abelpoly · መስከረም, 2012

የቅርብ ጊዜ ጽሁፎች በ abelpoly ከ መስከረም, 2012

ኢራን ጎግል እና ጂሜል እንዳይታዩ አገደች

እገዳው የተላለፈበተት ምክንያት ህዝቡ ብዙዎች እንደ ስድብ ቃል የሚያዩት በዩቱዩብ የሚገኘውን ጸረ እስላም ፊልም እንዲቃወሙ ነው (ዩቲዩብ የጎግል ንብረት ነው)፡፡ ኮራማባዲ “የወንጀል ይዘት ያላቸው ቅጽበቶች ድንጋጌ ኮሚሽን” ቁልፍ አባል ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እንዳንዶች የጎግል መታገድ እውነተኛው ምክንያት ከመስከረም 22 ጀምሮ ስራ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀውን እስካሁን ግን ብቅ ያላለውን የኢራናውያን ብሔራዊ በየነ መረብ የበለጠ ለማስተዋወቅ ነው ሲሉ ከወዲሁ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

#ውድየግብጽአየርመንገድ፣ እባካችኹ የተሻለ አገልግሎት

ባለፉት ጥቂት ዓመታት አመታት ውስጥ ግልጽ ሆኗል ፤ በበቂ ሁኔታ የሚጮህ ድምጽ እና ብዙ አድማጭ ያለው አንድ ሰው ካለ (ጥሩ አሽሙርን ለመጥቀስ አይደለም) ማኀበራዊ ሚዲያ ለለውጥ እንደትልቅ አማራጭ ሊያገለግል ይችላል፤ ለውጡ አብዛኛውን ጊዜ ፖለቲካዊ ወይም ማኀበራዊ ሲሆን ታዋቂው ጦማሪ የዶሱ ሂዘር አርምስትሮንግ እንዳረጋገጠው ደግሞ ትልልቅ ኩባንያዎች ቅሬታዎን እንዲሰሙ የማደረግም አቅም አለው፡፡

ኢራን፤ “የእስልምና ወታደሮች” የካርቱኒስቱን የፌስቡክ ገጽ መዘበሩ

ዝነኛው ካርቲኒስት ማና ናዬስታኒ ማክሰኞ መስከረም 11 ፣ 2012 ራሳቸውን “የእስልምና ወታደሮች” ብለው በሚጠሩ የስርዓቱ ደጋፊ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ ሰርጎ ገቦቹ በራሳቸው የፌስቡክ ገጽ “ፈጣሪ ይመስገን ፤ የማና ናዬስታኒን የፌስቡክ ገጽ በቁጥጥር ስር አዋልነው” የሚል መልእክት በመለጠፍ(አሁን ተነስቷል) ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሊባኖስ፤ የመካነ ድር ዐውደ ርዕይ ለቅድመ ምርመራ

  12 መስከረም 2012

ሊባኖስ ከ1940 እ.ኤ..አ ጀምሮ በሊባኖስ የተደረጉ የሳንሱር እርምጃዎችን በመስመር ላይ የሚያስቀምጥ የመረጃ ቋት የመካነ ድር ዐውድ ርዕይ ለሳንሱር በመክፈት ተኩራርታለች፡፡ ይህ መካነ ድር ይፋ የተደረገው ማርች በተሰኘ የሊባኖስ ድርጅት ሲሆን ከህዝብ ርቀው ወደተቀመጡ መረጃዎች ትኩረትን ለመሳብ ነው፡፡