ለዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ለሀምሌ 24 በተዘጋጀው ትዊተር ማራቶን ላይ በመካፈል አጋርነቶዎን በተግባር ያሳዩ::

Free Zone9 Tumblr collage. Images used with permission.
 የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይፈቱ ከሚለው የተምብለር ዘመቻ በፍቃድ የተወሰደ
በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው  በእስር  ላይ ለሚገኙት  የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ  እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል  ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::

የአለም አቀፍ የጦማርያን ማህበረሰብ  የሞያ አጋሮቻችን   የሆኑት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን  እና ጋዜጠኞች  በሀገራቸው  ጉዳዮች ላይ የሰለጠነ ማህበራዊ ተዋስኦ እንዲኖር ጠንክረው ከመስራት ባለፈ  ምንም የሰሩት ወንጀል ስለሌለ ፍትህ እንዲያገኙ አጥበቀን እንጠይቃለን:: የአጋሮቻችን እስር በአለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት የተደረሰባቸውን  ሰበአዊ እና ዲሞክራሲያዊ  መብቶቻቸውን የሚደፈጥጥ ከመሆኑ ባሻገር ጦማሪያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የተመሰረቱባቸው ክሶች ኢፍትሀዊ  ናቸው ብለን እናምናለን:: የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደት እየተከታተለ የሚዘግብ ድረገጽን በመመልከት ስለ ጉዳዩ ያሎትን ግንዛቤዎት ያስፉ::

 ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ  ሀምሌ 28 2006 በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ::  ፍርድ ቤት እስከ መገኛቸው ቀን እና ከዚያም በኋላ ባሉት ግዚያት የሞያ አጋሮቻችን የኛን ከፍተኛ ድጋፍ  ይሻሉ::  በመሆኑም ሀሙስ ሀምሌ 24 2006 በመላው አለም የምንገኝ ጦማሪያን: ጻህፍት እና የማህበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎች ይህንን  የድጋፍ መልእክት በየቋንቋችን ትዊተርን በመጠቀም ለማህበረሰብ መሪዮች: ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ አባላት እናስተላልፋለን::  ይህንንም በማድረግ የተለያዩ  አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት እናደርጋለን::

 ትዊተር ላይ የትኩረት ትእምርት የሆነውን የመሳላል ምልክትን እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ነጻ ይውጡ በእንግሊዘኛ #FreeZone9Bloggers:  በአለም አቀፍ ደረጃ የሚመራ የትኩረት ትእምርት እንዲሆን በትዊተር ማራቶን ላይ በመሳተፍ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን  እና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ በሚከተለው  መራሀግብር  መሰረት ይጠይቁ::  

ቀን: ሀሙስ  ሃምሌ 24፣2006

ሰአት: ጠዋት ከ4:00 ሰአት እሰከ ከሰአት 8:00 በየትኛውም የግዜ ስራት ውስጥ ይሰራል::

የትኩረት ትእምርት:  #FreeZone9Bloggers:  

 አስተናጋጆች:: ኑዋቹኩ ኢግቡንኪ @feathersproject ነደሳንጆ ማቻ  @ndesanjo ኢለሪ ሮበርትስ  @ellerybiddle

 ይህንን የትዊተር ላይ ማራቶን  ሃሙስ ለት መቀላቀል ይፈልጋሉ ? ወይ ዜናውን ለወዳጅ ዘመዶዎ ማጋራት ይፈልጋሉ? ስሞዎትን እና የትዊተር አዳራሻዎን በማህበረሰባችን የእቅድ ገጽ ላይ ማስፈር ይችላሉ::

 ምሳሌዎች

 የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ፍትህ ይገባቻዋል!

መጦመር ወንጀል አይደለም በመሆኑም የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ይፈቱ

ስለ ሚያገባን እንጦምራለን::  

የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች መታሰር የአፍሪካ የሰብአዊ እና የህዝቦች መብቶች  ቻርተር መጣስ  ነው::  

የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች መታሰር አለም አቀፉን የሲቪል እና የፓለቲካ መብቶች ስምምነት መጣስ  ነው::  

ጣቶች እስኪዝሉ እና  የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች  ፍትህ እስኪያገኙ  ትዊቶች ለመጻፍ አይታክቱ:: ፍትህ ለዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች !

8 አስተያየቶች

  • ፍቅሩ

    የዞን 9ጋዜጠኞች ሊፈቱ ይገባል የታሰሩት ያለ ጥፋታቸው በግፍ ነው የኢትዮጵያ መንግስት እርጉዝ ጋዜጠኞችን ሳይቀር ያስራል

  • እታፈራሁ ኃይሉ ተጫኔ

    መፃፍ ወንጀል አይደለም፣ ነፃነት ለጦማርያኑ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን…..
    የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ለነፃነት እየከፈሉት ያለውን ዋጋ ዓለም ትኩረት እንዲሰጠውና ስለነፃነታቸውም እንዲታገል አደራ እላለሁ፡፡
    ዞን ዘጠኝ ጦማርያን ሽብርተኞችን እና ሽብርን የሚጠሉ/ የሚፀየፉ ንፁሀን ዜጎች ናቸው፣ (የሥልጣን ናፍቆትም ፣ አምሮትም የላቸውም ናፍቆታቸው ፍትህና ነፃነት እንጂ) በማያምኑበትና በሌሉበት የተሰጣቸው ስም (ክስ) እጅግ ያሳዝነኛል፡፡ …. ግን አዝነን አንቀርም አንድ ቀን እውነት ቀን ይወጣላታል፡፡

    መንግሥት በሽብርተኝነት ክስ አቅርቦ በእስር እየተንገላቱ ያሉ ንፁሀን ወንድሞቼና እህቶቼን መንፈሳቸውን ሁሌም ጠንካራ እንዲሆን እግዚአብሔር ይርዳቸው

  • yoseph

    ጣቶች እስኪዝሉ እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ፍትህ እስኪያገኙ ትዊቶች ለመጻፍ አይታክቱ:: ፍትህ ለዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች !

  • yoseph

    ጣቶች እስኪዝሉ እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ፍትህ እስኪያገኙ ትዊቶች ለመጻፍ አይታክቱ:: ፍትህ ለዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች

  • dagmawi

    ጣቶች እስኪዝሉ እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ፍትህ እስኪያገኙ ትዊቶች ለመጻፍ አይታክቱ:: ፍትህ ለዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች !!!!!!!!!!!

  • የዞን 9ጋዜጠኞች ሊፈቱ ይገባል
    የታሰሩት ያለ ጥፋታቸው በግፍ
    ነው የኢትዮጵያ መንግስት
    እርጉዝ ጋዜጠኞችን ሳይቀር
    ያስራል

  • Abraham

    Free all Zone 9 bloggers and all political prisoners in Ethiopa

ምላሹን ያጥፉ

ንግግሩን ይቀላቀሉ -> Mesele Amare

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.