የቅርብ ጊዜ ጽሁፎች በ befeqe
አዳዲሶቹን ‘የግሎባል ቮይስስ’ ከሰሃራ በታች አርታኢዎች – እንዳልክ ጫላ እና ኦማር ሞሐመድ ተዋወቁ

ትልቅ መልካም ዜና አለን! ሁለት የማኅበረሰባችን አባላት - እንዳልክ ጫላ እና ኦማር ሞሐመድ በንዴሳንጆ ማቻ ተይዞ የነበረውን ከሰሀራ በታች ላለው የአፍሪካ ጉዳዮች የአርታኢነት ቦታ እየተረከቡ ነው።
ለምን አንዳንድ ቻይኖች በኪያኦቢ የማጠቢያ ኬሚካል ማስታወቂያ ውስጥ ያለው ዘረኝነት አልታያቸውም?
"ቻይኖች ከነጮች ዕኩል ሕዝቦች መሆን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ልክ እንደነጮች ሁሉ፣ ከፍ ያለ ደረጃን መጎናፀፍ የሚፈልጉት ጥቁሮች ላይ በመቆም ነው"
የኦሮሞ ሙዚቀኞችን የማፈን አሳፋሪ ገመና
የመንግሥት ሳንሱርን ለመስበር አማራጭ ይዞ የመጣውን ኢንተርኔት በመጠቀም፣ በዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ዩቱዩብ እና ፌስቡክ ላይ በተደረገ ቆጠራ ብቻ ከ300 በላይ ፖለቲካ ነክ ዘፈኖች ከ2006 ወዲህ የተለቀቁ መሆኑ የፖለቲካ ዘፈኖች መነሳሳት አለ ብሎ ለማለት ያስችላል፡፡
ኢትዮጵያ ‹ታይቶ ከማይታወቀው› የኢኮኖሚ ዕድገቷ በተፃራሪ ረኀብ ተጋርጦባታል
"ከኢትዮጵያ ውስጥ በተገኘ መረጃ መሠረት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች “ረኀብ፣ ችጋር ወይም ሞት” የሚሉ ቃላቶችን በምግብ ጥያቄዎቻቸው ውስጥ እንዳያካትቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡"
ተማሪዎች የዋና ከተማዋን የመስፋፋት ዕቅድ ለምን ይቃወማሉ?
"በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል፣ ኑሯቸውን የሚያጠፋ እና ማንነታቸውን የሚያንኳስሰውን ይህንን ዕቅድ ይዞ መቀጠል በጣም የሚያሳዝን ነው የሚሆነው፡፡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ተማሪዎች ለገበሬዎቹ ጥቅም ሲሉ ነው ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ያስቀመጡት"
ኢትዮጵያውያኖች የብሔራዊ ቴሌቪዥናቸውን ‹ውሸቶች› በኤፕሪል ዘ ፉል ቀን አፌዙበት
ኢትዮጵያውያኖች የማሞኛ (አፕሪል ዘ ፉል) ቀንን በትዊተር ላይ በመንግሥት በሚተዳደረው የአገር ውስጥ ብቸኛ የቴሌቭዥን ጣቢያቸው (ኢቴቪ) ባስመሰሏቸው የውሸት አርዕስተ ዜኛዎች እንደንፁህ የወንዝ ወራጅ ውሃ በሚንኮለኮል ትዊቶች አጥለቅልቀውት እየተሳለቁ ቀኑን አክብረዋል፡፡
ቋንቋዎች ነጻ ናቸው? የዓለም አቀፉን የአፍመፍቻ ቋንቋ የሚመለከቱ ሐሳቦች
ዛሬ የዓለምአቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን ነው፡፡ ቀኑ በUNESCO አባል አገራት የቋንቋ እና ባሕል ልዩነቶችን እና ብዝኃቋንቋዊነትን ለማበረታታት ይከበራል፡፡ ዕለቱ በተለይም በባንግላዴሽ እ.ኤ.አ. ከ1952 ጀምሮ ‹ኤኩሼ የካቲት› በመባል የሚታወቀው የቋንቋዎች...
‘ጋናን ጡመራ’ የተሰኘ የማኅበራዊ አውታር የመጀመሪያ መሰባሰቢያ ቋት እየመተመሠረተ ነው
"በአካል የመገናኛ ስፍራው (ቋቱ) ልምድ ያላቸው የስብስቡ (ቡድኑ) አባላት ለተማሪዎች እና ለባለሙያዎች ሥልጠና መስጠት የሚያስችላቸውን ዕድል ለመስጠት ረዥም መንገድ ይጓዛል፡፡"
የNSA ስለላን በተመለከተ ካርቱኖች ይላኩና፣ 1000 ዶላር ይሸለሙ
ዘ ዌብ ዊ ወንት ካርቱኒስቶችን፣ የዲዛይን ፈጣሪዎችን እና አርቲስቶችን መልሰን የምንታገልበት ቀን በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 11፣ 2014 የበይነመረብ ስለላን እና የግለሰብ ደኅንነት መብትን በተመለከተ ወጥ የካርቱኖች ውድድር ውስጥ እንዲሳተፉ...
ማንዴላ እ.ኤ.አ. ከ1918 – 2013
‹‹ማንም ማንንም በቆዳው ቀለም፣ ወይም ባለፈ ታሪኩ፣ ወይም በሃይማኖቱ እየጠላ አልተወለደም፡፡ ሰዎች መጥላት ይማራሉ፤ መጥላትን መማር ከቻሉ ደግሞ መውደድንም መማር ይችላሉ ምክንያቱም መውደድ ከተቃራኒው ይልቅ ለሰው ልጅ ልብ የቀረበ ነው፡፡›› ኔልሰን ማንዴላ