡ የመጀመሪያው ወሲብ፣ ወሲብ፣ ወሲብ እና ገንዘብ ሲሰብክ ይህንኛው ደግሞ ጨዋነትን በማስተዋወቅ፣ ወጣቶች እንዲታቀቡ ያበረታታል፡፡ የመጀመሪያው 20,000 ወዳጆች ፌስቡክ ላይ ሲያገኝ ተቃዋሚው ግን 5,000ዎች ብቻ ወደውታል፡፡

የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች የተሰኘውን ገጽ የተቃወሙ ሌሎች የፌስቡክ ገጾች ውስጥ እነጨዋ ቀወጢ-ቺኮች “የካምፓስ ቀወጢ-ቺኮች ለሀብታሞችን” ይቃወማሉ እና የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞችን አንፈልግምየካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች የፍቅር ሀብታም ለሆኑ ችስታ ወንዶች የሚሉ ይገኙበታል፡፡

ይህንን ተከትሎ በርካታ ኬንያውያን በትዊተር ላይ ምላሻቸውን ሲያሰፍሩ ኬንያውያን ለከፍተኛ ትምህርት መማርያ ብድር ማግኘት የሚቻልበትን መንገድ የሚያመቻች መሪ እንዲመርጡና የሚፈልጉት ሴት መጥበስ እንዲችሉ ጠይቀዋል፡-

@clansewe: የ‹ካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች› ገጽን የምትቃወሙ ኬንያውያን ሁሉ ዝባዝንኬያችሁን አቁሙ፡፡ ኬንያውያን ሁላችንም፣ ገንዘብን ከምንም በላይ እናስቀድማለን!

@kevoice: የከፍተኛ ትምህርት ብድር ( HELB [Higher Education Loans Board Allowance]) የሚያሳድግልንን መሪ በመምረጥ ለሀብታሞች የተዘጋጁትን የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ማውጣት አለብን፡፡  #TujipangeKisiasa [ራሳችንን በፖለቲካ እናደራጅ]

@mwendembae: “@lionsroar101 አሁን ደግሞ የ‹ካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞችን ተቃዋሚ› የፌስቡክ ገጽ ተፈጠረ ማለት ነው፤ ገርሞኛል፣ እኔኮ ልከሰት ነበር #idlers

የሚከተለው የዩቱዩብ አኒሜሽን ቪዲዮ የተፈጠረው ገጹን ተከትሎ በተፈጠረው ሙግት ዙሪያ ነው፡፡  የተፈጠረው የካምፓስ ሴቶችን ሕይወት ቀስበቀስ የምትጣጣም እንጂ በአንዴ ሁሉንም ነገር ለማግኘት መሞቀር ሞኝነት እንደሆነ በሚያስተምረው በሙሴ ኦቴኖ ነው፡-

http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=HhNWI1uVh2s

ይህ አስተያየት በሌሎችም ገጹን በተቃወሙ የመረብዜጎች ተንፀባርቋል፡-

@thatguydavy: የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች…… እና አሁን ለምን ማዕበል በሴቶች እንደተሰየመ ገባችሁ!

@mpalele: ስለነዚህ የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች አሳዛኙ ጉዳይ 50,000፣ ቡና እና ጥቂት ጉዞ የሀብታም ሰው ትርጉም ይመስላቸዋል፡፡

@rmresh: የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች…. ተስፋ መቁረጥ የመጨረሻው ደረጃ…

@nochiel: @savvykenya የ”ካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች ” ላይ ያሉ ፎቶዎች የቀድሞ የፕሮፋይል ስዕሎቻችሁ ሊሆኑ ስለሚችሉ ተጠንቀቁ፡፡

የኬቲን ቴሌቪዥን፣ የዩትዩብ አለፈመደብ (platform)በመጠቀም የፌስቡክ ገጹ የሴተኛ አዳሪነት ደወል እንደሆነ እና የካምፓስ ተማሪዎችን ሲጠየቁ ይህ ከተለመደው ውጪ አለመሆኑን ሲናገሩ አሳይቷል፡-

የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮች ለሀብታሞች በእንደዚህ ያለ ወግ አጥባቂ ማኅበረሰብ ውስጥ የኬንያ ወጣቶችን እና ወሲባዊ ተግባርን በተመለከተ በግልፅ ውይይትን በጉልህ ያራመደ ለመሆን በቅቷል፡፡

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.