2012 አልቋል፤ እናም ለፍራንኮፎን (የፈረንሳይ ቅኝ [የነበሩ]) አገራት የተረጋጋ 2013 በጉጉት ይጠብቃሉ፡፡
በ2012 በማሊ፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ኮንጎ) እና በሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ የትጥቅ ትግል ተካሂዷል፡፡ በሴኔጋል፣ ኩዊቤክ እና ፈረንሳይ ደግሞ ምርጫ ተካሂዷል፡፡ በቻድ፣ ማዳጋስካር እና ቶጎ ደግሞ ለውጥን የሚጠይቁ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ በርካታ ክርክሮች ስደትን፣ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውሶችን እና እኩል የጋብቻ መብቶችን በተመለከተ ተደርገዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ የሆኑት ዓበይት ለውጦችን ለማምጣት ሲሆን መረጃ በመለዋወጥ ዘዴ ነው፡፡
በ2012 የመጀመሪያው ክለሳችን፣ በፍራንኮፎን አገራት ውስጥ የተከናወነውን ጠቅለል አድርገን እናቀርባለን፡-
የማሊ መጪው ጊዜ (በማርክ-አንድሬ ቦይስቨርት)
ረዥም ሰንሰለታማ ኩነቶች በ2012 የቱዋርግ አማጺያን ያደረጉትን ወታደራዊ መፈንቅል እና የሰሜን ማሊን መውደቅ (በዚያው ሰበብ አካባቢው በኢስላማዊ ቡድኖች መያዙን) ተከትሎ አገሪቱን ድምጥማጧን አውጥቶታል፡፡ ማቧሪያ የሌላቸው ወታደራዊ ንጠቶች ተበራክተው ነበር፤ ባሳለፍነው አንድ ዓመት፣ የማሊ ዴሞክራሲያዊ እና ልማታዊ መልካም ገጽታ ሙሉ ለሙሉ ጠልሽቷል፤ አገሪቱንም መረጋጋት አሳጥቶ፣ ሰብሮና ትኩረት አሳጥቷት አልፏል፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት የትዊተር ጽሑፎች፣ የፌስቡክ ማስታወሻዎች እና ጦማሮች የግል ጉዳዮች ነበሩ፡፡ በ2012 መባቻ ላይ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጽሑፎች (አሁን ለተሰረዘው እና ሚያዝያ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ለነበረው ምርጫ) በፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩ እጩዎች የሚጻፍ ብቻ ነበር፡፡
በ2012 ማሊዎች፣ ከዋናው መገናኛ ብዙኃን ይልቅ ማኅበራዊ አውታሮችን ተቆጣጠሩ፡፡ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በኢስላሚስቶቹ ደርሰዋል የሚሏቸውን ጥፋቶች የሚያሳዩ ምስሎችን #Mali በተሰኘ ሀሽ-ታግ በመለጠፍ ተቆጣጠሩት፤ በተለይም ማሊሊንክ በተሰኘው ዝነኛ የመልዕት መለዋወጫቸው አማካይነት፡፡
የሰሜን ዜጎች ኅብረት (ኮረን) እና የCri de Cœur ማኅበር ማሊዎችን እና ወዳጆቻቸውን ለተወረሩ ቦታዎች ሰብኣዊ እርዳታ እንዲለግሱ አስተባበሩ፡፡ ማኅበራዊ አውታሮች ከዚያ በኋላ የሕዝቦች አለመቻል የሚንፀባረቅበት ተራ ቦታ ብቻ ሳይሆን ሰዎችን በማስተባበር ለለውጥ የሚነሱበት እና ሁኔታዎችን የሚጋፈጡበት ሆኗል፡፡
የማሊ ሕዝቦች የውጭ ጣልቃ ገብነት – በይነመረብ የዚያ ምሳሌ ነው – አልናፈቁም፡፡
የሕዝባዊ ሽግግርን ፈተና ማለፍ?
በ2012ቱ የፈረንሳይ ምርጫ የምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ማዕከላዊ ርዕስ ነበር፡፡ አራት ዓመታት ከሚጠጋ ቀውስ በኋላ ጥያቄው፣ ከጊዜያዊ ጥያቄነት በላይ ተሻግሮ የማኅበራዊ ቅርጽ ለውጥ እና የማምለጫ መንገዶች ላይ ያተኮረ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
አዳዲስ ሐሳቦች በወቅታዊ ምጣኔሀብታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አማራጭ አመላካቾችን ይዘው መጡ፡፡ ስታኒስላስ ጆርዳን ወቅታዊ እውነታውን በሚያሻሽሉ የሐሳብ ልውውጦች አብርኆትን እንድንጎናፀፍ ረድቶናል፡፡ በስዊዘርላን የመሠረታዊ ገቢ የቀጥታ ዴሞክራሲ ኢኒሼቲቭ ቲም ውጤት ሲሆን የዚሁ የአብርኆቱ አካል ነው፡-
L'initiative populaire « pour un revenu de base inconditionnel » propose d'inscrire dans la constitution fédérale « l'instauration d'une allocation universelle versée sans conditions » devant «permettre à l'ensemble de la population de mener une existence digne et de participer à la vie publique ». La loi réglerait le financement et fixerait le montant de cette allocation. Le revenu de base est inconditionnel : il n'est subordonné à aucune contre-prestation. [..] Comment le financer? Par l'impôt direct sur le revenu et la fortune, par l'impôt indirect sur la consommation (la TVA), par un impôt sur les transactions financières, et surtout par le transfert des ressources consacrées au financement de l'AVS, de l'AI, de l'aide sociale et des autres revenus de substitution inférieurs au montant du revenu de base.
የመቆጣጠሩ እንቅስቃሴ (occupy movement) በሰሜን አሜሪካ ነበር የተጀመረው፤ የነርሱ ትልም የቤተሰቦችን እና ተማሪዎችን እዳ በጅምላ ድጎማ (crowdfunding) አሰርዟል፣ ልክ መንግሥት ባንኮችን በደጎመበት subprime mortgage crisis መንገድ:-
[ይህ] የገንዘብ ትዕዛዛትን ከቁጥር ማቅለል (Quantitative Easing) በተመሳሰለ ሁኔታ ይፈጥረዋል፤ ነገር ግን ያንን ገንዘብ ወደ ሕዝብ የሒሳብ ቋት በማከል የመጀመሪያው የገንዘቡ ጥቅም ዕዳ መቀነስ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ብድራቸው ገቢያቸውን የበለጠባቸው ተበዳሪዎች ዕዳቸው ቢቀነስላቸውም አይሰረዝላቸውም፤ በሌላ ጽንፍ ደግሞ፣ ዕዳ የሌለባቸው ተከፋዮች ጥሬ ገንዘብ ይቀበላሉ…
ምክንያት የለሽ አማጺዎች?
የኮንጎዎቹ M23 አማጺያንም ሆኑ የሴንትራል አፍሪካ ሴሌካ ጥምረት ወይም ኢስላሚስቶች ቡድን በማሊ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ ጥያቄዎችን እምብዛም አያቀርቡም ወይም ደግሞ በተከፋፈለው እንቅስቃሴያቸው ውስጥ ተመሳሳይ ዓላማ አይታይም፡፡ እነዚህ ታጣቂዎች የተለያዩ ክልሎች ላይ መረጋጋትን ለመፍጠር በመደራደር በ2012 በጣም የተጽዕኖ አድማሳቸውን አስፍተዋል፡፡ በጁሊ ኦዎኖ እንደተገለጸው፣ በሴንትራል አፍሪካ የተደረገው ተከታታይ ጥቃት የሴሌካ አማጺያንን የአጭር ጊዜ ዒላማ የገንዘብ ነክ አጣብቂኞች እንደቀየሩት ነው፡፡ በኮንጎ አና ጉዬ ውስብስቡን የM23 አማጺያንን ታሪካዊ ዳራ እና የቅርብ ጊዜ አብዮት በዝርዝር አስቅምጧል፡፡ የገንዘብ ጉዳዩ አጣብቂኝ ኪቩ እና ካታንጋ በተሰኙት ክልሎች እጅግ ይከፋል፡፡ የ2012 አሳዛኝ ትርኢት የግጭቶች መባባስ እና ሰብኣዊ ቀውስ ለአመጽ ማቀጣጠያነት ውሏል፡፡ ጤና ነክ ጉዳዮችን ለመጠበቅ እና ማኅበራዊ ጥምረትን ለማሳደግ የተደረገው የሲቪሊያኑ እንቅስቃሴ ደግሞ በነዚህ ግጭቶች ሳቢያ ተዳክሟል፡፡
የ2012ቱ ክለሳ በነዚህ የፍራንኮፎን አገራት ዙሪያ በቅርብ ጊዜ ይቀጥላል፡፡
ለዚህ ጽሑፍ አስተዋጽኦ ያደረጉትአና ጉዬ፣ ጁሊ ኦዎኖ፣ አብዶላዬ ባሕ፣ ማርክ-አንድሬ ቦይስቨርት እና ስታኒስላስ ጆርዳን ናቸው፡፡