በመካነ አእምሮ ቅርጽ ሀገር በቀል ዕውቀትን ፍለጋ በቦሊቪያ

Alumnos de la Universidad Indígena Boliviana Aymara Tupak Katari. Foto usada con autorización.

የአይመራ የቦሊቪያ ሀገር በቀል ዩኒቨርሲቲ “ቱፓክ ካታሪ” ተማሪዎች ፎቶግራፍ በፍቃድ የጥቅም ላይ የዋለ

ይህ ጽሑፍ በላ ፐብሊካ መካነ ድር ላይ ከወጣው ትክከለኛ ቅጅ ተሻሽሎ የቀረበ ነው፡፡  እዚህ በድጋሚ የታተመው ባለው ጽሑፎችን የማጋራት ስምምነት መሰረት ነው፡፡ የአይማራ ቅጂ እዚህ ይገኛል፡፡

በመማሪያ ክፍሎች የሚነጋገሩት ስለ ከቅኝ ተገዢነት መላቀቅ እና እናት ምድርን ስለማክበር ነው፡፡ ባንድ በኩል ጥንታዊ ቴክኖሎጂዎችን ከጠፉበት እየፈለጉ እና በአዲስ ተፈጥሮዊ ውጤቶች እያዘመኑ በሌላ በኩል ደግሞ የምግብ ምህንድስና፣ የእስሳት ህክምና፣ የአዝመራ ጥበብ ወይም የጨርቃጨርቅ ምህንድስናን ያጠናሉ፡፡

እንኳን  ዪኒቦል ተብሎ ወደሚታወቀው ወደ አይመራ የቦሊቪያ ሀገር በቀል ዩኒቨርሲቲ “ቱፓክ ካታሪ” በደህና መጡ፡፡ ላ ፓዝ አጠገብ ዋሪሳታ ከተማ ላይ ነው የተመሰረተው፡፡ ሀገር በቀል ተማሪዎችን ከቦሊቪያ ያሰባሰበ እና መደበኛውን አካዳሚያዊ ትምህርት ከቀደምት ማኀበረሰቦች ባህላዊ ዕውቀት ጋር ማጠመርን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡

የዚህ ሀገር በቀል ዩኒቨርሲቲ የተወሰኑ ተማሪዎች በሚከተለው የምስክርነታቸው መገረማቸውን፣ ልምዳቸውን እና በዚህ ትምህርታዊ ፕሮጀከት መታቀፋቸው ለግለሰባዊ ዕድገታቸው ምን ማለት እንደሆነ ያጋሩናል፡፡ ለብዙዎቹ ዩኒቦል ማለት ጥናታቸው ጥንታዊ ዕውቀቶችን ከጠፉበት መመለስ፣ ከቅኝ ተገዢነት በተላላቀቀ አስተሰሰብ መበልጸግ እና ሁሉን አካታች የሆነ በባህሎች መካከል የሚገኝን የዕወቀት ምርትን ማሳደግ ነው፡፡

ሁሉን አካታች ትምህርት ለሁሉም

ናኦሚ ኮምፖስ ያራሪ የጨርቃ ጨርቅ ምህንድስና ተማሪ ሲሆን ስለ ዩኒቨርሲቲው እንዲህ በማለት ተናግሯል፡፡

Soy de la provincia paceña Muñecas, de la segunda sección Ayata, comunidad Huancarani […] Considero muy buena [la universidad] porque acoge a estudiantes que en su mayoría provienen de las provincias, del campo, de hogares con pocos recursos.

የመጣኹት ሙኘካስ  ከምትባል የላ ፓዝ አውራጃ በሁለተኛው የአያታ ክፍል ከሐውንካራኒ ማኀበረሰብ ነው  […] ከገጠራማው የሀገሪቱ ክፍል፣ በቤታቸው ትንሽ ሀብት ንብረት ካላቸው አውራጃዎች የሚመጡ ተማሪዎችን የሚቀበለው ይህ ዩኒቨርሲቲ በጣም ጥሩ ነው ብዬ አስባለው፡፡

ጆሲ ሉዊስ አታናሺዮ ማራዛ፣ ጉይዶ ሜንዴዛ ጁሰፔ፣ ማራያ አፓዛ ኮንዶሪ እና ቴዎዶራ ያናጉዋያ ፒሊኮ አራቱም የምግብ ምህንድስና ተማሪዎች ናቸው፡፡ ስለትምህርት ቤታቸው አስፈላጊነት ይናገራሉ፤ ታሪኩንም ያዘክራሉ፡፡

La Universidad Indígena Boliviana Aymara Tupak Katari existe gracias a la lucha de nuestros abuelos en muchos sentidos, por ejemplo en la siembra de alimentos. Ahora, desde la carrera de Ingeniería de alimentos (las otras tres son Veterinaria, Agronomía e Ingeniería textil), que ya tiene seis años, nos toca recuperar la tecnología ancestral, dar valor agregado a la materia prima e innovar con nuevos productos naturales, así como apoyar en la creación de empresas comunitarias en nuestras comunidades. Todo para el vivir bien de los bolivianos.

La Unibol fue fundada el 2 de agosto de 2008 (DS Nº 29664) en honor de nuestro líder indígena Julián Apaza Nina, alias Tupak Katari. Con su nacimiento se ha salido al paso de la discriminación que había en el país para el ingreso a las universidades.

በበርካታ ዘርፍ ለታገሉ ቀደምት አባቶቻችን ምስጋና ይግባና (ለምሳሌ በእህል ሰብል አስተራረስ) አይመራ የቦሊቪያ ሀገር በቀል ዩኒቨርሲቲ “ቱፓክ ካታሪ”  ህያው ሆኗል፡፡ ስድስት አመታትን ባስቆጠረው የምግብ ምህንድስና ጥናት ዘርፍ(የእንስሳት ህክምና፣የአዝመራ ጥበብ እና የጨርቃጨርቅ ምህንድና ሌሎቹ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ የጥናት ዘርፎች ናቸው፡፡) ጥንታዊ ቴክኖሎጂዎችን ከጠፉበት መመለስ፣ ጥሬ እቃዎች ላይ እሴት በመጨመር በአዳዲስ ተፈጥሮአዊ ምርቶች ማዘመን እና በየማኀበረሰባችን ማኀበረሰባዊ የንግድ ስራዎች እንዲፈጠሩ እንሰራለን፡፡ ሁሉም ነገር ለቦሊቪያውያን መልካም አኗኗር የሚውል ነው፡፡

ዩኒቦል የተመሠረተው ሀገሪቱ ተወላጅ  መሪ ጁሊያን አፓዛ በሌላ ስሙ ቱፓክ ካታሪን በማክበር ሐምሌ 26፣ 2000 ዓ.ም. (DS No. 29664) ነበር፡፡ ምስረታው በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቶች የተለመደውን የቅበላ መድሎን የመቃወም እንቅስቃሴን ይወክላል፡፡

የአዝመራ ጥበብ ተማሪ የሆነው ሩቤን ካስቲሎ ጁሰፔ ወደ ዩኒቦል እንዴት እንደመጣ ይናገራል፡፡

Nací en la comunidad de Ispaya Tocoli, en el municipio Ancoraimes de la provincia Omasuyos (La Paz), que se encuentra a orillas del lago Titicaca.

Estudié en la escuelita de la comunidad y tuve que enfrentar la dura caminata diaria de seis horas (ida y vuelta). Era el colegio más cercano a mi comunidad, así que no tuve otra alternativa.

Con todo y dificultades pude terminar el colegio y luego fui a prestar mi servicio militar. Al retornar a mi casa luego de un año, tenía muchas ganas de seguir estudiando. Quería ir a la universidad y sobre todo me gustaba el estudio de lenguas.

Ahora estoy estudiando en la Unibol, donde no hay la carrera de Lingüística; pero avanzo […] y ya estoy en sexto semestre.

የተወለድኩት በቲቲቻቻ ሐይቅ ኢዝፓያ ቶቾሊ ማኀበረሰብ በአንኮሪያሜስ ከተማ መዘጋጃ ቤት በኦማሱዮስ አውራጃ(ላ ፓዝ) ነው፡፡

ትምህርቴን የጀመርኩት በትንሽዬ የማኀበረሰብ ትምህርት ቤት ሲሆን የስድስት ሰዓታት ከባድ የደርሶ መልስ፣ የእግር ጉዞን ፊት ለፊት መጋፈጥ ነበረብኝ፡፡ ለእኔ ማኀበረሰብ በጣም ቅርብ የሆነው ኮሌጅ ያ ስለነበር ምርጫ አልነበረኝም፡፡

እነዚህ  አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም ትምህርቴን አጠናቅቄ ለወታደራዊ የግዴታ አገልግሎት ሄድኩኝ፡፡ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደቤቴ ስመለስ ትምህርቴን የመቀጠል ገጉት አደረብኝ፡፡ ወደ ኮሌጅ መግባት በተለይ ቋንቋዎችን ማጥናት ወደድኩኝ፡፡

አሁን በዪኒቦል እየተማርኩኝ [ምንም እንኳን የቋንቋዎች ጥናት ዘርፍ ባይኖርም] ነው፡፡ በየጊዜው እየተሻሻልኩኝ ነው፤ አሁን እንደውም ስድስተኛው መንፈቅ ዓመት ላይ ደርሻለው፡፡

በሌላ በኩል የምግብ ምህንድስና ተማሪ የሆነችው ክላውዲያ ኮልክዉ አኪውኖ የዩኒቦል ትምህርቷን እንዴት እያከናወነች እንደሆነ ታብራራለች፡፡

En la Universidad Túpac Katari se inculcan conocimientos descolonizadores a los estudiantes de las cuatro carreras. Nos enseñan lo que es el trabajo comunitario, el que se practica en las clases para que nosotros que provenimos de grupos con una identidad cultural, un origen aymara, veamos que las prácticas de nuestra formación no siempre requieren de tecnología moderna, también necesitan de instrumentos ancestrales. Al elaborar las tesinas y emprendimientos productivos, se busca y se utiliza alguna técnica ancestral que se podría aplicar a la investigación universitaria. La defensa se hace asimismo con una vestimenta originaria y a los tribunales se les ofrece la hoja de coca.

A los representantes estudiantiles les llamamos irpiris y sullka irpiri y entre nosotros nos llamamos hermanos, tal cual hacemos con los docentes, sean licenciados o ingenieros.

La forma de vestir en la Unibol es también variada y hay quienes portan la ropa que se usa en sus comunidades y provincias. Por todo esto, diría yo, ésta es una universidad distinta de las otras en el país.

በቱፓክ ካታሪ ዩኒቨርሲቲ ከቅኝ ተገዢነት የሚያላቅቅ ዕውቀት በአራት የትምህርት ዘርፎች ይሰጣል፡፡ መሠረታቸው አይማራ የሆኑ፣ ባህላዊ ማንነት ካላቸው ቡድኖች በመጡ ተማሪዎች በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚተገበር ማኀበረሰባዊ ስራ እንማራለን፡፡ በስልጠናችን ዘዴዎች ሁልጊዜ የግድ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንደማያስፈልግ እንመለከታለን፡፡ ጥንታዊ መሣሪዎችን የሚፈልጉም አሉ፡፡ ጥንታዊ የብልሃት ዘዴ ንድፈ ሐሳብ ለመቅረጽ እና ውጤታማ የንግድ ስራዎችን የሚያሳይ ነው፤ ለዩንቨርሲቲ ምርምር ስራዎች ላይ ተግባራዊ በማደረግ መጠቀምም ይቻላል፡፡ በፍርድ ቤቶች ክርክር የሚደረገው ባህላዊ ልብስ ተለብሶ የኮካ ቅጠል በመስጠት ነው፡

የተማሪዎች ተወካዮች ‘ኢሪፕሪስ’ እና ‘ሱልካ ኢሪፒሪ’  ነው የሚባሉት፤ ከመካከላችን ወንድሞች ብለን የምንጠራቸውም አለን፡፡ መምህራንን፣ ተመራቂዎችን ወይም መሀንዲሶችንም በተመሳሳይ መንገድ እንጠራቸዋለን፡፡

በዩኒቦል የአለባበስ ስርዓትም የተለየ ነው፤ እንደየአአውራጃቸው እና እንደመጡበት ማኀበረሰብ የሚለብሱም አሉ፡፡ ለዚህ ነው ይህ ዩንቨርሲቲ በሀገሪቱ ከሚገኙ ሌሎች ዪኒቨርሲቲዎች ይለያል የምለው፡፡

ተግዳሮቶች

በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ብዙዎች እንደሚሉት ፕሮጀክቱ መሻሻል የሚያሳየው እያዘገመ በመሆኑ ለማደግ እና ለመስፋፋት ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው ዘላቂ እንዲሆን ዋና ኃይል የሆኑት ተማሪዎቹ፣ ወደፊት መሻሻልን ለማምጣት የሚያስችሉ ጥሩ ዕድሎች እንዳሉ ያስባሉ፡፡ ይህንንም ሌሎች ተማሪዎችን የሚወክሉ ከፍ ያሉ ድምጾች በተሰኘው ስለዩኒቨርስቲው እና ስለእነርሱ በሚያወሳው የቀደመ ጽሑፍ እንናገኘዋለን፡፡

ዩኒቦል ብዙ ተግዳሮቶች ነበሩበት፡፡ አካዳሚያዊ ልማዶች፣ የመሳሪያዎች እጥረት እና የሀገር በቀል የኒቨርሲቲው በአከባቢው ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ ተማሪዎቹን የሚያነጋግሩ ርዕሶች ናቸው፡፡ በአዝመራ ጥበብ የትምህርት ለክፍል ተማሪ የሆነው ፍሌክስ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ባህሎች መካከል የሚነሱ ግጭቶች ላይ የፕሮፌሰሮች ሚናን ይጠቃቅሳል፡፡ በዚህ ልዩነት ምክንያት ከአውሮጳ ከተወረሱ አካዳሚያዊ ልማዶች እና በሀገር በቀል ዩኒቨርሲቲው ማካከል መገጫጨት ሊኖር እንደሚችል ግልጽ ነው

Algunos estudiantes de la carrera de Agronomía de la Unibol aymara tuvieron problemas el anterior semestre con algunos docentes de tiempo completo. [Los profesores] se habían parcializado con unos alumnos que trajeron costumbres de otras universidades [y que menospreciaban] las costumbres del pueblo aymara que son parte de los principios educativos de esta [Universidad]. Gracias a la inteligencia de la Dirección de la carrera se solucionaron los malos entendidos y se pudo seguir.

ባለፈው መንፈቅ ዓመት የተወሰኑ በአይማራ ዩኒቦል የአዝመራ ጥበብ ተማሪዎች ከተወሰኑ የሙሉ ጊዜ መምህራን ጋር ችግሮች ነበሩባቸው፡፡ መምህራኑ ከሌሎች የኒቨርሲቲዎች የተመለዱ ነገሮችን ለሚያመጡ ተማሪዎች የማዳላት አዝማሚያ ነበራቸው፡፡ ይህ ደግሞ የየኒቨርሲቲው የትምህርት መርህ አካል የሆነውን የአይማራ ህዝቦች ልማድ የሚያቃልል ነው፡፡ ምስጋና ለትምህርት ክፍሉ ቦርድ የማመዛዘን አቅም አለመግባባቶቹ ተቀርፈው ለመቀጠል ተችሏል፡፡

የአዝመራ ጥበብ ተማሪ የሆነው ጋብሬል ሴራኖ ሎፔዝም ምድሪቱን የመንከባከብ አስፈላነትን(ፓቻማማ) ይናገራል፡፡

Los desechos de plástico y otros derivados del petróleo abundan en los predios de la Unibol. Si bien en las aulas se habla de descolonizar y de respetar a la madre tierra, la Pachamama, los llamados a poner en práctica esos principios son los que contaminan el entorno con productos sintéticos. La basura de este tipo se acumula porque los estudiantes, administrativos y docentes compran refrescos, alimentos y otros productos en envases que se tiran por ahí, que llegan al río y luego llegan al lago Titicaca, agravando su grave contaminación. Ocurre que estamos en la comunidad lacustre de Cuyahuani, municipio Huarina de provincia paceña de Omasuyos.

የፕላስቲክ ቆሻሻዎች እና ሌሎች የነዳጅ ተረፈ ምርት ውጤቶች በዩኒቦል ቅጽር ግቢ ውስጥ በየቦታው ተጥለው ይገኛሉ፡፡ በመማሪያ ክፍሎች ስለፓቻማማ ከቅኝ ተገዢነት አስተሳሰብ ስለመላቀቅ እና እናት ምድርን ስለማክበር እንነጋገራለን፡፡ እነዚህ መርሖች በተግባር ላይ እንዲውሉ ሃላፊነት ያለባቸው አከባቢውን በፋብሪካ ውጤቶች የሚበክሉት ናቸው፡፡እነዚህ ቆሻሻዎች የሚከማቹት ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና መምህራን የታሸጉ ለስላሰ መጠጦች፣ ምግቦች እና ሌሎች ዕቃዎች ገዝተው ማሸጊያውን እቃ ባገኙት ቦታ ይወረውሩታል፡፡ ይህ ቆሻሻ ወደ ቲቲቻቻ ሐይቅ ሲገባ ደግሞ ብክለቱ የበለጠ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ እኛ የምንገኘው በሐይቅ ዳር በሚገኘው የኩያሃዋኒ ማኀበረሰብ በሁዋሪና የከተማ ማዘጋጃ ቤት በኦማሱዮስ አውራጃ ላ ፓዝ ውስጥ ነው፡፡

የአዝመራ ጥበብ ተማሪዎች የሆኑት ኤሚሎ ማማኒ ቺኖ እና ኢቫን አሊ በተመሳሳይ መንገድ ስላለው የውሃ እጥረት እና እነርሱ እንዴት እንደተቸገሩ ያስረዳሉ፡፡

En la Unibol TK hay problemas con los servicios básicos, especialmente con el agua, que es escasa y a veces se seca del todo. Por eso mismo, tampoco hay duchas y el aseo personal se hace difícil. Así es desde el inicio de las actividades académicas de esta universidad. Creo que es importante que los estudiantes presenten su reclamo y que las autoridades implementen las soluciones.

በቱፓክ ካታሪ ዩኒቦል በመሰረታዊ አገልግሎቶች ላይ ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ ለምሳሌ የውሃ እጠረት አለ አንዳንዴ ደግሞ ሙሉ በሙሉ የሚጠፋበት ጊዜም አለ፡፡ በዚህ ምክንያት ገላን ለመታጠብ እና የግል ንጽሕናነን ለመጠበቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ይህ ሁኔታ የተፈጠረው የዩንቨርሲቲው አካዳሚያዊ እንቅስቃሴ መጀመሪያ አከባቢ ነው፡፡ ተማሪዎች ያሉባቸውን ችግሮች ማሰማታቸው ሀላፊዎች ደግሞ መፍትሔን መፈለጋቸው አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡

ምንም እንኳን ጉድለቶች አስቸጋሪ ቢያደርጉትም ፕሮጀክቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ በተመሳሳይ በዩኒቦል የሚገኙ ተማሪዎች ‘በታላቅ ብርቅዬነት’ በሚል ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ ተቋም መውጣት እና እድገት መርዳታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ለብዙዎቹ ያጋጠሙት ችግሮች ጊዜያዊ እና የሚቀረፉ ናቸው፡፡ በመጨረሻም እንደሌሎቹ ዩንቨርሲቲዎች በተግዳሮት ውስጥ እንዳደጉት መልካም የሆነው ይቀጥላል ወይም ለመተግበር አስቸጋሪ የሆነው ይለወጣል፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.