- Global Voices በአማርኛ - https://am.globalvoices.org -

በማዳጋስካር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውስጥ የሚወዳደሩት ዋነኞቹ እጩዎች እነማን ናቸው?

Categories: ከሰሃራ በታች, ማዳጋስካር, ምርጫዎች, አስተዳደር, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን, ፖለቲካ
[1]

ማዳጋስካር ውስጥ ምርጫ የሚካሄድባቸው ቦታዎች፤ በማዳትሳራ ኢንፎ-ግራፊክስ፡፡

(ይህ ፅሁፍ የተፃፈው በተጋባዥ ፀሃፊ አንድሬይ ራዛፊምባኋካ ነው፡፡ ፅሁፉ ግልፅና ለወቅታዊ ሁኔታው አመቺ እንዲሆን በማሰብ፣ የዓለም ድምፆች የአርትዖት ስራ ሰርቶበታል፡፡)

በሃገሪቱ የተከሰተውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋትንና ህዝባዊ ተቃውሞን ለማርገብ፣ ሕገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ፣ ማዳጋስካራዊያን አዲስ ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ፣ ከጥቅምት 2018 ቀደም ብለው ድምፅ ይሰጣሉ [2] ፡፡ ዋነኞቹ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች ባላቸው የኋላ ታሪክ ምክንያት የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል ፡፡

ከመጋቢት 15 እስከ 27፣ 2018 ድረስ፣ አዲስ የምርጫ ሕግ በመወጣቱ ምክንያት ፕሬዝደንቱ ከስልጣናቸው እንዲለቅቁ የሚጠይቁ ፀረ-መንግስት ተቃውሞዎች ሲካሄዱ ነበር፡፡ ከፍተኛው  ሕገ-መንግስታዊ  ፍርድ ቤት መጋቢት 28 ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ያሉበት አዲስ የጥምር መንግስት እንዲቋቋም ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ይህ የጥምር መንግስት ስራውን የሚጀምረው ሐምሌ 12 ላይ ሲሆን፣ ቀዳሚ ስራው ሃገሪቱ ከገባችበት ፖለቲካዊ ቀውስ ማውጣት ነው፡፡

ተቃውሞውን ለማስቆም፣ ፕሬዝደንት ሄሪ ራጃኦናሪማምፒያኒና የዓለም ስራ ድርጅት (ILO) ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑትን ክርስቲያን ኔትሴይ [3]ን ጠቅላይ ሚኒስትር (ስለዚህ የመንግስት ዋና መሪ ናቸው፡፡) አድርገው ሹመዋቸዋል፡፡ ከዚህ ሹመት በኋላ፣ ከ30 የሚኒስትርነት ቦታዎች፣ አስርና ከዚያ በላይ የሚሆኑት በተቀዋሚዎች እንዲያዙ ተደርጓል፡፡

የማዳጋስካር ሕገ-መንግስት ፕሬዝደንት ራጃኦናሪማምፒያኒና ምርጫ ከመደረጉ ሁለት ወር አስቀድሞ ስልጣናቸውን እንዲለቅቁ ያዝዛል፡፡ ፕሬዝደንቱ እጩ እንዲሆኑና ከሁለቱ የቀድሞ ፕሬዝደንቶች ጋር እንዲወዳደሩ የሚያስችል ጥሩ ዕድል አለ፤ ምንም እንኳ ሁሉም እጩዎች አነጋጋሪ የኋላ ታሪክ ቢኖራቸውም፡፡

ማዳጋስካር፤ በተደጋጋሚ ቀውሶች የተናጠች ሃገር

እንደ ”ፖለቲካ”(Politikà) መፅሔት አዘጋጁ አንደሪያማናምቤ ራአቶ አስተያየት ከሆነ፣

Painful and constant as they are, the Madagascan crises represent a permanent reminder of this country's instability.

ማዳጋስካር ውስጥ የተፈጠሩት ቀውሶች አሰቃቂና ማባሪያ-አልባ ቢሆኑም፣ ሃገሪቱ ያለችበትን የአለመረጋጋት ሁኔታን በግልፅ ያሳያሉ፡፡

በደሴቲቱ ታሪክ ውስጥ ባልታዬ ሁኔታ የተፈጠሩት ፖለቲካዊ ቀውሶች [4] አጠቃላይ የዕድገትና ልማት ጉዞን ለማሰናከል ችለዋል፡፡

A chaque fois que Madagascar a connu une ébauche de décollage, celle-ci s’est soldée au bout de quelques années par une crise politique majeure qui a remis en question la dynamique positive amorcée.

ሁልጊዜ ማዳጋስካር የልማት ዕቅዶችን ትተልማለች፤ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በተፈጠረው የሃገሪቱ የዕድገት ጉዞ ላይ ጥያቄ በሚያስጭር ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ፣ ዕቅዱ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡

መጋቢት 21፣ 2018 ላይ የፕሬዘደንት ሄሪ ራጃኦናሪማምፒያኒና ተቀናቃኞች አዲስ የምርጫ ሕግ ላይ ተቃውሞ አቅርበው ነበር፤ ሕጉ የቀድሞዎቹን ፕሬዝደንቶች ማርክ ራቫሎማናና እና አንድሬይ ራጃኦሊናን ቀጣዩ ምርጭ ላይ በሚሳተፉበት ወቅት የሚጎዳ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

ይህ አዲስ ሕግ ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዝደንቶች ዕጩ ሆኖ እንዳይወዳደሩ ያደርጋል፡፡

ራቫሎማናና በሰሩት ወንጀል ምክንያት ከምርጫው ሊታገዱ ይችላሉ፡፡ 2009 ላይ ፕሬዘደንታዊ የፀጥታ ጓዱን በመጠቀም፣ 40 ሰላማዊ ሰልፈኞችን ስላስገደሉ፣ በጉልበት ስራ እንዲቀጡ ተፈርዶባቸው ነበር፤ ነገር ግን በፍርዱ መሰረት፣ የጉልበት ስራው ቅጣት ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ራጆሊና የማሰታወቂያ ኩባንያ ባለቤት ናቸው፤ በዛውም የራሳቸው ሚዲያ አላቸው፡፡ ሚዲያዎችን አላግባብ መጠቀምንና ከመጠን ያለፈ ገንዘብ ለቅስቀሳ ማዋልን ሕጉ ስለሚከለክል፣ ከምርጫ ውድድሩ ሊሰረዙ ይችላሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሁለት አንቀፆች ከምርጫ ሕጉ እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

ግን የምርምር ለልማት ኢንስቲትዩት የምርምር ዳይሬክተር ሚሬሌ ራዛፊንደራኮቶ እንደሚሉት፣ የመራጩ ህዝብ ዋነኛ ተግዳሮት የሚሆነው አስከፊው ድህነት ነው፡፡ ፕሬዝደንት ሄሪ ራጃኦናሪማምፒያኒና ቢያሸንፉና ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የሚፈሰውን ዕርዳታ ከተቋረጠበት ቢያስቀጥሉ እንኳ፣ ቀውሱን ማረገብ አይችሉም፡፡ ማዳጋስካር ውስጥ ሁልጊዜ እንደሚታየው፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች እጅጉን የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ለአስርት ዓመታት በፖለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት፣ ሃገሪቱ ድህነት ውስጥ እንድትዘፈቅ ሆኗል፡፡ በዛው ልክ፣ የውጭ ዕርዳታ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ እና፣ ህዝቡ ባላቸው አቋም ሰውዬውን ያምናቸዋል? ወይስ ሌላ የመጫዎቻ ካርድ ለመቀየር ይገደዳሉ?

የቀድሞ ፕሬዝደንት ማርክ ራቫሎማና

ከ1975 እስከ 1993ና ከ1997 እስከ 2002 ድረስ ፕሬዝደንት የነበሩት ዲዲየር ራትሲራካ የፈፀሙት የምርጫ ማጭበርበር ስለተጋለጠ፣ ማርክ ራቫሎማናና 2002 ላይ ፕሬዝደንት ለመሆን በቁ፡፡ የመጀመሪያው ዙር የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር በሚያቃቅር መልኩ የተካሄደ ነበር፤ ቢሆንም፣ ለሁለተኛ ዙር ምርጫ የሚጋብዝ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ ይህ ሁኔታ እንደተፈጠረ፣ ከሁለቱ ዕጩዎች መካከል ከፍተኛ ድምፅ በአንደኛው ዙር የምርጫ ሂደት ላይ ያስመዘገበ ዕጩ የመጨረሻ ብይን እንዲሰጠው ተደረገ፡፡ ራቫሎማናና ከ50% በላይ ድምፅ አግኝተዋል፤ ስለዚህ ሁለተኛ ዙር የምርጫ ሂደት አላስፈለጋቸውም፡፡ ራቫሎማናና ምርጫውን አሸነፉ፡፡

2008 ላይ ማርክ ራቫሎማና ዳኦው ሎጅስቲክስ ለሚባል የደቡብ ኮሪያ ድርጅት፣ ከአብዛኛው ህዝብ ፍላጎት ውጪ፣ በ90 ዓመት የሊዝ ኪራይ 1.3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ሰጡ፡፡ ከዚያም፣ 2009 ላይ ሃገሪቱ በዓለምአቀፍ የፋይናንስ ቀውስ ክፉኛ ተመታች፡፡ ጎዳና ላይ የሚደረጉ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ለበርካታ ወራት ከተከወኑ በኋላ፣ ሰውዬው ሚያዚያ 17፣ 2009 ላይ ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቅቀው ወደደቡብ አፍሪካ ተሰደዱ፡፡

አንድሬይ ራጃኦሊና፤ የቀድሞ “የሽግግር ጊዜ ፕሬዝደንት”

በዛው ቀን፣ ከ2007 እስከ 2009 ድረስ የአንታናናሪቮ ከንቲባ የነበሩት አንድሬይ ራጃኦሊና በጦር ኃይሉ ታግዘው፣ ስልጣን ላይ ወጡ፡፡

ሰውዬው የቀድሞዎቹን ፕሬዝደንቶች ከሚደግፉ ቡድኖች- ከማርክ ራቫሎማናና፣ ዲዲየር ራትሲራካና አልበርት ዛፍዬ ደጋፊዎች ጋር የጥምር መንግስት ለማቋቋም፣ ቃል ገብተው ነበር፡፡ ስልጣኑ በጦር ኃይሉ እጅ ላይ ያለ ቢሆንም፣ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ራጃኦሊና ፕሬዝደንታዊ ስልጣናቸውን እንዲለቅቁና ምርጫ እንዲያካሂዱ ግፊት አደረገባቸው፡፡ 2013 ላይ ብቻ ምርጫ እንዲካሄድ አደረጉ፡፡ በአራት ዓመት የስልጣን ዘመናቸው፣ ከዜሮ በታች ወይም ኔጌቲቭ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተዳምሮ፣ የድህነት መጠን በአስገራሚ ሁኔታ ጨምሯል፡፡

ራጃኦሊና በዚህ ዓመት የሚደረገውን ምርጫ በማሸነፍ፣ ያለምንም ጥርጥር አሁን ያለውን ችግር እንደሚቀርፉ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ከዚህ አኳያ፣ ከማላጋሲያዊዉ ቱጃር፣ አሁን ስልጣን ያሉት ፕሬዝደንት አጋር ከነበሩት፣ እንዲሁም በታክስ ማጭበርበርና ለተደራጁ የወንጀል ድርጊቶች የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣሉ ተብለው ከሚታሙት ከማሚኒያኢና ራቫቶማንጋ ጋር የሰፋ ልዩነት በመካከላቸው ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡.

በዚህ ሁኔታ፣ ቀጣዩ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሌላ ቀውጢ ጊዜ ለማዳጋስካር የፖለቲካ ህይወት ይዞ እየመጣ መሆኑን የሚያረዱ ምልክቶችን እያሳዬ ነው፡፡