ስለፍቅርና የፍቅር ጨዋታ ከአንጎላ

ወጣቷ ሮዚ አልቬስ አንጎላዊ ጦማሪ (cronista) ናት፡፡ መኖሪያዋን ያደረገችው በአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ውስጥ ነው፡፡ “cronista” ማለት በፖርቱጋል ቋንቋ መጦመር የሚለውን ቃል ተስተካካይ ትርጉም የሚሰጥ ሲሆን – ፅሁፎቹ ባብዛኛ ጊዜ በጋዜጣ  የሚታተሙ ታሪኮች  አንዳንዴ እውነተኛ ተሪኮች  ሌላ ጊዜ ደግሞ የፈጠራ ልብ ወለዶች ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ የራስ ችሎታን በአጭሩ ያሳያሉ፡፡

Sweet Cliché” በተሰኘው ጦማሯ አልቬስ አጫጫር ታሪኮችን የምትፅፍ ሲሆን፣ በአብዛኛው ስለፍቅር እና ስለፍቅር ጥብቅ ግንኙነቶች ትፅፋለች ( Bolgspot የፅሑፎቿ እንባቢዎች እድሜቸው ለፅሑፉ የሚመጥን ስለመሆኑ ያስጠነቅቃል)፡፡ከዚህ በታች ሰሞኑን በጣም አነጋጋሪ የነበረው ፅሑፏ ቀርቧል፡፡ “I killed my love” (“ፍቅሬን ገደልኩት”):-

Foi naquela noite fria e chuvosa, na entrada de casa. Com apenas um golpe no coração, cruel e sem dó, matei o meu amor. Matei aquele que me causava prazer e dor. Senti ele a morrer. Ele sangrava, aquele pedaço vermelho perdia a cor na medida que o sangue escorria…

Foi frio, cauteloso, vi ele decair-se lentamente e, um mar de sangue se formava. Tudo parecia girar. Pensei nos bons momentos que passamos juntos, nos grandes prazeres que ele me proporcionou, e não tardou, veio a imagem do dia em que ele me traiu, a rodar na minha cabeça. A senhora que passava às pressas com um saco plástico na cabeça para se abrigar da chuva, não pareceu se importar com o que vira.

በዚያ ቀዝቃዛና ዝናባማ ምሽት፣ ወደ ቤቱ መግቢያ በር ላይ፡፡ እንዴ ብቻ ልቡ ላይ፣ በጭካኔ እና ርህራሄ በጎደለው መንፈስ ፣ ለደስታዬና ለጉዳቴ ስል ፍቅሬን ገደልኩት፡፡ ፍቅሬ ሲሞት ተሰማኝ- ደም፣ ቀዩ እብጠት እቀነሰ ሲገረጣ  ደሙ እየተንዠቀዠ ፈሰሰ…

ቀዝቃዛ ነበር፣ ፍቅሬ ቀስ እያለ ወደ መሬት ሲወድቅ የደም ባህር ሰራ፡፡ ሁለም ነገር ጭው ያለ መሰለ፣ አብረን ያሳለፍናቸው እነዛ መልካም ቀናቶችን አሰብኳቸው ፣ፍቅሬ ያደለኝን የደስታ ቀናቶች፣ ግን ደግሞ ወዲያው የፍቅሬ ክህደት ጭንቅላቴን ተቆጣጠረው፡፡

ዝናብ ለመከላከል ጭንቅላቷ ላይ ፌስታል አድርጋ ጠደፍ ጠደፍ እያለች የምትራመደው ሴት ባየችው ነገር አንዳችም የተረበሽች አትመስልም፡፡

ቁጥራቸው እያደገ በመጣው ወጣት አንጎላውያን ጦማሪዎች ዘንድ የ21 አመቷ አልቬስ ልዩ ስፍራ እንደያዘች ትናገራለች፣ ምንም እንኳን እውቅናዋ ከአገሯ  ይልቅ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ቢሆንም፡፡ግንኝነቱ ውስን እና አስተማማኝ ባልሆነው 3ጂ ኢንተርኔት ግንኙነት አማካኝነት  በቅርቡ አልቬስን ቃለመጠይቅ አድርገንላት ነበር- ይበልጥ ለማወቅ

She has been blogging for three years, and has built up quite an online following in spite of her Twitter biography (@rosie_alves), which reads "Don't follow me, I'm lost".

ሮዚ ላለፉት ሶስት አመታት ስትጦምር በቆየችባቸው ጌዜያቶች  የቲውተር መለያዋ (@rosie_alves), “አትከተሉኝ፣ጠፍቻለሁ”

GV: የምትፅፊበትን የአፃፃፍ ስልት እንዴት ትገልጪዋለሽ?

የትረካ ስልት እወዳለሁ፣ በቃ ምልልስ የተሞሉ አይነቶቹን:: አጫጫር ታሪኮችን በአጭሩ ለመቋጨት ያስችላሉ::  በየዕለቱ ለሚፈፅሙ የየቀን ሁኔታዎችን ፣ አዘቦቶች እና የተለመዱ ክስተቶችን ለመፃፍ፡፡ አንዱን ከአንዱ መደበላላቅ እና እዲስ ነገር መፍጠርም እወዳለሁ፡፡

GV: መጦመር መቼ ነበር የጀመርሽው ? ለምን ትፅፊያለሽ?

ለመጦመር የወሰንኩት በ2010 ነው፡፡ መፃፍ ያረጋጋኛል፡፡ ሁሌም በፃፍኩ ቁጥር ከትከሻዬ ላይ ሽክም እንዳወረድኩ ይሰማኛል፡፡ ከምላሴም( ሳበሳ)፡፡ ለኔ መፃፍ ፈውስ ነው፡፡

GV: ፍቅር፣ የፍቅር እና ግብረ ስጋ ግንኝነት በተመለከተ ነው የምትፅፊው፡፡ እነዚህ ርዕሶች በአንጎላውያን ማህበረሰብ ዘንድ እንዴት ይታያሉ? ነውር አይደሉም? በአንጎላ ልቅ ወሲብን የተመለከቱ ስነፅሁፎችስ አሉ?

የአንጎላ ማህበረሰብ እኔ ስለማነሳቸው ሃሳቦች የሚይዙት አቋም ወግ አጥባቂ የሚባል አይነት ነው(ከስፔን በመቀጠል አንጎላ የኔን ጦማር በጥቂቱ ከሚመለከቱ አገሮች ተርታ መመደቧ ይህንን እውነት ያረጋግጣል) በአንጎላ ብዙ ነውር ነገሮች አሉ፡፡ ጊዜው ጥንት ቢሆን ኖሮ የወግ አጥባቂነት ጥያቄ ነው እንል ነበር፣ ነገር ግን በማህበረሰባችን ውሰጥ በርካታ ለውጦች በሚካሄዱበት በአሁኑ ወቅት ነውር ለሚባለው ነገር ምንም ቦታ የለኝም፡፡

በአንጎላ ልቅ ወሲብን በተመለከተ የተፃፉ ስነፅሑፎችን አላውቅም(የተፃፉእና ለንባብ የበቁ) ለዚህ ሃሳብ ቅርብ የሆነ  ያነበብኩት Paula Tavares ‘Ritos de Passagem’ (Rites of Passage) የተሰኛ ስራ ነው፡፡ ሰዎች የአንጎላ ማህበረሰብ ለእንደኔ አይነት ፅሁፎች ዝግጁ አይደልም ሲሉ በተደጋጋሚ እሰማለሁ፡፡ እውነት ነው አንጎላዊያን ለእንደኔ አይነት ፅሑፎ ዝግጁ አይደሉም፣ ነገሮች በሚሄዱበት የአካሄድ ፍጥነት ከሆነ  ደግሞ መቼም ዝግጁ አይሆኑም. . .

GV: ወጣትሴት ሆኖ በሉዋንዳ መኖር እንዴት እንደሆነ ትነግሪናለሽ?

ቀላል ሆኖ አያውቅም፡፡ እዚህ ከፍ ያለ ማግለል  እና ለሴት ልጅ ክብር አለመስጠት አለ፡፡ በመርህ ደረጃ ነፃ የወጣን ግን ማህበረሰቡ በዘልምድ ያስቀመጠልንን ሃለፊነት እንድንፈፅም የሚጠበቅብን ነፃ ያልወጣን ሴቶች ነን፡፡

GV: ስለልጅነት ትዝታሽ አጫውቺን?

በአራት አመት እድሜዬ አባቴ ሚሰጠኝን የተረት መፅሐፎች ማንበብ በጣም እፈልግ ነበር፡፡አባቴ የቤት ውስጥ አስተማሪጋር ወስዶኝ ገና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከመግባቴ በፊት ማንበብና መፃፍ ቻልኩ፡፡ በጀርባዬ የደብተር ቦረርሳ ተሸክሜ ሁሌም አስተማሪዬ ጋር እመላለስ ነበር፣ እስካሁንም ድረስ እነዚህ የልጅነት ጣፍጭ የምንግዜም ትዝታዎቼ ናቸው፡፡

GV: በአንጎላ ያሉ የአንቺ ዘመን ትውልዶችን እንዴት ትገልጪያቸዋለሽ?

የኔ ዘመነኞች በታላቅ ለውጥ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ የሚችል ትውልድ ነው፣ህልም እና እምቅ ችሎታ ያላቸው፡፡ መጥፎው ነገር እምቅ ችሎታ እንዳላቸው የተረዱት ጥቂቶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የኔ ትውልድ እርስ በእርሱ ተወዳዳሪ ነው ፡፡ ግን በዙሪያችን ያሉ ስዎች በአንድ አላማ ስር ሲሰባሰቡ አናይም፡፡ጥቂቶች ብቻ ናቸው ‘ህብረት’ እና ‘በአንድ አላማ መትጋት’ የሚሉትን ቃላት ፍቺ የሚያውቁ፡፡ ለመረጃ ቅርቦች ሆነን ሳለ ድርጊቶቻችን ግን በድንጋይ ዘመን እንደሚኖር ነው፡፡ በአንጎላ የተለመደ አባባል አለ “ወጣት ሆኖ በጭፈራ ቤት የማይጨፍር ወጣት አይደለም” የሚል፡፡ ወጣቶች ዛሬ ዛሬ መጨፈር ብቻ ነው የሚሹት ፣እርግጥ ነው ሁሉንም ወጣቶች በደፈናው  በአንድ ማጠቃለሌ አይደለም፡፡

GV: በአንጎላ ባሉ የጦማሪያን ምድብ ስር ራስሽን ትመድቢያለሽ?

እንደዛ ነው የማስበው፡፡የበይነመረብ ጓደኞች አሉኝ፡፡ የአንጎላ ጦማሪያን “Blogueiros Angolanos” (“Angolan Bloggers”) የተባለ ፌስቡክ ገፅ እንደተከፈተ የአባላቱ ቁጥር ወዲያው ጨመረ፡፡ገፁን እርስ በእርሳችን ለመደጋገፍ እንዲሁም ስራዎቻችንን ለበለጠ አንባቢያን ለማዳረስ እንጠቀምበታለን፡፡ሃሳቦችን ልምዶችን የምንገበያይበት አይነተኛ መንገድ ነው፡፡ ከአንጎላ ብቻም ሳይሆን ተጨማሪ በተለያዩ አገሮች በመላው አለም  በይነ መረብ ጓደኞችአሉኝ፡፡

Image from sweetclichee's Instagram: "- Waiter, a beer please.  - We don't have any. - Do you have Disappointment? I'll take a double. - We do, he's seated there with a cigarette in his hand. - That man there? What should I call him? - Call him love."

“- አስተናጋጅ እባክህን ቢራ?

- ምንን የለንም፡፡

-ብስጭትስ አለህ? ካለህ ሁለት ስጠኝ፡፡

- አለን፣በእጁ ሲጋራ ይዞ እዛጋ ተቀምጧል፡፡

- እዛጋ ያለው ሰውዬ? ማን ብዬ ልጥራው?

ፍቅር ብለሽ ጥሪው ”

GV: ስለአፃፃፍ ሂደትሽ ንገሪን? ስትፅፊ የሚያጋጥምሽ ችግሮችም ምንድን ናቸው?

በአጠቃላይ የሞባይል ስልኬን አውጥቼ መፃፍ እጀምራለሁ፣ ከሁለት ስዓት በሚያንስ ጊዜ ውስጥ እጨርሳለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንድ ፅሑፍ ለማቀናበር ሁለት ሳምንት የፈጅብኛል፣ ያኔ ትክት ነው የሚያደርገኝ፡፡ ብቸኛው ባይሆንም አንዱና ዋንኛው ችግሬ አንባቢዎቼ በፁሑፌ ውስጥ ራሳቸውን እንዲያገኙ ማድረጉ ላይ ነው፡፡ይህንንም ችግሬን በሚገባ እንደተወጣሁት በሚደርሱኝ የአንባቢዎቼ ምላሽ ለማወቅ ችያለሁ፡፡

GV: አንባቢዎችሽ ማን ማን እንደሆኑ ታውቂያለሽ? ስለፅሑፎችስ ሰዎች ምን ይላሉ?

ብዙ ሰዎች ፅሑፌን ያነባሉ ማለት እችላለሁ፡፡ ይህንንም ስል በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በተለያዩ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ስዎችን ማለቴ ነው፡፡ እንግዳ ነገር ነው በአለማችን  ከሚገኙ ሰዎች በስታትስቲክሱ መሰረት በርካታ አንባቢዎቼ የሚገኙት በአሜሪካን ነው፡፡በጉግል ትርጉም  አማካኝነት በመጠቀም ፅሁፌን እንዳነበቡ የገለፁልኝም አሉ፡፡ አብዛኞቹ አንባቢዎቼ በርትቼ እንድቀጥልና እንድጠነክር ማበረታቻ ሃሳብ ይሰጡኛል፡፡ በሌላ በኩል በፍፁም ፅሑፌን የማይወዱና በተሳሳተ መንገድ የሚተረጉሙትም አሉ፡፡  ስለምፅፈው ፅሑፋ ጥንቃቄ እንድወስድ ማስጠንቀቂያ የሰጠኝ  አንባቢም አለ፡፡

GV: የወደፊት ትልሞችሽ ምን ምን ናቸው?

ወደፊት ብዙ ህልሞች ያሉኝ ሰው ነኝ፡፡ ለወደፊት ማድረግ የምፈልጋቸው ትልሞቼን መዘርዘር ከጀመርኩ ዛሬ የምጨርስ አይመስለኝም ነገር ግን በጋዜጣ አሊያም በመፅሔት አምደኛ ሆኖ መፃፍ አንዱ ነው፡፡ አሪፍ ይሆናል፡፡

2 አስተያየቶች

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.