- Global Voices በአማርኛ - https://am.globalvoices.org -

ቪዲዮ፤ “ኖ ዉማን፣ ኖ ድራይቭ” ሳኡዲ አረቢያን አደመቃት

Categories: መካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ, ሳውዲአረቢያ, ሃይማኖት, ሐሳቦች, ሰብዓዊ መብቶች, ሴቶችና ስርዓተ ጾታ, አመጽ, አስተዳደር, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን, ዲጂታል አራማጅነት, ፌዝ

ዛሬ፣ ጥቅምት 16፣ 2006 ለሳኡዲ አራማጆች በኪንግደሙ ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የተጣለባቸው ማዕቀብ ላይ ለማመጽ የመረጡት ቀን [1] ነበር። የማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች በአገሪቷ ውስጥ መኪና እየነዱ ስለታዩት ሴቶች ቁጥር መጨመር [2] በስፋት እያወሩ ሳሉ፣ ተወዳጁ፣ የቦብ ማርሌይ “ኖ ዉማን፣ ኖ ክራይ” የተሰኘ ዜማ ሴቶችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸውን ለመንፈግ የወጣ የወግ አጥባቂ ስርዓተ ፆታ ሕግን እና ሐሰተኛ የሳይንሳዊ ማብራሪያ [3]ውን በሞገቱ ቆራጥ ሴቶች ድምፅ ድጋፍ ተቀይሮ በብርሃን ፍጥነት ሲሰራጭ ነበር፤