ታሪኮች ስለ 'የዓለም ድምጾች' አድቮኬሲ
ለዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ለሀምሌ 24 በተዘጋጀው ትዊተር ማራቶን ላይ በመካፈል አጋርነቶዎን በተግባር ያሳዩ::
በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::
የትርጉም መርሐ ግብር፤ ዓለምአቀፍ የበየነ መረብ ነጻነትን ጥበቃ መግለጫ
ለተከታዮቹ ሰባት ቀናት የዓለም ድምፆች የቋንቋ በጎ ፈቃደኞች፤ ህዝባዊ የመስመር ላይ የድጋፍ ፊርማን ይተረጉማሉ፡፡ ፊርማው በመጪው ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ህብረት (አይቲዩ) ጉባኤ ላይ የመስመር ላይ ሰብዓዊ መብት ጥበቃን የሚደግፍና የአይቲዩ...



