- Global Voices በአማርኛ - https://am.globalvoices.org -

የግራዚያኒ ኀውልት ግንባታን የተቃወሙትን መንግሥት መቃወሙ የድርዜጎችን አነጋገረ

Categories: ሕግ, ታሪክ, አመጽ, አስተዳደር, ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን

መጋቢት 8/2005 ሰማያዊ ፓርቲ ከባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር ጋር በመሆን የግራዚያኒን ኀውልት ግንባታ እንዲቃወሙ ኢትዮጵያውያንን ለሰልፍ ጠርቶ ነበር፡፡ ጄኔራል ግራዚያኒ ኢጣልያ ኢትዮጵያን ለአምስት ዓመታት ያክል በወረረችበት ጊዜ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዲጨፈጨፉ ምክንያት የሆነ ሰው ነው፡፡ በተለይም የካቲት 12/1937….. የተገደሉት ሰማዕታት ኀውልት ስድስት ኪሎ በሚባለው አካባቢ ይገኛል፡፡ ሰልፈኞቹ ከዚያ ተነስተው ወደ ጣልያን ኤምባሲ ማምራት ሲጀምሩ ያልተጠበቀ ተቃውሞ ከመንግሥት አካላት ገጠማቸው፡፡ በቦታው 43 ያክል [1] ሰልፈኞች ታፍሰው ለእስር መዳረጋቸው አነጋጋሪ ዜና ለመሆን በቅቷል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም [2] በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንዲህ በማለት [3] አሰፈሩ፡-graziani

የዛሬው ጉድ ነው፤ በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እየተሠራ መሆኑን ለመቃወም የተለያዩ አገር ወዳድ ወጣቶች ከስድስት ኪሎ ወደኢጣልያ ኤምባሲ ሰልፍ ለማድረግ ጠርተው ነበር፤ ግራዚያኒ በየካቲት አሥራ ሁለት በቦምብ ከቆሰለ በኋላ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስጨፈጨፈ አረመኔ ፋሺስት ነበር፤ ለዚህ ሰው ኢጣልያኖች ሐውልት መሥራታቸው የዛሬውን የኢትዮጵያ ትውልድ መናቅ ብቻ ሳይሆን ከኢጣልያ ጋር የተዋደቁትን ኢትዮጵያውያን ማዋረድ ነው፤ ስለዚህ ዛሬ መጋቢት 8/2005 ተቃውሞ ለማሳየት ታቅዶ ነበር፤ ፖሊሶች ሰልፉ እንዳይደረግ መከልከል ይችሉ ነበር፤ የተሰበሰቡትን በሰላማዊ መንገድ መበተን ይቻል ነበር፤ ፖሊሶች የመረጡት እየያዙ ማሰርን ሆነ፤ በአሁኑ ጊዜ ብዙ ወጣቶች ሴቶችና ወንዶች በየፖሊስ ጣቢያዎች ታስረዋል፤ ዶር. ያዕቆብ ኃይለ ማርያምንም ይዘውታል፤ በዓይኔ ባላየው ለማመን ትንሽ ያስቸግረኝ ነበር፤ እንዲያውም የተያዙትን ለመጠየቅ ሄጄ የፖሊስ ጣቢያው በር ላይ ያገኘሁትን ነጭ ለባሽ ዛሬ የታሰሩ ሰዎች እዚህ መጥተዋል ወይ ብዬ ብጠይቀው ‹‹ምናባክ አውቅልሃለሁ፣ ግባና ጠይቅ፤›› አለኝ፤ በሩ ላይ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ‹‹አለቆቹ ስለሌሉ በኋላ ተመለስ›› ለማናቸውም እስረኞቹ በረንዳ ላይ ታጉረው አየኋቸው፤ እኔ ይህ የጤንነት አይመስለኝም!

ማስተዋል ደሳለው [4] የተባለ የፌስቡክ ተጠቃሚም የመንግሥት እርምጃ አንድምታዎችን በዘረዘረበት ጽሑፉ ላይ ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት መሳቡን የጻፈው የጓደኞቹን አስተያየት (ሩዶልፎ ግራዝያኒ ለኢህአዴግ ምኑ ነው? [5] ባለው ጽሑፉ ላይ) በማጣቀስ ነው፡-

…እስኪ ፌስቡክ ላይ ካነበብኳቸው አስተያየቶች ሦስቱን ላካፍላችሁና ወደተነሳሁበት ቁም ነገር ልመለስ:: “I think it is just to say fascist invaded Ethiopia three times”. (“ፋሽስት ኢትዮጵያን የወረረው ሦስቴ ነዉ ማለት ይቻላል” – ማሕሌት “ለኢትዮጵያውያን ግራዚያኒን መቃወም የጋራ አገራዊ አጀንዳቸው ካልሆነ፤ ሌላ ምን አጀንዳ ነው የሚያገናኛቸው”) – ደረጀ “This is really very amazing. Ethiopians in Italy staged a peaceful demonstration in Italy and no problem. But Ethiopians can not peacefully protest the erection of a statue for Graziani and brutalized by their fellow country men (Ethiopian police). What kind of government is this? Such an act of ignorance and brutality can not be acceptable by standard. Shameful. Lenegeru shame yett yawqalu.” (“በጣም የሚገርም ነዉ በጣልያን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እንክዋን ጣልያን ዉስጥ ያለምንም ችግር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል ነገር ግን ኢትዮጵያዉያን ለግራዝያኒ የቆመዉን ሃዉልት በሐገራቸዉ በሰላማዊ ሰልፍ እንዳይቃወሙ በሐገራቸዉ ሰወች ( በኢትዮጵያ ፖሊሶች) የጭካኔ እርምጃ ተወሰደባቸዉ:: በየትኛዉም መመዘኛ ይህ ድንቁርናና ጭካኔ ተቀባይነት አይኖረዉም:: አሳፋሪ! ለነገሩ ሀፍረት የት ያዉቃሉ!”) – ኤፍሬም እነዚህ እና ሌሎች ጥያቄዎች የተሰጡ ሲሆን አንዳንዶችም ኢሕአዴግ ሰልፉን የከለከለው ከራሱ ፋሽስታዊ ባሕሪ በመነሳት ነው ሲሉ ጽፈዋል::…

ሰልፈኞቹ መበተናቸው እና መታሰራቸው ተገቢ ነው በሚል ለመከራከር የሞከረው ዳንኤል ብርሃነ [6]የሚከተለውን [7] [en] ብሏል፡-

Today, they [oppositions] came out of nowhere and wanted to conduct demonstration on the matter. Apparently, they didn't fulfill legal requirements, thus the police put the situation under control and detained some of them for investigation (probably released by now).

… ዛሬ [ተቃዋሚዎች] ከየት እንደመጡ ሳይታወቅ በጉዳዩ ዙሪያ ሰልፍ ማድረግ ፈለጉ፡፡ በግልጽ እንደሚታወቀው፣ የሕግ ግዴታዎችን አለሟሉም ነበር፤ ስለዚህ ፖሊስ ሁኔታውን በቁጥጥር ስር አዋለውና ጥቂቶቹን ለምርመራ ወደማረፊያ ቤት ወሰዳቸው (ምናልባትም አሁን ይለቀቃሉ፡፡)…

ዳዊት ተፈራ [8] ደግሞ የአንድ የተፈረደበት ወንጀለኛ ጉዳይ ተበዳዮቹን ኢትዮጵያውያን ለሁለት ከፍሎ ሊያሟግተን ቀርቶ እውነተኞቹ ጣሊያኖች ራሱ የተቃወሙት ጉዳይ እንደሆነ እንዲህ በማለት [9] [en] አስፍሯል፡፡

Rodolfo Graziani was a convicted war criminal. Opening of a memorial to him last August in his birth-town has been a painful memory. The insult to us, through this avowed disrespect to humanity by unrepentantly honoring the ‘butcher’, was vehemently condemned by those Italians who feel sense of responsibility for the damages caused by fascism, let alone us – the victims of the massacre. It should not stir any divisive debate among us (Ethiopians) about airing our voices condemning this spiteful act. It's saddening to hear Ethiopian police arrested protesters by cracking down a demonstration organized to condemn opening of Graziani's memorial. Where are we heading?

ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተፈረደበት የጦር ወንጀለኛ ነበር፡፡ ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ በትውልድ ከተማው መታሰቢያ የተከፈተለት መሆኑ የሚያም ትዝታ ነው፡፡ ለኛ ስድብ የሚሆነው፣ የዘር ጭፍጨፋው ሰለባ የሆንነው እኛ ቀርቶ – በፋሺዝም ለደረሰው ጥፋት የኃላፊነት ስሜት የሚሰማቸው ጣልያናውያን ሳይቀሩ የተቃወሙትን የዚህን ስጋበል ሰው ክብር መደገፋቸው ነው፡፡ በእኛ (በኢትዮጵያውያን) መካከል ስለዚህ የተረገመ ተግባር ከማውገዝ የሚከፋፍለን ነገር መኖር የለበትም፡፡ የኢትዮጵያ ፖሊስ የግራዚያኒን መታሰቢያ ኀውልት ሊቃወሙ የወጡ ሰልፈኞችን መበተኑ የሚያሳዝን ነው፡፡ ወደየት እየሄድን ነው?

ስደተኛው ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ [10]ም በበኩሉ እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች በተከሰቱ ቁጥር ሰዎች እንዳዲስ የሚገረሙ መሆኑን በአግራሞት እንዲህ [11] ጽፏል፡-

ሰዎች ስለመንግሥትና ስለሥራው አንድ ጭቆና ሲናገሩ “አሁንስ አበዙት” ወይም “የዛሬውስ በዛ” በማለት ሲደነቁ መልሶ ይደንቀኛል። ልክ ከዚህ በፊት ከዚህ የባሰ ግፍ ተፈጽሞ የማያውቅ ወይም ገዢዎቻችን ድንገት ከጥሩነት ወደመጥፎነት የተቀየሩ ይመስል….። መገረምና መደነቅ የፖለቲካ ብሂል ሲሆን ማየት ያሳዝናል። ተገርሞና ተደንቆ ያልጨረሰ ሰው የያዘውን ጉዳይ በስክነት ወደ መመርምር ለመሔድ ጊዜ ይፈጅበታል። በጭቆና የደነዘዘ ማኅበረሰብም እንዲሁ ነው፤ እያንዳንዱ የአፈናና የግፍ ተግባር እንደ አዲስ ይገርመዋል፤ ይደንቀዋል። ጭቆናው የገዢዎቹ ባህሪይ ሳይሆን ድንገት የተፈጸመ የሚያስመስል ቅዠት ብጤ የሚከጅለውም አይጠፋም። በአንዱ ግፍ ተገርሞ ሳይጨርስ፣ በሌላ የጭቆና ዜና ድንቅ ይጠመዳል….ሲገረም፣ ሲደነቅ ይኖራል። ስብሰባ ተከለከለ፣ መገረም። የግራዚያኒን የመታሰቢያ ሃውልት ለመቃወም የወጡ ሰዎች ታሰሩ፣ መደነቅ። ጋዜጣ ተዘጋ፣ ጋዜጠኛ ተከሰሰ..እንደገና መገረም። ዜጎች በብሔር ማንነታቸው ተጠቃሚ ሆኑ ወይም ተጎዱ…በየቀኑ እንደአዲስ መደነቅ። ታሰሩ፣ ተሰደዱ፣ ተፈናቀሉ፣ ተበደሉ፣….በየቀኑ፣ በእያንዳንዱ የጭቆና ዜና ነገሩ ሁሉ ከዚህ በፊት ሆኖ የማያውቅ ይመስል፤ ወይም አዲስ የተባለው የጭቆና ዜና ሊሆን እንደሚቸል አስቀድሞ በቂ ምልክት እንዳልተሰጠን፣ ጭቆናው የማይቀር መሆኑ እንዳልተነገረን፣ ጨቋኙ የተፈጠረበትን እያከናወነ እንዳልሆነ ሁሉ ደርሶ እንደአዲስ መደነቅ! ጭቆናውና መገለጫው የሆኑት ድርጊቶች መዘገባቸው፣ መጋለጣቸውን መቃወሜ አይደለም። ዜናዎቹን የምናስተናግድበት መንገድ ግን መጨረሻ የሌለው አጃጃይ መገረምና መደነቅ መሆን የለበትም። በጭቆና ዜና ከመገረምና ከመደነቅ ወጥትን ስለጭቆናውንና ስለጨቋኙ ወደ ማሰላሰል፣ ወደማሰብ…. “እንዲህማ አያረጉም” ብሎ ራስን ለሌላ ዙር መደነቅ ከማዘጋጀት ይልቅ አምባገነኖች ማንኛውንም አይነት የግፍ ተግባር ከመፈጸም ወደኋላ እንደማይሉ ራስን ማሰመን ቢያንስ ጊዜ ይቆጥባል። ሰዎቹ ሥርዓታቸውን ለማሰንበት በሚያደርጉት ነገር የሕግም፣ የባህልም፣የፖለቲካም ሆነ የሞራል ልጓም የላቸውም፤ ልምዳችን ይህን ያረጋግጣል። ቀጣዩ የጭቆና ዜና ስንቶችን ያስደንቅ ይሆን?

ታምራት [12] የተባለ ሌላ የፌስቡክ ተጠቃሚም ጉዳዩን ‹‹ሰምና ወርቅ›› ነው በማለት በጻፈው ጽሑፍ ላይ መንግሥት ሰልፈኞቹን ያሰረው ‹‹አንድም የግራዚያኒ ኀውልትን በመቃወማቸው ነው፣ አሊያም የተቃውሞ ሰልፍ በመውጣታቸው ነው የሚለውን›› ካብራራ በኋላ ወርቁ ይሄ ነው [13] [en] ይላል፡-

… we have no historical or whatever apparent reason to associate the government with Italian invaders nor have conclusive evidence to claim that the government is benefited from silencing the protestors in favor of erection of the statue. Had the case was of Nazi, the world would have raised its voice heard against the erection of brutal Nazi. For Ethiopians Graziani is no less atrocious than Nazi is; and protesting in the most non-violent way is lawful. It’s well recognized for government too.

For me the government interest is not the protest against erection of the statue. They are more curious about the gathering, setting agenda and bring it to the public life […] Few days before we learned the banning of already reserved hotel hall when the managers understood its gathering of people protesting the existing political system, even though they knew the gathering was not to protest any of government agenda.

… መንግሥት ከኢጣልያ ወራሪዎች የሚገናኘው ታሪካዊም ሆነ የተለየ ግልጽ ግንኙነት ስለሌለ እና መንግሥት የኀውልቱን መቆም የሚቃወሙ ሰልፈኞቹን ዝም በማሰኘት የሚያገኘው ጥቅም መኖሩን የሚያስረዳ መረጃ የለም፡፡ ጉዳዩ ስለናዚ ቢሆን ኖሮ፣ የነፍሰበላው ናዚ መታሰቢያን በመቃወም ዓለም አብሮን ድምፃችንን ያስተጋባ ነበር፡፡ ለኢትዮጵያውያን ግራዚያኒ ከናዚዎች ያነሰ በደለኛ አይደለም፤ እናም፣ ይህንን አመጽ በሌለበት መንገድ መቃወም ሕጋዊ ነው፡፡ መንግሥትም ይህን ያውቃል፡፡

ለኔ፣ የመንግስት ጉዳይ ከኀውልቱ መቆም ጋር አይደለም፡፡ እነርሱን ያስጨነቃቸው መሰባሰቡ፣ አጀንዳው ለውይይት መብቃቱ እና የሕዝብ ጉዳይ መሆኑ ነው፡፡ […] ከጥቂት ቀናት በፊት በሆቴል ውስጥ ቀድሞ የተዘጋጀ የእራት ፕሮግራም ሲሰርዙ የሆቴሉ ኃላፊዎች መሰባሰብ በራሱ የፖለቲካውን ሥርዓት መቃወም እንደሆነ ስለገባቸው ነው፤ ምንም እንኳን ስብሰባው የመንግሥትን አጀንዳ የመቃወም እንዳልሆነ ቢያውቁም ቅሉ፡፡

ውይይቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን ለጊዜው ማስቆም ቢቻልም፣ ተቃውሞውን ግን እንደሚቀጥሉበት ብዙዎች አሁንም እየተናገሩ ነው፡፡