የአንድ ቬንዙዌላዊ አገርበቀል ዩንቨርስቲ ውስጣዊ ምልከታ

ቬንዙዌላ አገርበቀል ዩንቨርስቲ ተማሪ መሆን ምን ይመስላል? ከትምህርታዊ ተግባቦት የወጡ ሦስት ተማሪዎች በእያደጉ ያሉ ድምፆች ትዕይንተ ሥራ ላይ ዲጂታል ፎቶዎችን እንዴት ማንሳት፣ በይነመረብ ላይ መስቀል እና ማጋራት እንደሚቻል ለመማር ተሳትፈው ነበር፡፡

እነዚህ ሦስት ተማሪዎች፣ በዚህ ልዩ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከቬንዙዌላ ማኅበረሰብ የተውጣጡ እና በይነባሕላዊ እና ተግባራዊ የትምህርት ዓይነቶችን እንዲለዋወጡ የሚደረገው ጥረት ማሳያ ናቸው፡፡ በመንግሥታዊው ኢንፎሴንትሮስ [es] የተሰኘ ፕሮግራም በተዘጋጀው የዩንቨርሲቲውን የሳተላይት ግንኙነት በመጠቀም ተማሪዎቹ እንቅስቃሴዎቻቸውን፣ ንብረቶቻቸውን እና አስደናቂ ውበት የተላበሰውን እና በቦሊቪያ ውስጥ 2,000 ሄክታር ላይ የተንጣለለውን ካምፓሳቸውን በበይነመበረብ አጋርተዋል፡፡

ስለ ዩንቨርስቲው እና ስለ የካቲት 2005ቱ ትዕይንተ ሥራ የተጻፉ ተጨማሪ ነገሮችን ለማንበብ እያደጉ ያሉ ድምፆች ላይ የተጻፈውን ጦማር ይጎብኙ፡፡

የሚከተሉት በተማሪዎቹ ከተነሱት እና በዩንቨርስቲው የፍሊከር ቋት ላይ የተሰቀሉ ናቸው፡፡ የፎቶዎቹን ዋና ቅጂ ለማየት ፎቶግራፎቹ ላይ ጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡

ተማሪዎቹ ለስብሰባ እና ለሌሎች ተግባራት የሚገናኙበት “ቹሩታ” በመባል የሚታወቀው እና የተለመደ ጎጆ መሳይ ቤት፤ ፎቶ በአኬንቶ

“ኪውክሲ” የተባለ በብራዚል የተገደለ የአካባቢ መሪ ምስል የግድግዳ ላይ ቅብ የቹሩንታን የውስጥ ግድግዳ አስውቦት፤ ፎቶ በአዴንቶ

በደቦ ሥራ ወቅት በፊት ገጽ ላይ የሚሳል ትዕምርት፡፡ ከክፉ መንፈስ ራስን ለመጠበቅ ሲባልም ይደረጋል፤ ፎቶ በወዳነበደቦ ሥራ ወቅት በፊት ገጽ ላይ የሚሳል ትዕምርት፡፡ ከክፉ መንፈስ ራስን ለመጠበቅ ሲባልም ይደረጋል፤ ፎቶ በወዳነ

በዩንቨርስቲው ጊቢ ውስጥ በሚያለፈው ወንዝ ዳርቻ ምግብ ሲያዘጋጁ፤ ፎ በአኬንቶ

በተማሪዎቹ የተዘጋጀ የተለመደ ዓይነት አሳ ጥብስ፤ ፎቶ በኩራኒቻ

በካምፓሱ ውስጥ የምታልፍ እና ካኖ ቱቻ የምትባል ወንዝ ላይ የተዘረጋ ድልድይ፡፡ ድልድዩን ተማሪዎች ለመታጠብያ እና አሳ ለማጥመጃ ይጠቀሙበታል፡፡ፎቶ በኩራኒቻ

ከዬክዋና ማኅበረሰብ የመጣው የጄደዋናዲ ምስል፤ ፎቶ በወዳነከዬክዋና ማኅበረሰብ የመጣው የጄደዋናዲ ምስል፤ ፎቶ በወዳነ

ሌሎችም ፎቶዎች እዚህ ይገኛሉ፡፡

Exit mobile version