- Global Voices በአማርኛ - https://am.globalvoices.org -

የግልበጣ ዘገባውን ተከትሎ የቱርክ በየነመረብ ዜጎች ጠየቁ፣ መፈንቅለ መንግስት ወይስ ትያትር?

Categories: መካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ, ቱርክ, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን, ጦርነት እና ግጭት, ፖለቲካ
Cartoon widely shared on Facebook.

በፌስቡክ በስፋት የተጋራ ካርቱን

ባለፈው አርብ ሌሊት (ሐምሌ 8/9 2008 ዓ.ም.) የተፈጠረውን መንግስታዊ ትርምስ ተከትሎ በመንግስት እና በአብዛኛው ቱርካዊ እንደከሸፈ የተወሰደውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የተወሰነው የኢንተርኔት ክፍል አልተቀበለውም፡፡

ወታደሩ በትረ መንግስቱን መቆጣጠሩ እንደተነገረ ወዲያውኑ #DarbeDegilTiyatro [1] (መፈንቅለ መንግስት አይደለም ትያትር ነው) የሚል ትሬንድ ያደረገ ሀሽታግን የያዙ ጽሑፎች በማኀበራዊ ሚዲያዎች በብዛት መታየት ጀመሩ፡፡

ሀሽታጉን በመጠቀም የሚጽፉ ሰዎች 160 ሰዎች የሞቱበት፣ፓርላማው በቦምብ የተመታው እና በኢስታንቡል እና አናካራ የጦር ጀቶች በሚያስፈራ ሁኔታ ዝቅ ብለው እና ተጠጋግተው የበረሩት ክስተት  የአሁኑ ፕሬዝዳንት ሬኬፕ ጠይብ ኤርዶጋን  ቀደሞም የተፈራ እና የተከበረውን የሀገር ውስጥ ፖለቲካ ተጽዕኖውን የበለጠ ለማስፋት እንደተወነው በአማካኝ ያምናሉ፡፡

በአሁን ሰዓት በቱርክ ትዊተር ላይ ትሬንድ እያደረጉ ያሉት “የሞት ቅጣት እፈልጋለው” እና “መፈንቅለ መንግስት አይደለም፣ ትያትር ነው” ናቸው፡፡

ኦስካር ሽልማቱ ወደ ሬኬፕ ጠይብ ኤርዶጋን[RTE] ሄዷል!!!!

የኦስካር አሸናፊ… ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን!

ሐምሌ 8 – ሐምሌ 9፤ እጅግ በጣም ከጠቆሩ የቱርክ ምሽቶች አንዱ

እንደ ሬዎተርስ ብጥብጡ ሙሉ በሙሉ የፈነዳው ወታደሮቹ በሀገሪቱ ትልቋ ከተማ ኢስታንቡል የሚገኘውን የቦስፖረስ ድልድይ መግቢያ መንገዶችን የመዝጋታቸው ዘገባ በኢንተርኔት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ ሲሰራጭ ነው፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት አከባቢ የኢስታንቡል ሁለተኛው ድልድይ በወታደሩ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ከግማሽ ሰዓት በኋላ አዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ቢናሊይ ዪልዲሪም በሚያስታውቅ መልኩ እየተንቀጠቀጡ በተወሰኑ የቱርክ ጦር አባላት “አመጽ” እንደተቀሰቀሰ እና  አመጹ የፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የረጅም ጊዜ የግል ተቀናቃኝ የሆኑት መቀመጫቸውን በአሜሪካ ባደረጉት እስላማዊ መምህር ፈቱላ ጉለን [13] እንደተደገፈ ተናገሩ፡፡

ከዚያ ቀጥሎ ባሉት ሰዓታት የተኩስ ልውውጦች እና ፍንዳታዎች በኢስታንቡል እና በአንካራ ተሰሙ፤ የጦር ሂሊኮፕተሮች እና ኤፍ አስራ ስድስቶች (F16s) በቱርክ ዋና ዋና ከተሞች ሰማይ ላይ ሲራወጡ ታዩ፡፡

ቱርካውያን የበየነመረብ ዜጎች ኢንተርኔት መጠቀም እንደተቸገሩ ዘገቡ፤ እናም ተነልቢር የተባለ የግል የኢንትርኔት ኔትዎርክ [VPN] አገልግሎት ሰጪ  “በቱርክ ላሉ ጓደኞቹ” እርስ በርስ እንዲገናኙ ገደብ የሌለው የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጠ፡፡

በቱርክ ያላችኹ ጓደኞቻችን፣ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እርስ በርስ እንድትገናኙ ገደብ የሌለው የኢንተርኔት አገልግሎት አግኝታችኋል፡፡

ዋና አዛዥ መሪያቸው ወዲያው ያልታወቀ [18] ወታደሮች የቱርክን መንግስታዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን፣ የሲኤንኤን ቱርክ [19] ህንጻን እና ሌሎች ቁልፍ ዜና ማሰራጫዎች ተቆጣጠሩ፡

ሰበር ዜና፣ የወታደሮች ቡድን ሲኤንኤን ቱርክ ወደሚገኝበት ወደ ዶጋን ሚዲያ ደርሰዋል፡፡ ወደዜና ማሰራጫ ክፍልም ገብተዋል፡፡

በዚህ ትርምስምስ  መካከል ጦሩ የመንግስትን ስልጣን እንደተቆጣጠረ፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መልሶ እንደሚያሰፍን እና ወታደራዊ ስርዓት እና ሰዓት እላፊ መታወጁን የሚገልጽ መግለጫ አወጣ፡፡

ከኢስታንቡል አየር ማረፊያ ውጪ የተሰለፉ ታንኮችን የሚያሳዩ ምስሎች መውጣት ጀመሩ፡፡

የት እንደሄዱ ብዙ ሴራ ትንተና ከተካሄደ በኋላ — መፈንቅለ መንግስቱ ሲካሄድ በዓል ሲያከብሩ እንደነበረ —  ዝምታው ተሰብሮ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ሀገሪቱን ጥለው እንደወጡ የሚገልጽ ጭምጭምታ ተበተነ፡፡

ፌስታይም በተሰኘ የአይፎን ስልክ አፕሊኬሽን ለሀገሪቱ ህዝብ ባደረሱት መልዕክት ህዝብ ወደአውራ ጎዳናዎች እንዲወጣ እና ለዴሞክራሲ እንዲታገል በግልጽ ጥሪ አቀረቡ፡፡

“ወደ አውራ መንገዶች ውጡ እናም መልሱንም ስጧቸው” ብለው ተናገሩ፡፡

ህዝቦቻችን ወደአደባባዮች እና ወደ አየር ማረፊያዎች ወጥተው ለዴሞክራሲ እና ለብሔራዊ ዓላማ እንዲቆሙ እጋብዛለው፡፡

ከዚያም ህዝቡ አውራ መንገዶችን ያዘ፤ በብዙ ጉዳዮች ህዝቡ የጦር መኮንንኖችን ላይ የበላይነቱን አሳይቷል፡፡

እንደ ሲኤንኤን የቀጥታ ጦማር [24] የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራው በጠቅላላው ለ161 ሰዎች ሞት፣ ከ1400 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መቁሰል እና 2839 ወታደሮች መታሰር ምክንያት ሆኗል፡፡

እናም መንግስት የመፈንቅለ መንግስት አድራጊዎቹ ዕቅድ እንደተቀለበሰ እና በትረ መንግስቱን በሙሉ መልሶ እንደተቆጣጠረ ተናገረ፤ ምንም እንኳን  ባብዛኛው በመጓጓት ኤርዶጋን ለትንኮሳ ፖለቲካ ያለውን ውዴታ ቢረዱም በርካታ ቱርካውያን በሀገሪቱ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እንደተካሄደ ድምዳሜ ላይ ደረሱ፡፡

ይህንን አትቀበሉት፡፡ በፍጹም ሊታምን የሚችል ወሬ ቀስ በቀስ እየወጣ ነው፡፡ ይህንን ነገር በ300 የቀጥታ ስርጭት ብቻ በቀላሉ ልትተውነው አትችልም፡፡

ከመፈንቅለ መንግስቱ በፊት ኤርዶጋን የቱርክን ዴሞክራሲ የገደል አፋፍ ላይ አደረሰው፤ እነዚህ መፈንቅለ መንግስት ያካሄዱ መኮንኖች ዴሞክራሲን ወደገደሉ ገፈተሩት፡፡

አልፕ ኤረን ቶልፓል ባንድ በኩል መፈንቅለ መንግስቱ የተተወነ ነው የሚለውን ወሬ የሚያፈርስ ንድፈ ሐሳብ ሲፈጥር [29] በሌላ በኩል ዱለታን የሚረጭ ሀሰብ ጨመረ፡፡

ባለፉት ጥንድ የመጨረሻ ሳምንታት በቱርክ የታጠቀ ጦር ውስጥ የሚገኙ በርካታ ከፍተኛ ሹማምንት በክረምቱ መጨረሻ በግዴታ ጡረታ እንዲወጡ እንደሚደረግ  የሚያወሩ አሉባልታዎች ሲናፈሱ ነበር፡፡ የትላንትና ማታው እንቅስቃሴ የእነዚህ መኮንኖች ቡድን የተደራጀ ሙከራ  ይሆናል ብዬ ገምቼ ነበር፡፡

በመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ የተስተዋለው የታወቀ ቀላል ዝግጅት ማነስ እና ብቁ ያለመሆን የሴራ ንድፈሐሳብ  ወይም የተተወነ ‘ቀድሞ የተጠና ትዕይንትን’ ትያትራዊነትን ሳይዘወተር መብራራት ይችላል፡፡ ጁንታው ተዘጋጅቷል፣ ቢያንስ መፈንቅለ መንግስት የማካሄድ ሐሳብ አለ፣ ዜናው በዚያም ሆነ በዚህ ይሾልክና አሉባልታ በአከባቢው ይናፈሳል፡፡

አንዳንድ መንግስታት መረጃው ይደርሳቸዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የኤርዶጋን መጥፋት እንደገናም ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በአያሌ የውጭ ኢምባሲዎች አከባቢ የታየው የጋለ ስሜት ለአሉባልታዎቹ አስተዋጽኦ አድርገው ሊሆን ይችላል፡፡ መንግስት በቅድመ ጥንቃቄ ምቾት ውስጥ በመሆን እና  የጁንታውን ውስኑነት በመረዳት መፈንቅለ መንግስቱን መሳሪያ በማድረግ እና በመጠቀም ለራሱ ፍላጎት ሊጠቀምበት በጣም ይችላል፡፡

ምናልባትም ጁንታውን በሙሉ በእንቅስቃሴ ላይ እንዳለ ለመያዝ አቅደው ይሆናል፣ ይህም ጉዳዩን የበለጠ የተከፈተ እና የተዘጋ ያደርገዋል፡፡

ምናልባትም ጁንታው ምስጢሩ እንዳፈተለከበት እንዳወቀ ግልጽ ይሆንና በምላሹም የመጨረሻ ምርጫቸውን ለመጠቀም ያለጊዜው እርምጃ በመውሰድ ራሳቸውን ለማዳን የትላንትናውን ምሽት ቁማር ተጫውተው ሊሆን ይችላል፡፡ መፈንቅለ መንግስቱ ለምን ቀልድ እንደመሰለ እጅግ በጣም ምክንያታዊው ትንታኔ ይህ ይመስለኛል፡፡

ኤርዶጋን ከአደጋው በኋላ ያለውን ትርምስምስ እንደ ፈጣሪ ጥብቆትን መመልከቱ እጅግ በጣም ትክክል ይመስለኛል፡፡ ይህ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በተሻለ ጊዜ አልመጣም፡፡

መቶ ሰማንያ ዲግሪ የዞረው የውጭ ፖሊሲ፣ ወደ ሶርያ በመግባት የተሰራው ስህተት፣ በፓርቲው ውስጥ ያለው ታላቁ ማስወገድ፣ የሶርያ ስደተኞች ጉዳይ እነዚህ ሁሉ ፓርቲውን እርስ በርሱ ከመደጋገፍ እና መተባበር አስወጥተው ከመቼውም ጊዜ ያነሰ ሲያደርጉት ኤርዶጋንን ደግም ከመሰረቱ የተነጠለ ሆኖ ነበር፡፡

ይህ ደግሞ ኤርዶጋንን በሀገር ውስጥ ፖለቲካ ወሳኝ ድል ያጎናጽፈዋል፡፡ አሁን ለአንድ ተጨማሪ ጊዜ ድል አድራጊ መሪ ሆኗል፣ ከጦርነት ዘመቻ የተመለሰ፡፡

አውራ ጎዳናዎችን የወረሩት ህዝቦች ደግሞ የመሪያቸው ጋሻ መከታ በመሆን አንድ ይሆናሉ፤ ይህም መነጠልን ለማሸነፍ ወደሚያስችል እድል ይለወጣል፡፡ ኤርዶጋንም በድጋሚ በትክክል የተቃኘ እና  በአምላክ የተሰጠ እና የሚ’መራ መሪ መሆንን በእጁ ያስገባል፡፡ እርግጥ ነው ይህን ዝና እና ክብር አሟጦ እንደሚጠቀምበት የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

በ1826 የጃንሰሪ ጓዶች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መወገዳቸው ልክ እንደ ተስፋ ሰጭ ጉዳይ (Vaka-yı Hayriye) ሆኖ ነበር፡፡ ይህ የከሸፈ መፈንቅለ መንግስትም የስኬታማነት ገጽ አለው፡፡ ግና ትርምስምሱን በማሰብ ደግሞ በርካታ ገጾች እንደሚኖሩት መገመት እንችላለን፤ ይህ ደግሞ በትክክል ለቱርክ ዜጎች ሸክም እና ጨቋኝ የሚሆናቸውን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

በዓለማችን እጅግ በጣም ትልቅ ቋሚ ጦር ካላቸው ሀገሮች አንዷ የሆነችው ቱርክ እ.ኤ.አ. በ1960፣ 1980 እና 1997 በተደረጉ መፈንቅለ መንግስታት ጉዳት ደርሶባታል፡፡

የኤርዶጋን እና የወግ አጥባቂው ፓርቲው ፍትሕ እና ልማት ፓርቲ [AKP] መነሳት በድህረ-እስራ ምዕቱ ዘመን ጦሩ በሀገር ውስጥ ፖለቲካ የነበረውን ድርሻ በመገዝገዝ አዳክሞታል፡፡

ህገ መንግስቱን ለመለወጥ ያላቸውን ተነሳሽነት በተደጋጋሚ ያሳዩት ኤርዶጋን በቱርክ ታሪክ ከነበሩ እጅግ በጣም ብርቱ እና ከፍተኛ ጉጉት ካላቸው መሪዎች አንዱ ተደርጎው በሰፊው ይታያሉ፡፡

ምንም እንኳን ፓርቲው ሲጀምር ለአስር ዓመታት የተመነደገ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ ዝነኛ ቢሆንም የመንግስት ውሳኔን ተከትሎ ወደ ጎረቤት ሶርያ ግጭት መዝፈቁ እና በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል አስርት ዓመታት እድሜ ያስቁጠረው የኩርዱሽ አማጽያን ጋር ያለው ግጭት ማባባሱ ሀገሪቱን ወደ ጦርነት እና ወደማያስተማምን ሁኔታ ጠምዟታል፡፡