-
-
የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይፈቱ ከሚለው የተምብለር ዘመቻ በፍቃድ የተወሰደ
- በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች [1] ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::
የአለም አቀፍ የጦማርያን ማህበረሰብ የሞያ አጋሮቻችን የሆኑት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች በሀገራቸው ጉዳዮች ላይ የሰለጠነ ማህበራዊ ተዋስኦ እንዲኖር ጠንክረው ከመስራት ባለፈ ምንም የሰሩት ወንጀል ስለሌለ ፍትህ እንዲያገኙ አጥበቀን እንጠይቃለን:: የአጋሮቻችን እስር በአለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት የተደረሰባቸውን ሰበአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የሚደፈጥጥ ከመሆኑ ባሻገር ጦማሪያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የተመሰረቱባቸው ክሶች ኢፍትሀዊ ናቸው ብለን እናምናለን:: የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደት እየተከታተለ የሚዘግብ ድረገጽን [2] በመመልከት ስለ ጉዳዩ ያሎትን ግንዛቤዎት ያስፉ::
ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ ሀምሌ 28 2006 በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ:: ፍርድ ቤት እስከ መገኛቸው ቀን እና ከዚያም በኋላ ባሉት ግዚያት የሞያ አጋሮቻችን የኛን ከፍተኛ ድጋፍ ይሻሉ:: በመሆኑም ሀሙስ ሀምሌ 24 2006 በመላው አለም የምንገኝ ጦማሪያን: ጻህፍት እና የማህበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎች ይህንን የድጋፍ መልእክት በየቋንቋችን ትዊተርን በመጠቀም ለማህበረሰብ መሪዮች: ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ አባላት እናስተላልፋለን:: ይህንንም በማድረግ የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት እናደርጋለን::
ትዊተር ላይ የትኩረት ትእምርት የሆነውን የመሳላል ምልክትን እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ነጻ ይውጡ በእንግሊዘኛ #FreeZone9Bloggers: በአለም አቀፍ ደረጃ የሚመራ የትኩረት ትእምርት እንዲሆን በትዊተር ማራቶን ላይ በመሳተፍ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ በሚከተለው መራሀግብር መሰረት ይጠይቁ::
ቀን: ሀሙስ ሃምሌ 24፣2006
ሰአት: ጠዋት ከ4:00 ሰአት እሰከ ከሰአት 8:00 በየትኛውም የግዜ ስራት ውስጥ ይሰራል::
የትኩረት ትእምርት: #FreeZone9Bloggers:
አስተናጋጆች:: ኑዋቹኩ ኢግቡንኪ @feathersproject [3] ነደሳንጆ ማቻ @ndesanjo [4] ኢለሪ ሮበርትስ @ellerybiddle [5]
ይህንን የትዊተር ላይ ማራቶን ሃሙስ ለት መቀላቀል ይፈልጋሉ ? ወይ ዜናውን ለወዳጅ ዘመዶዎ ማጋራት ይፈልጋሉ? ስሞዎትን እና የትዊተር አዳራሻዎን በማህበረሰባችን የእቅድ ገጽ [6] ላይ ማስፈር ይችላሉ::
ምሳሌዎች
የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ፍትህ ይገባቻዋል!
መጦመር ወንጀል አይደለም በመሆኑም የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ይፈቱ
ስለ ሚያገባን እንጦምራለን::
የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች መታሰር የአፍሪካ የሰብአዊ እና የህዝቦች መብቶች ቻርተር መጣስ ነው::
የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች መታሰር አለም አቀፉን የሲቪል እና የፓለቲካ መብቶች ስምምነት መጣስ ነው::
ጣቶች እስኪዝሉ እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ፍትህ እስኪያገኙ ትዊቶች ለመጻፍ አይታክቱ:: ፍትህ ለዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች !