በጃፓን ሦስት ጎንዮሽ (3D) የቡና ጥበብ

ከትኩስ መጠጦች ሁሉ አረንጓዴ ሻይ የመጀመሪያ ተመራጭ መጠጥ በሆነባት ምድር፣ በወተት አረፋ በስሪ ዲ ጥበብ የሚሠራ የቡና ጥበብ ብዙዎችን ልብ ማርኳል፡፡

በጃፓን  ካፍቴሪያ ጎብኚዎች  በማኅበራዊ ድረገጽ በሚታዩ የማኪያቶ ፎቶግራፎች በመማለል የሚጠጡት ማኪያቶ በምስሎች አሸብርቆ በተለያዩ ምስሎች ታጅቦ እንዲቀርብላቸው ይጠይቃሉ፡፡

ጃፓን ለቡና እንግዳ አገር አይደለችም፡፡ መላው የጃፓን ቡና ማኅበር እንዳቀረበው ሪፖርት ጃፓን በዓለም ቡና ወደ አገራቸው ከሚያስገቡ አገሮች በተጠቃሚነት የሦስተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

በ2010 የጃፓኑ ሃሩና ሙራያማ ዓለም አቀፍ የማኪያቶ ጥበብ ሻምፒዮና አሸናፊ ሆኗል፡፡

በውኃ በተከበችው ይህች አገር የተለያዩ ጠፍጣፋ የማኪያቶ ቅርፆች የተለመደ ነው፡፡ በቲውተር በተደረገ የማኪያቶ ጥበብን[ja] ፍለጋ ግን በርካታ ፎቶዎች የተገኙ ሲሆን የተለየ ጥበብ ያላችው በልብ ቅርፅ፣ በቅጠል ቅርፅ፣ ድብ ቅርፅ (ቴዲ ቤር)፣ ታዋቂ የካርቱን ፊልም ተዋኒያን እንዲሁም የኢንተርኔት ምልክቶች ሳይቀሩ ተገኝተዋል፡፡

በቶኪዮ ዓለም አቀፍ ሄንዳ ኤርፖርት ውስጥ የሚገኝ የቡና መሸጫ በታዋቂው ዮጂያ ኮስሞቲክስ ኩባንያ  ዲዛይን የተደረገ የጃፓን ሴት ምስል ያለበት  ካፑችኖም ሳይቀር አቅርቧል[ja]፡፡

የዩ ቲዩብ ተጠቃሚው ኖዋቱ ሱጊ እንዴት አድርጎ በቡና እና በቸኮሌት አማካኝነት ማኪያ ላይ ምስሎችን መስራት እንደቻለ ያብራራል፡፡

አዲስ ደረጃ መድረስ

ነገር ግን አንዳንድ ባሬስታዎች የዚህ የቡና ላይ ምስል የመፍጠር ችሎታ ክስተት በወተት አረፋ አማካኝነት በሶስት ጎን (ስሪ ዲ) እይታና ቅራፅ ወደ አዲስ ደረጃ አድርሰውታል፡፡

3D latte art by twitter user @george_10g: a cat is looking at golden fish. Image captured on twitter

ስሪ ዲ ማኪያቶ ጥበብ በቲውተር ተጠቃሚ @george_10g “ድመቷ ወርቃማ ዓሣዎችን ስትመለከት”

ካዙኪ ያማሞቶ (@george_10g) በማኪያቶ ላይ ምሰል በመስራት ጥበብ ሊቅ፣ ይህንን ምስል በቲውተር ገፁ ያስቀመጠ ሲሆን በራሱ ጦማር ላይ በኦሳካ ቤላጊአን ቢራ ቤት እንደሚሰራ ፅፏል፡፡ የማኪያቶ ጥበቦቹን  “የትርፍ ጊዜ ካፕችኑ” እያለ ይጠራቸዋል፡፡ በድብርት አሊያም በትርፍ ጊዜ የሚሰሩ ቢሆኑም ግን ትልቅ ችሎታ እና የስራ ፍቅር የሚጠይቁ ናቸው ይላል፡፡ በአንድ ወቅት ከዚህ በፊት ማኪያቶ ላይ የሰራቸውን ምስሎች ሰብስቦ በቲውተር ገፁ ላይ ለጥፏቸው ነበር፡

@george_10g:最近気づいた怖いこと。去年から始めて1000杯くらい描いているけど作品も描いた時期も飲んだ人も覚えてる。

@george_10g:በማኪያቶ ላይ ምስል መስራት የጀመርኩት በ2011 ነው፡፡ በደፈናው እስከ 2012 ድረስ በማኪያቶ ላይ ምስል ሰርቼ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን አስተናግጃለሁ፡፡ ነገርግን በሚገርም ሁኔታ መቼ እና ምን እንዲሁም ለማን የምስል ማኪያቶዎቹን እንደሰራሀትና እንዳስተናገድኩ አስታውሳለሁ፡፡ ነገሩ ትንሽ የማይገባ ነገር ነው፡፡

የቲውተር ተጠቃሚ  @petakopetako አድናቆቱን በመስጠት እና ሥራዎቹ ልዩ መሆናቸውን በመናገር ምላሽ[ja] ሰጥቶታል፡

@petakopetako: じょーじさんこんにちは。私は人物写真を撮るのが好きですが人の顔を覚えるのは超苦手です。が、写真を撮らせてもらうと場所や会話がすぐに思い出せます。思い入れがあるからでしょうかね。

@petakopetako ፡ ፎቶ ማንሳት እወዳለሁ፡፡ በመደበኛ ሁኔታ የሰዎችን ፊት አይቼ የት እንደማውቃቸው ማስታወስ አልችልም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ፎቶ ካነሳኃቸው፣ ፎቶውን የት እንዳነሳኃቸው፣ ፎቶውን  ሲነሱ ምን እያወሩ እንደነበር ማስታወስ እችላላሁ፡፡ ምናልባት ሰዎች የማስታወስ ችሎታቸው የተሻለ የሚሆነው የሚወዱትን ስራ በሚሰሩበት ወቅት ይሆናል፡፡

የማኅበራዊ ድረ ገፆች ተፅእኖ

 

በጃፓን የሚገኙ የካፍቴሪያ ባለቤቶችና ባሬስታዎች ባለሦስት ጎን ምስል(ስሪ ዲ) እይታ ያላቸውን የማኪያቶ ፎቶግራፎች ሜኑ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች ላይ ጫኑ፡፡ እነዚህ ምስሎች በከፍተኛ ሁኔታ ሲሰራጩ አፋታም ሳይቆይ የአገሪቱን መፅሔቶች፣ ሬዲዮኖችና ቴሌቭዥኖች ቀልብ ለመግዛት ችለዋል፡፡

በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች እና ማህበራዊ ገፆች የስሪ ዲ ማኪያቶ መሰራጨት ደንበኛ ለማግኘት ለሚሯሯጡ የቡና መሸጫ ቤት ባለቤቶች የተለያ አዳዲስ ተጠቃሚዎች እንዲመጡ መንገድ ከፍቶላቸዋል፡፡ በሺዞካ ክልል የካፌ ባር ጂሃን ባለቤት በጦማሩ ላይ ስለ ፌስቡክ ተፅእኖ ሲፅፍ [ja]:

お客様のリクエストがきっかけで始めた3Dラテアート。 お遊びのつもりでfecebookにアップしたその日、物凄い数の『いいね!』とシェアにビックリしました。
その拡散がきっかけで取材の問い合わせが幾つかありました。 中でも東京のTVメディアからの出演依頼には戸惑いました。(*^_^*)

ባለሦስት ጎን ምስል (ስሪ ዲ) ማኪያቶ መስራትና መሸጥ የጀመርኩት የረጅም ጊዜ ደንበኛዬ እንድሰራለት ከጠየቀኝ በኃላ ነው፡፡ ከዚያም ፎቶ ግራፍ አንስቼ በፌስቡክ ገፄ እንደው እንደ ቀልድ አስቀመጥኩት፣ በኃላ ፎቶዎቹንየወደዱ በርካታ ሰዎች ቁጥር ሳይ በጣም ነው የተደነቅኩት፡፡ ምስሎቹን ሰዎች በራሳቸው መንገድ ሲቀባበሏቸው የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የኔን ቡና ቤት በተመለከተ የዜና ሽፋን መስጠት እንደሚፈልጉ ጠየቁኝ ፡፡ በቶኪዮ ቴሌቭዥን እንድቀርብ ጥያቄ ሲቀርብልኝ ግራ ገብቶኝ ነበር፡፡

facebook photo by caffe.bar.jihan. A cat is taking a bath in espresso coffee

Facebook photo by caffe.bar.jihan. A cat is taking a bath in espresso coffee.

እንዲህም ጽፏል [ja]:

このニャン子は、作るのにとっても時間が掛かりますので混雑時はお受け出来ないのが目下の悩みです。
平日の18時からでしたら比較的にお時間が取れると思いますので、どうしても3Dラテアートを…というお客様はこの時間帯のリクエストをお願いいたします。

በጥቁር ቡና ገንዳ ውስጥ የተዘፈዘፈችውን ድመት ማኪያቶ ለመስራት ብዙ ሰዓት ይወስዳል፡፡ በካፍቴሪያችን ውስጥ ብዙ ተስተናጋጅ ደንበኞች እያሉ ይህንን ለመስራት ትዕዛዝ መውስድ አልችልም፡፡ ይህንን ነገር ምን ላድርገው ብዬ ከራሴ ጋር ብዙ ተሟግቻለሁ፡፡ ቢያንስ ካፌያችን ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ በስራ ቀናት ቀዝቀዝ ይላል ስለዚህ እርሶ ካፍቴሪያችንን የሚጎበኙት ለስሪ ዲ ማኪያቶ ብለው ከሆነ በዚህ ሰዓት ቢመጡ ይመረጣል፡፡

ይህ ጽሑፍ በመጀመሪያ የተፃፈው በአያኮ ዮኮታ ነው፡፡ ኬኢኮ ታናካ አርዕቶ ሰርታለች፡፡ ኤል ፊኒች በድጋሚ አርዕቶ አድረጋለች፡፡

@petakopetako ፡ ፎቶ ማንሳት እወዳለሁ፡፡ በመደበኛ ሁኔታ የሰዎችን ፊት አይቼ የት እንደማውቃቸው ማስታወስ አልችልም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ፎቶ ካነሳኃቸው፣ ፎቶውን የት እንዳነሳኃቸው፣ ፎቶውን  ሲነሱ ምን እያወሩ እንደነበር ማስታወስ እችላላሁ፡፡ ምናልባት ሰዎች የማስታወስ ችሎታቸው የተሻለ የሚሆነው የሚወዱትን ስራ በሚሰሩበት ወቅት ይሆናል፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.