· ሕዳር, 2012

ታሪኮች ስለ ታሪክ ከ ሕዳር, 2012

የመለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ ኢትዮጵያውንን እያሳደደ ነው?

  30 ሕዳር 2012

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የት ይሆኑ ይሆን በሚለው ላይ ወራት የዘለቀው ግምት አቧርቶ በ57 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ በመደበኛ መንገድ ከተገለጸ ወዲህ ሦስት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ቢሆንም የመለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ዋና ዋና ከተሞች እና የገጠር መንደሮች አውራ ጎዳናዎች ላይ በተሰቀሉ ምስሎቻቸው ኢትዮጵያውያንን አጥብቀው የያዙበት እጃቸው የመላላት አዝማሚያ አላሳየም፡፡