የ‹‹ሕገ-መንግሥቱ ይከበር›› እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ

በአዲስ አበባ የሚገኙ ወጣት ጦማሪ እና አራማጆች ከኢትዮጵያ የድርዜጎች (netizens) ጋር በማበር መንግሥታቸው የኢትዮጵያን ሕገ-መንግሥት እንዲያከብር ጠየቁ፡፡ ‹‹ሕገ-መንግሥቱ ይከበር›› የተሰኘው እንቅስቃሴ በትዊተር እና በፌስቡክ ላይ የተካሄደው የኢትዮጵያ መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን የጣሰባቸውን መረጃዎች በመለዋወጥ ነበር፡፡

‹‹ሕገ-መንግሥቱ ይከበር›› የፌስቡክ ገጽ ከተጠቀመባቸው ባነሮች አንዱ፡፡

ቡድኑ ለእንቅስቃሴው የፌስቡክ እና የኩነት ገጽ የፈጠረ ሲሆን ዕድገታቸውም ፈጣን ነበር፡፡ በዘመቻው የኢትዮጵያ መንግሥት ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን መቃወም አስፈሪ ነገር እንዳያደርገው ተጠይቋል፡፡ የ‹ዓለም ድምፆች› አማርኛ ቋንቋ አርታኤው በፍቃዱ በአማርኛ ጽሑፍ ያጋራውን የሚከተለው ጽሑፍ በርካታ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች አስተጋብተውታል፤

ፍርሐት ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም፤ የአንድን አገር የሰብኣዊ መብት ጥሰት ባሕል እና ታሪክ መንሰራፋት የሚያረጋግጥ እውነታ እንጂ! ፍርሐት አርቆ አሳቢነትን ይገላል፣ ብሎም የተሻለ ነገን የመፈለግ እና የማለም አቅም ያሳጣል። ፍርሐት እንቅፋት ነው፣ ፍርሐት መንፈስን ሰብሮ ሐሳብና ምናብ ያሳጣል፤ ነጻነት ግን ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው፣ ነጻነት ያበረታታል፣ ነጻነት ሰላማዊ ነው፣ ነጻነት ይታገሳል፣ ነጻነት ፍቅር ያቃል፣ ነጻነት ከሁሉም ይልቃል፣ ነጻነት ማለቂያ የለውም/ዘላቂ ነው፡፡ ራዕይ የሌለው ሕዝብ ይባክናል ይባላል፡፡ ኢሕአዴግ ሕዝቡን በፍርሐት ግድግዳ በማጠርና ሐሳብን በነጻ የመግለጽ ተፈጥሯዊ መብታችንን በመገደብ ሕዝባችንን እያባከነው ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱን በማክበር እና ኢሕአዴግም እንዲያከብረው በመጠየቅ ኢትዮጵያን እናድን፡፡ ሕገ-መንግሥቱ ይከበር!

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በአርብ ዕለቱ ፀሎታቸው ማጠናቀቂያ ላይ ሰላማዊ አመጽ የሀይማኖ፣ እምነት እና አመለካከት ነጻነት የሚደነግገው የሕገ-መንግሥቱ  አንቀጽ 27 ይከበር ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኅዳር 28/2005 በታላቁ አኑዋር መስኪድ ባካሄዱት አመጽ መንግሥት በሃይማኖታቸው ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ ጠይቀዋል፡፡ 27 ቁጥር የሚወክለው የሕገመንግሥቱ ሃይማኖታዊ ነጻነት አንቀጽን ነው፡፡ ፎቶው የተገኘው ከድምፃችን ይሰማ የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡

በትዊተር ላይ የ#RespectTheConstitution ሀሽታግ ብዙ ውይይት አጧጡፎ ነበር፡፡ የሲፒጄው የአፍሪካ ሚዲያ ፕሮግራም እንዳስተዋለው:-

@africamedia_CPJ: #የኢትዮጵያ የትዊተር ምኅር በ#RespectTheConstitutionechoing እና #protests በሃይማኖት እና ሌሎች ነጻነቶች  ጉዳይ ተጠምዷል፡፡ #socialmedia #FF@BillGates

ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀጾች ሊባል በሚችል ሁኔታ ወደትዊትነት እየተለወጡ ነው ሲል ክሩቤል ተሾመ ትዊት አድርጓል:-

በዛሬይቱ #ኢትዮጵየ ሐሳብን ፣ የመናገር እና የማሰራጨት ነጻነቶች በጣም የተጋነኑ እና በገንዘብ የማይገኙ ሸቀጦች ሆነዋል፡፡ #RespectTheConstitution!

ዳንኤል በየነም በበኩሉ፡-

@DanielBeyene: ሚዲያው በነጻ ሪፖርት የማድረግ እና ማንኛውንም የመንግሥት ተግባር የመተቸት መብት አለው፡፡ #FreeMedia #RespectTheConstitution #Ethiopia

ኩዌንሽንሚዲያም እንዲሁ፡-

@KweschnMedia: አንቀጽ 29፡5 በመንግሥት ገንዘብ የሚተዳደር የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አስተያየቶችን ማስተናገድ በሚችልበት መንገድ ይዋቀራል” #RespectTheConstitution

ማሕሌት ሰለሞን ደግሞ:-

@MahletSolomon: ኅዳር 29፣ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት 18 ዓመት ይሞላዋል፡፡ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መብታቸውን በመጠቀማቸው እስር ቤት ገብተዋል፡፡ #RespectTheConstitution

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኅዳር 28/2005 በታላቁ አኑዋር መስኪድ ባካሄዱት አመጽ መንግሥት በሃይማኖታቸው ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ ጠይቀዋል፡፡ 27 ቁጥር የሚወክለው የሕገመንግሥቱ ሃይማኖታዊ ነጻነት አንቀጽን ነው፡፡ ፎቶው የተገኘው ከድምፃችን ይሰማ የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.