- Global Voices በአማርኛ - https://am.globalvoices.org -

የሱዳን የዴሞክራሲ ፀደይ ማለቂያ ወደሌለው አስቀያሚ የበጋ ንዳድ እየተቀየረ ነው

Categories: ከሰሃራ በታች, ሱዳን, መገናኛ ብዙሐን እና ጋዜጠኝነት, ሰብዓዊ መብቶች, አመጽ, ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች, የንግግር ነፃነት, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን, ጦርነት እና ግጭት, ፖለቲካ, The Bridge
[1]

ተቃዋሚዎች የሱዳን ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት አካባቢ፣ አፕሪል 2019. ፎቶ ኤም ሳለህ [1] (CC BY-SA 4.0)

ተቃዋሚዎች በሚያዚያ ወር ከ30 አምባገነናዊ አገዛዝ ዓመታት በኋላ ኦማር አል በሽርን ከሥልጣን ሲያባርሩት [2] ለመላው ዓለም መልካም ዜና ነበር። በሽር እአአ ከ2008 ጀምሮ በዘር ጭፍጨፋ እና የዳርፉር ጦር ወንጀል [3]በሔግ ሲፈለጉ ነበር።  ከሥልጣን መወገዳቸው ለሱዳን ዴሞክራሲ ቁልፍ እርምጃ ሲሆን፥ ለዳርፉሮች ደግሞ ፍትሕ ነው።

ከዚያ በኋላ የተከሰተው ግን ተስፋ አስቆራጭ ነው። የሱዳን ሠራዊት ምርጫ ለማድረግ ቃል ገባ ግን ይህ በሁለት ዓመታት ውስጥ አይሆንም። አገሪቱን አሁን እየመሩ ያሉት ወታደራዊ መሪዎች የሚመራው የሽግግሩ ወታደራዊ ምክር ቤት የበሽርን የቅርብ አማካሪዎች፣ ለምሳሌ የጃንጃውድ የዳርፉር ወታደራዊ ጭፍጨፋ በመምራት የሚጠረጠሩት ሌተ/ጄነራል አሕመድ አዋድ ኢብን ኡፍን ይጨምራል።  ብዙ የሱዳን ጉዳይ ታዛቢዎች በወታደራዊ ምክርቤት ውስጥ ነገሮችንን እያከረሩ ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ በቅፅል ሥማቸው ሔምድቲ ናቸው። ሔምድቲ በዳርፉር የተቃውሞ ድምፆችን በኀይል የጨፈለቁትን የጃንጃዊድ ተዋጊዎች ከመምራታቸውም ባሻገር ሕፃናት ወታደሮችን ከዳርፉር በመመልመል የየመን ደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ሳውዲን ወክለው እንዲዋጉ አድርገዋቸዋል። [4]

አደጋው ግልጽ ቢሆንም የሱዳን የዴሞክራሲ ኀይሎች ግን አደባባይ ተመልሰው ወጥተው በአስቸኳይ ሲቪል የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም እየጠየቁ ነው።  ጥያቄያቸው አስከፊ ጥቃት ነው ያስከተለባቸው። በጁን 3፣ በዳርፉር ጭፍጨፋ ተጠያቂ የሆኑት የጃንጃዊድ ሠራዊት የቀድሞ አባላት የተገነባው ፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች [5] ከመቶ በላይ ሰዎችን ገድሎ ሬሳቸውን ናይል ወንዝ ውስጥ ወርውሮታል። በወታደራዊ ፍተሻ ጣቢያዎች የተገኙ ሰዎችን አስቁመው፣ ደፍረዋል። ዘርፈዋል።  [6]

እነዚህ ዘግናኝ ክስተቶች እያሉም የሱዳን ዜጎች ትግላቸውን ቀጥለዋል። እሁድ ጁን 9 ሰፊ ጠቅላላ አድማ ሲያደርጉ ነበር። [7]

የበይነመረቡ ትግል

ዛሬ ዛሬ እንደሚከሰቱት ብዙ ግጭቶች፣ በአክቲቪስቶቹና በወታደሮቹ መካከል ያለውን ትግል የሚገልጽ መረጃ አለ። በሽርን ከሥልጣን ያስወገዳቸውን እና ወታደሩን እየተጋፈጡ ያሉትን ተቃውሞዎች ያስተባበሩት መካከለኛ ገቢ ያላቸው እንደ የሱዳን ባለሙያዎች ማኅበር [8] እና የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ [9] ያሉ ሱዳኖች ማኅበራዊ ሚዲያን በተለይም ፌስቡክን በመጠቀም ነው። ከጁን 3ቱ ጭፍጨፋ በኋላ፣ የሱዳን በይነመረብ በሰፊው ተዘግቶ ከርሟል፤ [10] ይህም በይነመረብ ላይ ማስተባበሩን እና ሪፖርት የማድረጉን ሥራ መሬት ላይ አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል። የሱዳን መንግሥት ከዚህ በፊት ለ68 ቀናት በይነመረብ በመዝጋት [11] ተቃውሞዎችን በመከላከል የበሽርን ከሥልጣን መሰናበት ለማስቆም ሞክሮ ነበር።

ፌስቡክ ሴቶች በሽርን ጎዳና ላይ እንዲቃወሙ በማስቻል የተለየ ሚና ተጫውቷል። ታሜራ ግሪፊን በፊት ወሬ ለመለዋወጫ ይጠቀሙበት የነበረ እና በኋላ ግን ጎንታይ የፀጥታ ሠራቶችን ለማጋለጥ እና አንዳንዴም ከመኖሪያ ሥፍራቸው እስኪሹሹ ድረስ ዒላማ እንዲሆኑ በማድረግ ሴቶች ብቻ ይጠቀሙበት የነበረ የፌስቡክ ገጽ [12] እንደነበረ ይፋ አድርጋለች። በተቃውሞ ንቅናቄዎቹ ውስ የሴቶች መኖር እና የዛግሮንዳ ዝማሬያቸው [13]— ሴቶቹ በአደባባይ ተቃውሞ ወቅት ያወጧቸው የነበሩ መፈክራዊ ዜማዎች — የአብዮቱ ፊርማ [14] ሆኗል። በሽር መንግሥት በዋትሳፕ ወይም ፌስቦክ እንደማይለወጥ [15] መናገራቸው ይታዋሳል። የእርሳቸው መባረር እንደሚያሳየው የማኅበራዊ አውታሮች ንቅናቄ መፍጠሪያ መሣሪያነት ላይ መንግሥታት ተደጋጋሚ ማናናቅ እንደሚያደርጉ ነው።

አሁን ግን ተቃዋሚዎች የሚጠቀሙበትን ያክል ወታደራዊ ኀይሉም ማኅበራዊ ሚዲያዎችን እየተጠቀመባቸው ነው። በይነመረብ ሙሉ ለሙሉ አልተዘጋም። በፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ [16] ቁጥጥር ሥር ያለው እና የቀድሞ ወታደሮቹን ተግባራት የሚያሳየው [17] የመንግሥት የፌስቡክ ገጽ አሁንም አለ። የሱዳን አክቲቪስቶች ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ አመፅ የሚያበረታቱ መሆኑን አውቆ ፌስቡክ እነዚህ የመንግሥት ገጾች እንዲያግዳቸው ፊርማ እያሰባሰቡ [18] ነው።

የሱዳንን የፌስቡክ ፕሮፓጋንዳ ከመዋጋትም በተጨማሪ አገር ውስጥ ያሉ እና ስደተኛ የሱዳን አክቲቪስቶች ተቃውሞ ማስተባበራቸውን ለመቀጠል እና የመንግሥትን የመብት ጥሰቶች ለመመዘገብ ይችሉ ዘንድ በይነመረብ ለብዙኀኑ መልሶ የሚዳረስበትን መንገድ እየፈለጉ ነው። አክቲቪስቶቹ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት እና በድምፅ ጥሪ የመረጃ ልውውጥ ኔትዎርኮችን እያደራጁ ነው። ነገር ግን ለኔም የሱዳን አክቲቪስቶችእንደ ጉግል ሉን [19] ያሉ ቴክኖሎጂዎች ካርቱም ላይ የመገናኛ ዘዴ መፍጠር ይችሉ እንደሁ ለመጠየቅ እየደወሉልኝ ነው።  (መልሱም፦ ሉን ቴሌኮም አውታሮች እንደ አንቴና ሆኖ ነው የሚያገለግለው። የሱዳን አውታሮች ደግሞ ከግንኙነት ውጪ ተደርገዋል። በተጨማሪም፣ ከከተማው 20 ኪሜ ከፍ ብሎ የሚንሳፈፍ ባሉን በቀላሉ የሚሳኤል ታርጌት ሊሆን ይችላል።)

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፣ በኤዲኤስኤል (በስልክ ገመድ የሚዳረስ ኢንተርኔት አገልግሎት) ያላቸው ጥቂት ሱዳናውያን ዋይፋይ በማብራት እና የይለፍ ቃላቸውን ለወዳጆቻቸው በመስጠት ከቤታቸው መረጃዎችን እንዲለጥፉ እና እንዲለዋወጡ እያደረጉ ነበር። ከሁለት ቀናት በፊት – ማረጋገጥ ባልችልም – ኤዲኤስኤልም ተዘግቷል የሚሉ መረጃዎችን እያየሁ ነበር። ይህ አዲስ ተቃውሞዎቹን ለመበተን እንቅስቃሴ መጀመሪያቸው ይሆን ይሆናል።

ጁን 10፣ የሱዳን ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ደቡብ ሱዳን እንዳትገነጠል ባደረገው ውጊያ ታዋቂው ያሲን አርማን ከካርቱም ወደ ጁባ በወታደራዊ ሔሊኮፕተር ተገዶ ተልኳል።

ሌላኛው ዋናው የሱዳን የመረጃ መንገድ ምናልባት ከሱዳን ወደ ጎረቤት አገራት የተሰደዱ ነገር ግን ሱዳን ውስጥ ተቃውሞዎችን ከሚያደራጁ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በዚያ በኩል የሚያገኙት መረጃ ነው።

አገራት በአጋሮቻቸው ነው የሚታወቁት። ወታደራዊው መንግሥትም ብዙ የወዳጅ ሀብት አለው፦ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ [23] ለወታደራዊ አመራሮቹ የ3 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጥተዋል። የትረራም አመራርም ቢሆን ከአረብ ኢሜሪትስ ጋር ባለው ለነዚህ አገራት መሣሪያ መሸጥ የሚከለክለውን የኮንግረስ ውሳኔ እስከመሻር የሚያደርስ [24] ጥብቅ ትሥሥር ኋይት ሀውስ ፈጥኖ ደራሹን ኀይል በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲመዘግበው የተዘጋጀው ፊርማ ማሰባሰብ [25] በቅርቡ ውጤት ያመጣል ብሎ መጠበቅ አያስኬድም። (በተቃራኒው የአፍሪካን ወታደራዊ አገዛዞች ቸል በማለት የሚያስቆጭ ታሪክ ያለው የአፍሪካ ኅብረት ሱዳን በዚህ ሳምንት ካደረገችው ተቃውሞን የመጨፍለቅ ሥራ በኋላ ከአባልነት አግዷታል። [26]

እኛ ልናደርግ የምንችላቸው ጥቂት ነገሮች

ሱዳን ውስጥ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር እኛ እንደ አንድ ዜጋ የምናደርገው ይጠፋናል። አንዳንድ ሐሳቦች ምን ማድረግ እንደምንችል ሊየመላክቱ ይችላሉ፦

–  ሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ እና ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቁ። ሁሉም መንግሥታት – ወታደራዊ መንግሥታትን ጨምሮ – የሚወስዱት እርምጃ ሕዝባዊ ዕሳቤውን እየተመከቱ ነው። የሳዑዲ እና የአረብ ኢምሬትስ አገራት ሰዎች የሱዳን ሠራዊት ምን እየሠራ እንደሆነ የሚከታተሉ ከመሰላቸው ልምድ ባላቸው የዘር ጨፍጫፊዎች እየተመራ ያለውን መንግሥት ለመደገፍ ፈቃደኝነታቸው ሊገደብ ይችላል። and ሪፖርተር ዩሰራ ኤልባጊር ከካርቱም፣ ሱዳን ሆና ዜና እየሠራች ነው፤ ትዊቶቿ [27] በጣም ጠቃሚ ናቸው። Declan Walsh, the New York Times bureau chief, is doing የኒዎርክ ታይምስ ቢሮ ኀላፊ ዴክላን ዋልሽም ከመሬት ላይ ጠቃሚ ሪፖርት እያወጣ ነው። [28] ሪም አባስ የተባለው ሱዳናዊ ጋዜጠኛ እና ጦማሪም [29] በአብዛኛው በአረቢኛ በርካታ ጽሑፎችን እያጋራ ነው።  የአልጄዚራም የግጭት አዘጋገብ በጣም ጥሩ ነው። ነገር ግን በእስካይፕ ኢንተርቪው ላይ ብቻ ጥገኛ መሆናቸው የወደፊት ሽፋን አሰጣጣቸው ላይ እንቅፋት ይፈጥራል ብዬ እሰጋለሁ፦

– ሰዎች ሱዳን ውስጥ እየሆነ ያለውን ነገር ወደው እንዲከታተሉት የሐሰን ሚንጃህን – አልፎ አልፎ ቂላቂል የሆነ ነገር ግን ጥሩ ልብ ካለው የአርበኝነት ተግባር የሚመነጩ የሱዳን የዴሞክራሲ ንቅናቄ እና የመንግሥት የኀይል ምላሽ ምን እንደመሚመስል የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መከታተሉ ይጠቅማል።

– ወታደራዊ መንግሥቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ የግፊት አድራጊ ድርጅቶች – እነ ፌስቡክን ጨምሮ ከፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ የሚመጡ ጽሑፎችንም [18] ይሁን ሌሎች መሰል ይዘቶች በማስተናገድ ወታደራዊ የሽግግር መንግሥቱን መርዳት የለባቸውም።

የሱዳን በይነመረብ አገልግሎት አቅራቢዎች – ኤምቲኤን እና ዛይን – ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ናቸው፤ በኀልዩት ደረጃ የወታደራዊ መንግሥቱን ትዕዛዝ በግፊት ብዛት እምቢ ብለው በይነመረቡን ሊከፍቱት ይችላሉ። ዛይን የኩዌት ኩባንያ ነው። በሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሥር ሊወድቁ ይችላሉ። ነገር ግን ኤምቲኤን የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ነው። የአክሲዮን ባለቤቶቹ ግፊት ወይም የሕግ ተጠያቂነት ጉዳይ ሊያሰጋው ይችላል። ወዘተ. የኢንተርኔት ሶሳይቲ የተባለው ድርጅት ሱዳን በይነመረቡን መልሳ እንድትከፍተው ጥሪ አቅርቧል። [10] ምናልባት ይህ ሶሳይቲ ኤምቲኤን ላይ ተፅዕኖ ለማድረስ ማደራጃ ይሁን አይሁን ግልጽ አይለደም።

– ሱዳን ውስጥ ገንዘብ ማሰባሰብ አስቸጋሪ ይሆናል። የትራም አስተዳደር የሱዳን መንግሥት ላይ የተጣለውን የፋይናንስ እገዳ እኤአ በ2017 ቢያነሳም [30] ሌሎች የዳርፉር ግጭትን ተከትሎ የተጣሉ ዕቀባዎች አሁንም አሉ። ሱዳን ውስጥ ያሉ ጓደኞች በክሪ አሊ እና አሜሪካ ያለው የካርቱም አልሙናዮች ማኅበር  [31]ከታክስ ነጻ የሆነ US 501c3 ዕድላቸውን በመጠቀም አገር ውስጥ ያለውን የዴሞክራሲ ንቅናቄ እየደገፉ እንደሆነ ጠቁመውኛል።

በሌላ በኩል፣ የግብጽ አብዮት እና ሰፊው የዐረብ ፀደይ የፈጠሩትን ፈንጠዝያና ተስፋ ማስታወስ ከባድ ያደርገዋል። የሙዝሊም ብራዘርሁድ መንግሥት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከተመረጠ ዓመት በኋላ ወታደራዊው አምባገነን ሥልጣን ነጥቋል። አሁን የነገሠው ፍርሐት ሱዳን ከአንዱ አምባገነን ወደ ሌላው አምባገነን ልትሸጋገር ነው የሚል ወን። ከዐረብ ክረምት ወደ ሌላ ክረምት ፀደይ ሳታይ ትከርማለች የሚል ነው። አንዳንድ የሱዳን ተቃዋሚዎች “ሱዳን ወይም ግብጽ” የሚል መፈክር ይዘው የሱዳን ወደ አምባገነንነት መመለስ የመጨረሻ አስቀያሚው ውጤት መሆኑን አመልክተዋል። ከዚህም በላይ የሚከፈው ውጤት ግን ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ ሳይገባ የዳርፉሩን ዓይነት ጭፍጨፋ ሊከሰት ይችላል የሚለው ስጋት ነው። ያንን ጭፍጨፋ የፈፀሙት ሰዎች አሁን ኀላፊነት ተሰጥቷቸዋል። እኛ ደግሞ ፊት ነስተናቸዋል።