‘ጋናን ጡመራ’ የተሰኘ የማኅበራዊ አውታር የመጀመሪያ መሰባሰቢያ ቋት እየመተመሠረተ ነው

Blogging Ghana's proposed Social Media Hub. Photo used with permission.

ጋናን ጡመራ (Blogging Ghana) ለተሰኘው የታሰበ የማኅበራዊ አውታር ቋት/ሰፈራ፡፡ (ፎቶው በባለቤቱ ፈቃድ ነው የተለጠፈው)

በጋና፣ የበይነመረብ ተዳራሽነት መጠን 14 በመቶ ገደማ ነው፤ በተጨማሪም ባለፉት ዐሥር ዓመታት በተለይም ወጣት ጋናውያን ከመረጃ መረብ ጋር መተዋወቃቸውን ተከትሎ እያደገ፣ እያደገ መጥቷል፡፡  በዚህም፣ ማኅበራዊ አውታር የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ አንዳንዶች የማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎችና ስለምንነቱ መማር ለሚፈልጉትም ጭምር መሰባሰቢያ ስፍራ እንደሚያስፈልግ ታይቷቸዋል፡፡

ጋናን ጡመራ (Blogging Ghana)ን ይመልከቱ፣ 100 አባላት ያክል ያሉት የአገሪቱ ጦማሪዎችና ማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች ትልቅ ስብስብ ነው፡፡ ቡድኑ ጥር 12/2006 የጋናን የመጀመሪያውን የማኅበራዊ አውታር መሰባሰቢያ ቋት ለመመሥረት የሚያስችለውን ዘመቻ ድረገጹ ላይ በተደረገ ማብራሪያ ጀምሯል፡-

በአካል መገናኛ ስፍራ፣ ቋት፣ ስብስቡ ውስጥ ያሉ ብዙ ልምድ ያላቸው ጦማሪዎች ተማሪዎችን እና ባለሙያዎችን ጡመራን ብዙ ትረካዎችን (#morestories) ለመፍጠር እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ እና ማኅበራዊ አውታሮችን በመጠቀም እንደ ጋና ዜግነታቸው ተሳትፏቸውን ማበርከት እንዲችሉ ያስተምሯቸዋል፡፡

የዘመቻው አንድ እርምጃ በመሆኑ፣ ጡመራ ጋና 10,000 የአሜሪካ ዶላር በራሳቸው የጡመራ መድረክ ኢንዲዬጎጎ በኩል ለመሰብሰብ ያልማሉ፡፡ ለበይነመረብ ዘመቻው የተጠቀሙበት ሀሽታግ ብዙ ታሪኮች (#morestories) የሚል ነው፡፡ ስብስቡ ዩቱዩብ ላይ የሚከተለውን ቪዲዮም ለቋል፡-

አፍሪካ በጦማር የተሰኘ ብዙ ደራሲዎችን የአቀፈ በባብስ ሳዉል እና ሳራ አሮው የሚደገፍ የአፍሪካ ቅርስ ሰዎች የጡመራን ታሪክ በጋና አብራርተዋል፡-

ጡመራ እና ማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚነት ባለፉት አምስት ዓመታት በጋና ዕድገት አሳይቷል፡፡ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር እ.ኤ.አ. በ2005 ከነበሯት በጣት የሚቆጠሩ ጦማሪዎች ዛሬ ላይ በርካታ መቶዎች የሚሆኑ ጦማሪዎችን ለማየት በቅታለች፡፡ ይህ ዕድገት አንድ ወደጋና የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ የመጣ ስዊድናዊ በወሰደው ትልቅ ርምጃ ሊሳካ ችሏል፡፡ ካጅሳ ሆልበርግ አዱ፣ በአሁኑ ሰዓት የጋና ትልቁ የጦማሪዎች ማኅበር ሊቀመንበር ሲሆን በወቅቱ በይነመረብ ላይ በንቃት ይሳተፉ የነበሩትን ጦማሪዎች ሰብስቦ በአንድ ጣሪያ ስር ስለሥራዎቻቸው እንዲወያዩ አስችሏቸዋል፡፡ በጊዜ ሒደት፣ ይህ ትንሽ ቡድን ጡመራንና ማኅበራዊ አውታርን ባለማወቅ ዝም ያሉ ነገር ግን ቢያውቁ ኖሮ እነሱ እንደሚጠቀሙበት ሊጠቀሙበት የሚችሉ ሰዎችን ከማኅበራዊ አውታሮች ጋር ለማስተዋወቅ ወሰነ፡፡ ይህ ዕውቀትን የማሰራጨት የግል ፍላጎት ዛሬ አገሪቱ በጡመራ እና ማኅበራዊ አውታር አጠቃቀም ለደረሰችበት ደረጃ አድርሷታል፡፡

ኤድዋርድ አማርቴ-ታጎ፣ በጋናን ጡመራ ውስጥ የኮርፖሬት አገልግሎቶች ዳይሬክተር – የዛሬ አምስት ዓመት ነገሮች እንዴት እንደነበሩ አስታውሰዋል፡-

የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ በጣት የሚቆጠሩ ጦማሪዎች ብቻ ነበሩ፤ ከዚያ ወዲህ ግን ጦማሪዎች እና የኢንተርኔት ወዳጆች በአንድ ጥላ ሥር ተደራጅተው አቅማቸውን ለመገንባት እና አንዱ ከሌላው ለመማርና ሐሳቦችን ለመለዋወጥ ችለዋል፡፡ ዛሬ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብስብ ከመሆናችንም ባሻገር በየዓመቱ ጥሩ አገራዊ ይዘት ያላቸውን ጦማሮች የሚጽፉትን የምንሸልምበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ክኅሎታችንን በማጋራት ብዙ ትረካዎች እንዲፈጠሩ እንፈልጋለን፡፡

ኢኒውስ ጋና ስለዘመቻው በድረገጻቸው ላይ የሚከተለውን ጻፉ፡-

የጋና ጦማሪዎች እና የማኅበራዊ አውታር ወዳጆች የሚገናኙበት የመጀመሪያውን ቋት በመመሥረት ሊገናኙ እና ሐሳቦቻቸውን ሊለዋወጡ ነው፤ ይህ ለዘለቄታዊ መልካም ዕድል ነው ብለን እናምናለን፡፡

የማኅበራዊ አውታር በጋና እያደገ ነው፡፡ እና እኛ (ጋናን ጡመራ) ላለፉት አምስት ዓመታት በጋና የጡመራ መሪዎች ሆነናል፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ. ከUSAID፣ UKAID፣ EU እና DANIDA በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ማኅበራዊ አውታርን የጋናን ምርጫ ሽፋን ለመስጠት ተጠቅመንበታል፤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤዎችን በማስጨበጥ እና ፖለቲከኞችን እና ዜጎችን በማጎልበትም ጭምር፡፡ እ.ኤ.አ. 2013 የጋናን የመጀመሪያውን የጋናን የጦማሪዎች ሽልማትንም በማዘጋጀት ትልቅ ስኬት ተቀናጅተናል፡፡ የቡድኑ ሥራዎች በጆይ ኤፍ ኤምሲቲ ኤፍ ኤምማሻብልአልጄዚራ እና ቢቢሲ ሽፋን ማግኘት ችሏል፡፡

ብዙ መሥራት እና ብዙ ጋናውያን ወደማኅበራዊ አውታር በመውጣት ታሪካቸውን እንዲናገሩ እንፈልጋለን፡፡ ጦማሪዎች የሚገጥሟቸውን የበይነመረብ እና የኃይል ችግር መቅረፍ እንፈልጋለን፡፡ ለዚህም ከዜጎች ገንዘብ በመሰብሰብ የመገናኛ ስፍራ መመሥረት  ለጋራ ጡመራ እና የአገር ውስጥ መረጃዎችን ለመጻፍ የሚያስችለንን ዘመቻ ጀምረናል፡፡

ስፓይ ጋና፣ የተባለ የበይነመረብ የዜና ወኪል፣ የጋናን ጡመራ ሊቀመንበር ካጅሳ ሆልበርግ አዱን (@kajsaha) አጣቅሶ ጽፏል:-

የጋራ ጽሑፎችን በመጻፍ ሕልሞቻችንን እውን ለማድረግ ማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች መደራጀት ሲሆን ትርጉም ይሰጣል፡፡ ጋና የማኅበራዊ አውታር ወዳጆች ሊሰባሰቡ ዝግጁ ናቸው ብለን እናምናለን፤ ብዙ ታሪኮችን ለመፍጠርና መላው ዓለም ስለጋና ለመንገርም ቸኩለናል!

ሽልማት-አሸናፊው ጦማሪ ማክጆርዳን (@Macjordan) በጦማሩ ለማኅበራዊ አውታሩ ቋት ያለውን ድጋፍም ገልጧል:-

ጋናን ጡመራ የኢንዲዬጎጎ ዘመቻውን የማኅበራዊ አውታር ቋት ለጋና ጦማሪዎች እና የዜግነት ጋዜጠኞች በመፍጠር ዜጎች ማኅበራዊ አውታር አጠቃቀምን በመማር የአገራዊ መረጃዎችን በጡመራ የሚያበረክቱበትን መንገድ ለማመቻቸት መጀመሩን ስንገልጽ በደስታ ነው፡፡

ጋናን ጡመራ – የጋና የመጀመሪያውና ትልቁ የጦማሪዎችየዜግነት ጋዜጠኞች እና የማኅበራዊ አውታር ወዳጆች ስብስብ ሲሆን ሁሉም ሰዎች ጋር ለመድረስ እየጣረ እና ለዚህ መልካም ሥራ ድጋፍ እየሻተ ነው፡፡

የዚህ ስብስብ አካል በመሆኔ ክብርም፣ ደስታም ይሰማኛል፤ እናም ድጋፋችሁን በማንኛውም መንገድ አበረታታለሁ፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.