ዮርዳኖስ: ፓርላማው በይነመረብን የሚገድብ አዋጅ የሚያጸድቅበት ቀን ሐዘን

በዮርዳኖስ የፕሬስ እና ሕትመት ሕግ በበይነመረብ (Internet) ላይ ሐሳብን የመግለጽ መብትን እንዲያደግድ ተደርጎ ትላንት [መስከረም 2/2005] እንዲሻሻል ተደረገ፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት ሕጉን ከሚያፀድቁበት ፓርላማ ፊት ለፊት ጋዜጠኞች እና የነፃ ሐሳብ አራማጆች ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡

እንደመሪ ቃል “የበይነመረብ ነፃነት” የሚል ባነር የያዙት በነፃ ሐሳብን የመግለጽ መብት አራማጆች በዮርዳኖስ የበይነመረብን ሞት አዝማሚያ ጠቁመዋል፡፡ የበይነመረብ ቀብር ለተባለለት ለዚህ አዋጅ ሰልፈኞቹ ጥቁር ልብስ ለብሰው ነበር፡፡

የፀደቀው ሕግ አሁንም በሥራ ላይ ለመዋል፣ የላዕላይ ፓርላማውን ፈቃድ እና ሕጎች ሁሉ በዮርዳኖስ በተግባር ላይ ከመዋላቸው በፊ የሚያስፈልጋቸው የዳግማዊ ንጉሥ አብዱላህን ፊርማን ይጠብቃል፡፡ ጀሚል ኒመሪ የተባሉ፣ አዋጁን የተቃወሙ የፓርላማ አባል፣ አዋጁን ከመቃወምም ባሻገር ሰልፉ ላይም ተሳትፈዋል፡፡ እንደርሳቸው አባባል እንዲህ ዓይነት አዋጆች ነፃነትን በመገደብ የሕዝቦችን ድምጽ ብቻ ለማፈን ይጠቅማሉ፡፡

አዲሱ ሕግ በይነመረብን ቅድመምርመራ እና ቁጥጥር የሚያጋልጥ ነው፤ የድረአምባዎች (websites) ባለቤቶችን በመንግስት እንዲመዘገቡ እና ‹‹ልክ እንደሌሎቹ ሕትመቶች›› ፈቃድ እንዲያወጡ ይጠይቃል፡፡  የድረአምባዎች ባለቤቶች አንባቢዎቸው ድረአምባዎቻቸው ላይ ለሚለጥፏቸው አስተያየቶች ሳይቀር ኃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሳበት ሲሆን፣ ወዲያውም በመረብዜጎች (netizens) ሚያስከትለው ጦስ ዙሪያ ትኩረትን ለመሳብ በሚል  የመስመር ላይ እንቅስቃሴን አስጀምሯል፡፡

በትዊተር ላይ፣ የመረብ ዜጎች ብስጭታቸውን በጽሑፍ ገልጸዋል፡፡

The beginning of the Internet freedom funeral in front of the Jordanian Parliament

የበይነመረብ ነፃነት ቀብር አጀማመር በዮርዳኖስ ፓርላማ ፊት ለፊት፡፡ ፎቶግራፉ የተገኘው ከሞሐመድ አል ቃድ ትዊተር ላይ ነው፡፡

ሞሐመድ አልቃድ በትዊቱ [አረብኛ]

بلشت جنازة حرية الانترنت #انترنت_بلا_قيود
@moalQaq: የበይነመረብ ነፃነት ቀብር ተጀምሯል

ይህንን ፎቶግራፍ ያጋራው ከሰልፉ ቦታ ሆኖ ነው፡፡

ኒዛር ሳማሪም በበኩሉ:

أقر مجلس النواب قبل قليل مشروع القانون المعدل لقانون المطبوعات و النشر.. اخص
@NizarSam: የተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ማሻሻያውን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አሳለፈ… አሳፋሪ ነው

@godotbasha ደግሞ:

@godotbasha: እና አሁን በዮርዳኖስ እና በአገሪቷ ፖሊስ መካከል ንፅፅር  ‪#ከሳንሱር ጉዳይጋ ባስቀምጥ በወንጀል እጠየቃለሁ ማለት ነው? ‪#freenetjo

ሐሺም አል ባላውነህም በትዊቱ፡

مش مقتنع ابدا هدف قانون المطبوعات والنشر هو التنظيم بل هدفه تكميم الافواه وارجاع الاردن للخلف
@Jor2Day: ከፕሬስ እና ፐብሊኬሽኑ ሕግ በስተጀርባ ያለው ጉዳይ ስርዓት የማስያዝ ነው ብዬ አላምንም፤ ይልቁንም ሕዝቡን ዝም ለማሰኘትና ዮርዳኖስን ኋላ ለማስቀረት ነው

ሐኒን አቡ ሻማትም፡

@HaninSh: ከ#FreeNetJO ድራማ በስተጀርባ ምን አለ? ሴኔቱ (ላዕላይ ምክርቤቱ) እኮ መጀመሪያ ሊያፀደቀው ይገባል…. እኔ የማምነው ሴኔተሮቻችንን እንጂ ከንቱ የፓርላማ አባሎቻችንን አይደለም 🙂 #JO

የሻህዘይዶ ምላሽ፤

@Shahzeydo: ኋላ በሚቆጩበት ሕግ የዮርዳኖሳውያን አስተዳደር የዮርዳኖስን የዕውቀት ምጣኔ ኃብት ላይ ማዕቀብ ጣለበት፡፡ ‘አጀብ’ የመንግስት አመክንዮ እየወደቀ ነው፡፡  #FreeNetJo”

ማጅ ዮሴፍም ቀጥሎ:

الحرية في بلادنا قتلوها و اتهموها بشرفها عشان يطلعوا براءة من دمها
@Mayousef: ነፃነትን በአገራችን ገደሏት እና መልሰው እኛኑ በክብረቢስነት እየከሰሱ ገጽታቸውን ይገነባሉ፡፡

ፋዲ ዛገሞት አስተያየት ሲሰጥ:

يوم أسود في تاريخ الأردن
@ArabObserver: በዮርዳኖስ ታሪክ ውስጥ አንዱ ጥቁር ቀን

ሞሐመድ ሻዋሽም ሲያስጠነቅቅ:

مش قادر اعبر اكتر عن امتعاضي – مجلس النواب الأردني انتو لعبتو بالنار

@Moeys: ስለብስጭቴ ምንም አልልም – የዮርዳኖስ ፓርላማ፣ ከእሳት ጋር እየተጫወትክ ነው

ባሽር ዚዳን አዲሱን የነፃነት ጥቃት ከዮርዳኖሳውያን የበይነመረብ ፀደይ ጋር ያያይዘዋል፡፡ እሱ እንደሚለው፡

منذ بدء #الربيع_الاردني والحكومة تقمع وترفع وتحجب وتقمع.. فاهمين الموضوع غلط!

@BasharZeedan: መንግስት ከ#ዮርዳኖሳውያን_ ፀደይ ጀምሮ እስካሁን እየጨቆነ፣ ቅድመምርመራ እያደረገ እና እያፈነ ቆይቷል… ጉዳዩ አልገባቸውም

እናም ኦማር ቁዳህ ሲጨምርበት:

مجنون من ظن أنه قادر على تسييج الفضاء كما يسيج دوار ومزرعة‏! ‏
@OmarQudah: የእርሻ ቦታን እንደሚያጥር፣ ነፃነትን አጥራለሁ ብሎ የሚያስብ ሰው እብድ ነው!

ኦማር ካመል ምርጫውን ለማስተጓጎል እንደተወሰደ የእርምጃ ደወል ይመለከተዋል፡

مجلس “الأنياب” .. اشوف فيك يوم !! وهذا سبب الف بعد الالف لمقاطعة الانتخابات!
@BshMosawer: ‘የገጣጦች’ ፓርላማ… መከራችሁን የምታዩበትን ቀን እናፍቃለሁ! ይሄንኛው ሌሎች ምክንያቶችን የሚከተለው ምርጫውን ለማስተጓጎል ያላችሁ 1000ኛው ምክንያት ነው!

አቀንቃኞች በAvaaz.com ላይ “በይነመረብን አድን” በሚል ዳግማዊ ንጉሥ አብዱላህ፣ የመረጃ ሚኒስትር እና የፓርላማ አባላት በፕሬስ እና ሕትመት ሕጉ ማሻሻይ ላይ ድጋሚ እንዲያስቡ የሚጠይቅ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀምሯል፡፡

ሒዩማን ራይትስ ዋች በበኩሉ፣ በዮርዳኖሳውያን ድረአምባዎች ላይ ዕቀባ ለመጣል የፓርላማውን ይሁንታ ባገኘው አዋጅ ዙሪ ያ “ዮርዳኖስ፤ በመስመር ላይ ሐሳብን የመግለፅ መብትን ቀድሞ ወደመመርመር እየሄደች ነው ” የሚል ሪፖርት አውጥቷል፡፡

 

1 አስተያየት

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.