ታሪኮች ስለ ፌዝ ከ መስከረም, 2012

#ውድየግብጽአየርመንገድ፣ እባካችኹ የተሻለ አገልግሎት

ባለፉት ጥቂት ዓመታት አመታት ውስጥ ግልጽ ሆኗል ፤ በበቂ ሁኔታ የሚጮህ ድምጽ እና ብዙ አድማጭ ያለው አንድ ሰው ካለ (ጥሩ አሽሙርን ለመጥቀስ አይደለም) ማኀበራዊ ሚዲያ ለለውጥ እንደትልቅ አማራጭ ሊያገለግል ይችላል፤ ለውጡ አብዛኛውን ጊዜ ፖለቲካዊ ወይም ማኀበራዊ ሲሆን ታዋቂው ጦማሪ የዶሱ ሂዘር አርምስትሮንግ እንዳረጋገጠው ደግሞ ትልልቅ ኩባንያዎች ቅሬታዎን እንዲሰሙ የማደረግም አቅም አለው፡፡

ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ፤ መለስ ዜናዊ ከመቃብር ውስጥ ትዊት እያደረጉ ነው

  9 መስከረም 2012

"ከዚያ በኋላ ድንገት@PMMelesZenawi (መለስ ዜናዊ) ጣልቃ ገቡ፤ ከሞት በኋላ ለታንዛኒያው የፓርላማ አባል ዢቶ ካብዌ መልስ መስጠት ጀመሩ:: @PMMelesZenawi: @zittokabwe እባክዎ ከኔ የተሻለ ይሁኑ፡፡ እዚህ ቀልድ የለም፤ ዋጋዬን ልከፍል እየተዘጋጀሁ ነው" የሚለው መልስ በታንዛኒያ ከፍተኛ ውይይት ፈጠረ::