- Global Voices በአማርኛ - https://am.globalvoices.org -

ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ በእስር 1000 ቀን ሞላት

Categories: ከሰሃራ በታች, ኢትዮጵያ, መገናኛ ብዙሐን እና ጋዜጠኝነት, ሰብዓዊ መብቶች, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን, ፖለቲካ

መጋቢት 7/2006 ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ [1] የታሰረችበት 1000ኛ ቀን ነው፡፡ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ተብላ የአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ከተበየነባት ጥር 2004 ጀምሮ በእስር ላይ ትገኛለች፡፡

Jailed Ethiopian journalist Reeyot Alemu.Photo source: Facebook page of Free Reyoot Alemu campaign.

ታሳሪዋ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ:: ፎቶው በፌስቡክ ርዕዮት ዓለሙ እንድትፈታ ከሚወተውት ገጽ የተወሰደ ነው፡፡

ርዕዮት ዓለሙ፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር ስትሆን፣ የUNESCO-ጉሌርሞ ካኖ የዓለም የፕሬስ ነጻነት ሽልማት [2]የሔልማን/ሐሜት ሽልማት [3]፣ እና የዓለም አቀፍ ሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን በድፍረት የጋዜጠኝነት ሽልማት አሸናፊ ናት፡፡

እንደ የጋዜጠኞች ጠባቂ ኮሚቴው (CPJ) [4] መረጃ፣ ርዕዮት ዓለሙን እና እስክንድር ነጋ [5]ን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት 11 ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪዎችን ከ2003 ጀምሮ በፀረ-ሽብርተኝነት ስም አስሯል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የሶማሌ ብሔር አማፂ ቡድኖችን ደግፋችኋል በሚል 11 ዓመት እስር የተፈረደባቸው ሁለት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች [6] (አሁን በይቅርታ ተፈትተዋል) ይገኙበታል፡፡  

በዚህ ጦማር ላይ [7]፣ ጦማሪ በፍቃዱ ዘ ኃይሉ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችን ፈተና ጽፏል፡-

የእስር ጥቅሙ ጥፋተኞችን ማረም ከሆነ ንባብ እና ትምህርት ይህንን ግብ ለማሳካት መሣሪያዎች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ግን ሁለቱም ተፈቅደዋል፣ ነገር ግን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ለተፈረደባቸው ጋዜጠኞች በቃላሉ የሚፈቀዱ ነገሮች አይደሉም፡፡

እነዚህ እስረኞች መጽሐፍ ማስገባት አይፈቀድላቸውም፡፡ እስክንድር እንደሚለው ‹‹በተለይ ‹ኢትዮጵያ› እና ‹ታሪክ› የሚሉ ሁለት ቃላትን አንድ ላይ የያዙ ቃላት እንዲገቡ አይፈቀድም፡፡›› እነ ርዕዮት፣ እነ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም የታሰሩበት ክፍል ውስጥም እንዲያው ነው፡፡

የአገር ውስጥ ነጻ ጋዜጦች እና መጽሔቶችም እንዲሁ እንዲገቡ አይፈቀድም፡፡ እስክንድር ይህን ሲያብራራልኝ ሌላው ቀርቶ የዜና ቲቪ ቻናሎች እነ ቢቢሲ እና አልጄዚራ እሱ እና ሌሎችም የታሰሩበት ዞን ውስጥ አይፈቀዱም፡፡

ርዕዮት ዓለሙ፣ ከእስርቤቱ አለቆች ጋር ባደረገችው ብርቱ ትግል እና ሚዲያዎች ጉዳዩን ካወሩበት በኋላ የርቀት ትምህርት እንድትማር ተፈቅዶላታል፡፡ ነገር ግን ከኮሌጇ ቀጥታ ከሚላኩላት መጽሐፎች በቀር ማጠናከሪያ መጽሐፍት እንዲገባላት አልተፈቀደላትም፡፡

የትዊተር ተጠቃሚዎች #ReeyotAlemu [8] የሚለውን ሀሽታግ በመጠቀም ለታሰረችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል፡፡ ከታች ጥቂቶቹን ትዊቶች እንመልከት፡-