- Global Voices በአማርኛ - https://am.globalvoices.org -

ኢትዮጵያውያን #SomeoneTellSaudiArabia በሚል ስደተኞች ላይ የደረሰውን እርምጃ ተቃወሙ

Categories: መካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ, ከሰሃራ በታች, ሳውዲአረቢያ, ኢትዮጵያ, ሕግ, ሰብዓዊ መብቶች, ስደት እና ስደተኞች, ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን, ጉልበት

ጥቅምት 25፣ 2005 ሳኡዲ አረቢያ በሕገወጥ ስደተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች፡፡ ሳኡዲአረቢያ 7 ሚሊዮን የሚሆኑ የውጭ ዜጋ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን አስጠልላለች ተብሎ ይታመናል፡፡ የሳኡዲ አረቢያ መንግሥት ለሕገወጥ ስደተኞች የዘጠኝ ወር የእፎይታ (amnesty) ጊዜ በሚያዝያ ወር 2005 ሕጋዊ ዕውቅና እንዲያገኙ አሊያም አገሪቷን እንዲለቁ ሰጥቶ ነበር፡፡

ከሰሃራ በታች የምትገኘዋ የኢትዮጵያ ስደተኞች በዚህ የመንግሥት እርምጃ በፅኑ ከተቸገሩት ውስጥ ይመደባሉ፣ ይህም ዓመፅ እና ብጥብጥ አስከትሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በሳኡዲአረቢያ በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩትን ሰዎች በሳኡዲ ፖሊሶች አንድ ኢትዮጵያዊ መገደሉ ከተነገረ በኋላ [1]ወደአገራቸው መመለስ ጀምሯል፡፡

በተለያዩ የዜና እና የማኅበራዊ አውታሮች እንደተገለጸው ከሆነ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም የሳኡዲ አረቢያን ሕገወጥ ስደተኞችን የማስወጣት መብት ቢያምኑም [1] የኃይል አጠቃቀማቸው እና ሴቶች ላይ የደረሰው የመድፈር ድርጊትን አውግዘዋል፡፡

ከታች የሚታየው ቪዲዮ [2]አምሃሪክትዩብ [3] የተለጠፈ ሲሆን ከሳኡዲ አረቢያ የሕገወጥ ስደተኞችን መመለስ ያሳያል፡-

MoveOn.org የተባለ ድረገጽ ላይ ፊርማ የማሰባሰብ [4] ሥራ የተጀመረ ሲሆን ለተባበሩት መንግሥታት እና እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ላሉ የሰብኣዊ መብቶች ድርጅቶች በሳኡዲ አረቢያ ስለኢትዮጵያውያን ስደተኞች አያያዝ ለማሳወቅ ታቅዷል፡፡

ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በበይነመረብ #SomeoneTellSaudiArabia [5] የሚል ኃይለ ቃል በመጠቀም በሳኡዲ አረቢያ ያለውን የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አያያዝ አውግዘዋል፡፡

ማሕሌት (@Mahlet_S [6]) ስደተኞች ወንጀለኞች ሳይሆኑ ሥራ ፈላጊዎች መሆናቸውን አስታውሳለች፡-

አዲስ ስታንዳርደ  (@addisstandard [9]) የተሰኘ ወርሓዊ የኢትዮጵያ መጽሔት ደግሞ፡-

አንዳንዶች ደግሞ በኢትዮጵያ እና ኢስላም መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት አስታውሰዋል፡፡ ሐፍሳ መሐመድ (@hafsamohamed1 [11]) የሚከተለውን ጠቁሟል፡-

ካሊ (@KaliDaisyy) የጻፈው [15]:-

የሥነ ልቦና ባለሙያው አንቶኒዮ ሙላቱ (@AntonZfirst [17]) በነብዩ መሐመድ ስለኢትዮጵያ የተሰጠውን ምክር ማጣቀስ መርጧል፡-

 

በኢትዮጵያ እና በሙስሊሞች መካከል ያለው ግንኙነት የሚጀምረው ኢትዮጵያ በመካ ገዢዎች ተሰደው ለመጡት ሙስሊሞች ሠላማዊ መሸሸጊያ [20] ስትሰጥ ነው፡፡ ቢላል ኢብን አል ሐበሽ [21] ከቀደምት የመሐመድ ተከታዮች አንዱ እና የመጀመሪያ ሙኧዚን (የአዛን ዜማ አሰሚ) ሲሆን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡

 

በኢስላም አራተኛ ቅዱስ ከተማ [22] የምትባለዋ ሐረር ከተማ በኢትዮጵያ ነው የምትገኘው፤ 82 መስኪዶች፣ ሦስቱ ከ10ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ያሉ ሲሆን 102 መስገጃዎችም አሏት፡፡

 

ኢትዮጵያ ከዚህም በተጨማሪ በእስልምና ታሪክ የመጀመሪያው ሒጅራ [23] (የሙስሊሞች ስደት ከክስ ሽሽት) የተካሄደባት አገር ናት፡፡

በሌላ በኩል አኑፍ (@anoofesh [24]) ከሪያድ፣ ሳኡዲ አረቢያ የኢትዮጵያዊ ስደተኞች በሳኡዲ አረቢያ እና የያኔዎቹ የሳኡዲ አረቢያ እና ሙስሊም ስደተኞች በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ልዩነት በተመለከተ ልዩነቱን ተናግሯል፡-

መላክ መኮንን (@melak_m [27]) ያንን በተመለከተ፡-

የእንግሊዙ ሪስፔክት ፓርቲ ሊ ጃስፐር (@LeeJasper [29]) ደግሞ የኢትዮጵያውያን ስደተኞቹን ጉዳይ በእስራኤል ይዞታ ካሉት ፍልስጤማውያን ጋር አነጻጽራዋለች፡-

جبرتينهو (@iabj [34]) አስተያየት ደግሞ፡-

በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ የሰብኣዊ መብት ባለሙያው ይሄነው ዋለልኝ (@YeheneWalilegne [36]) የሳኡዲ አረቢያን ለተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብት ቆንስላ እጩ ሆና መቅረብ ተቃውሟል፡-

ሕዳር 3፣ 2006 ግን ሳኡዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ራሺያ እና ኩባ የሰብኣዊ መብት ቆንስላውን መቀመጫዎች ማሸነፍ ችለዋል [39]

አኑፍም ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ብሏል፡-