#ውድየግብጽአየርመንገድ፣ እባካችኹ የተሻለ አገልግሎት

ባለፉት ጥቂት ዓመታት አመታት ውስጥ ግልጽ ሆኗል ፤ በበቂ ሁኔታ የሚጮህ ድምጽ እና ብዙ አድማጭ ያለው አንድ ሰው ካለ (ጥሩ አሽሙርን ለመጥቀስ አይደለም) ማኀበራዊ ሚዲያ ለለውጥ እንደትልቅ አማራጭ ሊያገለግል ይችላል፤ ለውጡ አብዛኛውን ጊዜ ፖለቲካዊ ወይም ማኀበራዊ ሲሆን ታዋቂው ጦማሪ የዶሱ ሂዘር አርምስትሮንግ እንዳረጋገጠው ደግሞ ትልልቅ ኩባንያዎች ቅሬታዎን እንዲሰሙ የማደረግም አቅም አለው፡፡

ባለፈው ረቡዕ በግብጽ አየር መንገድ አገልግሎት ተስፋ የቆረጠችው  እንግሊዝ-ግብጻዊቷ ጸሐፊ ኤሚ ሞዋፊ  ትኬት ለመቁረጥ በአየር መንገዱ ያገጠማትን ፈተና ለሌሎች ለማካፈል ወደ ትዊተር ወሰደችው፡፡

ገዳይ ትኬት ለመቁረጥ አንድ ሰዓት ሙሉ ፈጀብኝ  @flyegyptair በስልክ ላይ  #ህይወቴንአቃወሱት

ሞዋፊ መከታተያ ታርጋ( hashtag) በመጨመር  ስለ አየር መንገዱ ያላቸውን ቅሬታቸውን ትዊት እንዲያደርጉ ተከታዮቿን አበረታታች፡፡

ከዚህ በፊት በ@flyegyptair ለተጎሳቀላችሁ በሙሉ ራሳቸው መልስ እንዲሰጡን እና እንዲያስረዱ ቅሬታዬን በመደገፍ እርዱኝ ፡፡ #ውድየግብጽአየርመንገድ

ብዙዎች በፍጥነት ጥሪውን ተቀበሉት ፡፡ ዋሌድ ሞዋፊ (@WallyMow) ለጠቀች

#ውድየግብጽአየርመንገድ   የግብጽ አየር መንገድ ብርድልብስ ስለሚናፈቀኝ አንዳንዴ ቤት ስሆን እጆቼን በብርጭቆ ወረቀት አሻለው፡፡ @flyegyptair

ማኢ እልዲብ (@14inchHEELS) ቅሬታውን አሰማ፡፡

#ውድየግብጽአየርመንገድ አብራሪዎቹ ጋቢና ውስጥ ሳያጨሱ አንዴ እንኳን መብረር ብችል @AmyMowafi

@Mayounah  ተጨማሪ የሚመለከታት ነገር አለ፤

#ውድየግብጽአየርመንገድ እባካችኹ ከአየር ማቀዝቀዣው ውሀ እየተንጠባጠበ እንደሆነ ቅሬታዬን ሳቀርብ አይናችኹን አታጉረጠርጡብኝ …መነገር ያለበት ጉዳይ  እንደሆነ እኔ በጣም እርግጠኛ ነኝ፡፡

ብዙዎቹ ደግሞ በአየር መንገዱ በሚስተናገዱት “አስደሳች” ምግብ ላይ አተኩረዋል፡፡@ShadenFawaz  ስለኬኩ ይናገራል፤

#ውድየግብጽአየርመንገድ የምታቀርቡትን “ኬክ” ቀምሳቹት ታውቃላችኹ? መልካም!  ምንአልባት ካላስተዋላችኹት ምግብ አይደለም፡፡

@LailaShentenawi ተሳለቀች፡፡

#ውድየግብጽአየርመንገድ  ማንም ሰው ስለት ያለው ነገር ይዞ እንዳልተሳፈረ እግጠኛ ናችኹ፤ ግና እንዳላየ ዝም ብላችኹ በማታቀርቡት ዳቦ የሆነ ሰው ከተመታ ሊሞት ይችላል፡፡

ዋሌድ ሞዋፊ አፌዘች፤

#የተከበረውየግብጽአየርመንገድ  እኔ እንደማስበው በምትገፉት ጋሪ ውስት ያለው በተለያየ ሳህን ያስቀመጣችኹት  አሳ ፣ ዶሮ እና ስጋ ጣዕሙ አንድ ነው፡፡  @flyegyptair

@MarwaAyad  የበለጠ በግልጽ ትናገራለች፡፡

#ወድየግብጽአየርመንገድ  ምግቦቹን የሚያዘጋጀውና የሚያበስለው ማነው ? የምር ግን ማን ነው?

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.