ታሪኮች ስለ መገናኛ ብዙሐን እና ጋዜጠኝነት ከ መስከረም, 2012

ኢትዮጵያ፤ በእስር ላይ ያለውን ጦማሪ እስክንድር ነጋን ማስታወስ

  17 መስከረም 2012

ሐምሌ 6/2004 የኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት ጦማሪው እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችንም 23 የተቃውሞ ተግባር የፈፀሙ ሰዎችን ለ18 ዓመታት እና ሌላ መጠን ያለው የእስር ፍርድ ከአሸባሪነትጋ በተያያዘ በይኖባቸዋል፡፡ እስክንድር ነጋ የተቃውሞ ሐሳቦቹን መተንፈሻ ለማግኘት የመስመር ላይ ጦማሪ የሆነ ጋዜጠኛ ሲሆን መጨረሻ ጊዜ ከታሰረ አንድ ዓመት ሞላው፡፡ መስከረም 4/2005 የታሰረበት አንደኛ ዓመት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ማኅበረሰብ በፌስቡክ ላይ አስታውሶታል፡-

ዮርዳኖስ: ፓርላማው በይነመረብን የሚገድብ አዋጅ የሚያጸድቅበት ቀን ሐዘን

አዲሱ ሕግ በይነመረብን ቅድመምርመራ እና ቁጥጥር የሚያጋልጥ ነው፤ የድረአምባዎች (websites) ባለቤቶችን በመንግስት እንዲመዘገቡ እና ‹‹ልክ እንደሌሎቹ ሕትመቶች›› ፈቃድ እንዲያወጡ ይጠይቃል፡፡ የድረአምባዎች ባለቤቶች አንባቢዎቸው ድረአምባዎቻቸው ላይ ለሚለጥፏቸው አስተያየቶች ሳይቀር ኃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡