በኪዌት ህቡዕ የትዊተር ገጽ ታላቅ ተቃውሞን እየመራ ነው

ትልቁን አመጽ ከተመለከቱ በኋላ ህቡዓኑ “የክብር ሰልፍ” አዘጋጆች ሌላ የተቃውሞ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የኪዌት መሪዎች የመምረጥ መብት ህግን በመከለሳቸው በሚሽረፍ እና ሳባህ አል ሳሌም አከባቢዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡ ይህ ህግ  አንድ ዜጋ ለአራት እጩ ተወዳዳሪዎች የሚሰጠውን ድምጽ ወደ አንድ ያወርደዋል፡፡ተቃዋሚዎቹ የአሚሩን ውሳኔ ሕገ መንግስታዊ ሆኖ አላገኙትም አዲሱ ህግ የተዘጋጀው በዚህ ዓመት ቀድሞ አብዛኛውን የፓርላማ ወንበር ያሸነፈውን ተቃዋሚ ፓርቲ  በመጪው ታህሳስ በሚካሂደው ምርጫ ላይ  ለማዳከም ነው ብለው ያምናሉ፡፡ እንደ መጀመሪያው ሰልፍ ዕለተ ሰንበት [ህዳር 4 2012] የአስለቃሽ ጢስ እና ቦንቦችን ሰለባ የሆኑ ሲሆን በርካቶችም ከታሰሩ በኋላም መለቀቃቸው ታውቋል፡፡

ተቃውሞውን የሚመራው ማነው ?

ባለፉት ጥቂት አመታት አመጸኞቹ በተቃዋሚ የፓርላማ አባላት በመመራታቸው ትችት ደርሶባቸዋል፤ በኋላ ወጣቶቹ የተቃውሞው መሪዎች ለመሆን ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህ ለውጥ “የክብር ሰልፎች” ላይ የተሳተፉ ሰዎች ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል፡፡ሌላው አስገራሚ የሚያደርገው ነገር ደግሞ የሁለቱም ሰልፎች ቀንና መነሻ ቦታ የተወሰነው በህቡዕ የትዊተር ገጽ መሆኑ ነው፡፡

ጥቅምት 24  @KarametWatan (በአረብኛ የሀገር ክብር) የተሰኘ  የትዊተር ገጽ ትዊተር ማንነታቸውን ለኪዌት መንግስት አሳልፎ እንዳይገልጥ የሚጠይቅ መልዕክት  በትዊተር አስተላለፈ፡፡

እኛ የኪዌት ህዝቦች የገጻችንን @karametwatan ግለኝነት እና ዝርዝር መረጃዎች በዚህ ገጽ ተጠቅሞ የሚለጥፍን ግለሰብ የበየነመረብ አድራሻ (IP addresses) ከሚፈልጉ ከሁሉም / ከማንኛውም  ባለስልጣናት እንዲትጠብቁልን እንጠይቃለን፡፡ በኪዌት ታሪክ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ቁጥር ያለው ዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብቶችን እና ሙስናን መዋጋት የጠየቀውን “ክብር ለሀገራችን” የተሰኘውን ሰልፍ የማዘጋጀቱን ሃላፊነት እንወስዳለን፡፡ ይህ ግልብጥ ብሎ የወጣው ከ150, 000 በላይ ቁጥር ያለው ህዝብ(ከጠቅላላው የከዌት ዜጋ 11.5% አከባቢ) መንግሰትን ያስበረገገ ነበር፡፡በምላሹም መንግስት በአውሬነት፣ ያለምክንያት፣ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ይህን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያጠቁ ሀይሎቹን አዟል፡፡ከመቶ በላይ ሰዎች ሲጎዱ ከሀምሳ በላይ የሚሆኑት ደግም በህገወጥ መልኩ ወህኒ ወርደዋል፡፡በአደጋ ውስጥ እንዳለን ይሰማናል፤ ለግለኝነታችን የምታደርጉት ጥበቃ ወሳኝ ነው፡፡

እነዚህ ትልልቅ ሰልፎችን የሚያስተባብረው የትዊተር ገጽ መሆኑ ያሰገረመው ሓማድ አል ሳባህ ይህንን አስተያየቱን አስፍሯል፡፡

@hmalsabah:  በሺዎች የሚቆጠሩ በኪዌት ያሉ ሰዎች የአንድን ህቡዕ የትዊተር ገጽ ትዕዛዝ ማክበራቸውን ማመን የከበደኝ እኔ ብቻ ነኝ?

ባህሬናውያን ኪዌቶችን ደግፈዋልን?

የጎጠኞቹን ሐተታ ግምታ ውስጥ በማሰገባትና የኪዌት ተቃዋሚ መሪዎች የጥር 14 አብዮት የባህሬንን ስርዓት በመደገፋቸው፤ የኪዌት ሻይቶች ከተቃዋሚዎች ጎን ሆነው መሰለፍ አይፈልጉም፡፡ በውጤቱም የተፅእኖ ወስጥ የወደቀው ባህሬናዊ ሻይት  ሰልፉን መደገፍ እንዳለባቸውና መደገፍ እንደሌለባቸው ውይይት ጀምሯል፡፡ ለዚህ ርዕስ ምላሽ ባህሬናዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ማርያም አልካዋጃ እንዲህ ጽፏል፡፡

@MARYAMALKHAWAJA: አዎ! ጥያቄዎቹ ሐቀኛ ከሆኑ እነርሱ የኔን ጉዳይ ቢደግፉም ባይደግፉም፤ የኔ ድጋፍ አይለያቸውም፡፡

@MARYAMALKHAWAJA: የባህሬንን ተቃውሞ የሚደግፉ  በርካቶች በኪዌት አመጽም ሱታፌ አላቸው፤ ነጥቡ ግን ያ አይደለም፡፡

አህመድ አል ሓዳድ የተባለ ሌላ የባህሬን አራማጅ ከአውሮጳ-ባህሬን  የሰብዓዊ መብት ድርጅት ይህን ጽፏል፡፡ [ar]፤

اذ كنت تعتقد بأن لك الحق بتصوير الحراك الكويتي على أنه أخونجي وطائفي اذا يحق لغيرك تصوير حراكك بالشيعي الطائفي

@DiabloHaddad: የኪዌትን ትግል እንደ ሙስሊም ወንድማማች እና ጎጠኛ አድርገን የመቁጠር መብት እንዳለህ ካሰብክ ሌሎች ደግሞ ያንተን (የባህሬንን ትግል) እንደ ሻይቶች እና ጎጠኛ ትግል አድረገው የመውሰድ መብት አላቸው፡፡

ሌሎች ተቃዉሞዎች

 

ከጎጣዊ ግጭት ውጭ ሌሎች ደግሞ ለዚህ አመጽ ያላቸውን ተቃውሞ አሳይተዋል፡፡ ከተቃውሞ ይልቅ መጪው ፓርላማ  ችግሩን ይፈታዋል ብሎ የሚያስበው ሓማድ አል ሳባህ እንዲህ ተወተ፡፡

@hmalsabah: የማምነውን እንደገና ሳስተውለው የአማጺያኑ ጥያቄ ፍትሐዊ ነው፤ ነገር ግን የሚከተሉትን መንገድ አልደግፈውም፤ በሰላማዊ መንገድ በቀላሉ ሊፈታ ይችላል፡፡

ፋዋዝ አል ማትሩድ  መለሰለት፡፡

@FawazAM: ህዝቦች አብዛኛውን ጊዜ በንቅናቄ ህጎች እና ፖለቲካዊ መብቶች ላይ ይሳሳታሉ፡፡ ብዙ ሰዎች በህብረት ህግን ስለጣሱ እነርሱን ትክክል አያደርጋቸውም፡፡

ጦማሪው “His & Hers” ተወተ፡፡

@HisHersQ8: ህገወጥ ተቃውሞ ጋር ስንመጣ አሚሩ ነጥብ አላቸው፤  በዓለም ዙርያ ያሉ ዴሞክራሲዎች ሁሉ የትኛውንም ህገ ወጥ ተቃውሞችን ያቆማሉ፡፡

በግለሰብ መብት የሚያምነው ካህሌድ አጃሴር ተወተ፡፡

@k_jaser: አስለቃሽ ጭስና የድምጽ ቦንቦች ክምችት እዚህ ኪዌት ገድብ የላቸውም፤ ከዚህ ህገ ወጥነት ጋር መደራደሪያ ሌላ መንገድ የለም፡፡

 

የአመጹ ፎቶዎች እና ቪድዮዎች

በአስለቃሽ ጭስ ሲገረፉ(@Fajoor በትዊተር ላይ ከለጠፈው)

ወታደራዊ መኪኖች ወደ አማጽያኑ ስፍራ ሲያመሩ የሚያሳይ ምስል(በጦማሪው alziadiq8 የተለጠፈ )

ከተቃዋሚዎች አንዷ ከነ መፍክሯ (በጦማሪው alziadiq8 የተለጠፈ)

ይህ ፎቶ በስፋት እና በብዛት የተሰራጨ ሲሆን አንድ አማጺ በአስለቃሽ ጢስ ጉዳት የደረሰበት የደህንነት አባል ሲረዳ ያሳያል፡፡

ሚሽራፍ አከባቢ የነበረውን አመጽ የሚያሳይ ቪዲዮ (በsaad971 የተለጠፈ)

http://www.youtube.com/watch?v=3pln0LiuZis

ቦንቦችን ጉዳቶችንና እና ተቃውሞውን የሚያሳይ ሌላ ቪድዮ(በ7eyad የተለጠፈ)

ሳባህ አል ሳሌም አከባቢ የነበረውን ተቃውሞ የሚያሳይ ቪድዮ

ጆርዳናዊያን በኪዌቶች እርምጃ ተወስዶባቸዋል ?

ከሳምንታት በፊት ሙታሂድ በሚል ስም የሚራ ህቡዕ የትዊተር ገጽ የኬዌት ተቃዋሚዎችን ለማፈን ጆርዳን ወታደሮቿን ልካለች ብሎ ተወተ፡፡ ታወቂውን እና አወዛጋቢ ሳሊፊ የፓርላማ አባል ዋሊድ አልታባቲበያ ዜናውን በተዊተር አሰራጨው፡፡ ትላንት ደግሞ የቀድሞው የፓርላማ አባል እና የተቃዋሚው ፊትአውራሪ ማስላም አል ባራክ አወዛገቢ ንግግር አደረገ፡፡ ባለፈው ሳምንት የአሚሩን ክብር በማሳነሱ የታሳረ ቢሆን እርሱን የሚደግፍ ታላቅ ተቃውሞ በመቀስቀሱ በሁለት ቀናት ውስጥ ሊለቀቅ ችሏል፡፡

 

በዚህ ቪድዮ አልባራክ “የደህነት ሰዎች ወንድሞቻችን ናቸው፤ ቢመቷችኹ አጸፋውን አትመልሱላቸው፤ ግን የጆርዳን እና ፍልስጤም የደህንነት ሰዎች ቢሆኑ ግን ተነሱባቸው” ብሏል፡፡

በምላሹ የጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክሱን ክዶ መግለጫውን አቅርቧል፡፡

የአሚሩ ምላሽ

በትልልቆቹ አመጾች ምክንያት አሚሩ ውሳኔውን ቀልበሶ ተቃውሞውን ያረጋጋዋል የሚል ግምት በህዝቡ ዘንድ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰኞ ዕለት ባደረገው ንግግር ውሳኔውን ወደኋላ እንደማይመልስና ለመጪው ፓርላማም የመምረጥ ህጉን እንዲከለስ እንደተወ ተናገረ፡፡በተጨማሪም የባህረ ሰላጤው ሀገራት የሀገሪቱን ደህንነት እንዲጠብቅ እንደሚደገፉትም አከለበት፡፡ የንግግሩን ቪድዮ እዚህ ያገኙታል፡፡(የለጠፈው ጦማሪው AlZiadiq8 ነው )

1 አስተያየት

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.