የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የሱዳን አቻውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ገጥሞ 2 ለ ዜሮ አሸነፈ፤ ከ31 ዓመታት በኋላም ወደ የአፍሪካን ዋንጫ ውድድር ተቀላቀለ፡፡ ይህ ድል ኢትዮጵያውያንን እጅግ አስፈንድቋል፡፡በተለይ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጎዳናዎች በደስታ በተሞሉ ሰዎች ተጨናንቋል፡፡በኢትዮጵያ ማኀበራዊ ሚዲያም ሰፊ ሽፋንን አግኝቷል፡፡
በሰው ለሰው ድራማ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው ተዋናይት ማህደር አሰፋ ድሉ በአትዮጵያዊነቷ እንድትኮራ አስገድዷታል፡፡
እንዴት ደስ ይላል ከ31 አመታት ጉዞ በሁዋላ በኛ ትዉልድ አየነው፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆን ስሜቱ እጅግ ከባድ ነው በዚህም እኮራለሁ:: የምር ደስ ብሎኛል፤ ወደፊትም ለቡድናችን ታላቅ ስኬትን እመኛለው፡፡
ናትናኤል ፈለቀ(@universaliberty) በበኩሉ በተጋጣሚዉ የሱዳን ቡድን ላይ በማፌዝ በትዊተር ደስታውን ገልጿል፡፡የሱዳናዊውን ድምጻዊ ሰይድ ከሊፋ ቆየት ያለ የአማርኛ ዘፈን እንደምርኩዝ ተጠቅሟል፡፡
ENDEMIN NACHIHU? DEHNA NACHIHU? keSUDAN METAN… I went crazy, the whole nation went crazy.#Ethiopia
እንደምን ናችኹ ደህና ናችኹ ከሱዳን መጣን . . . እኔ እብድ ሆኛለው፤ መላዋ ሀገሬም ተከትላኝ አብዳለች #ኢትዮጵያ
የስፖርት ጋዜጠኛው የፍስሐ ተገኝ(@fisseha505 ) ትዊትም ብዙዎች ወደውለታል፡፡
GREAT! Ethiopian footballers of my generation have done something spectacular! Ethiopia qualify to the African Cup of Nations after 31 years
ታላቅ! የኔ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ኳስ ተጫዋቾች እጅግ የሚደነቅ ነገርን አድርገዋል፤ ከሰላሳ አንድ አመታት በኋላ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች፡፡
በዚሁ በዓለም ድምጾች ኢትዮጵውያን መንግስት ድሉን ሟቹን ጨቋኝ መሪ ለማወደስ ይጠቀምበታል የሚል ስጋት እንደነበራቸው መግለጻችን ይታወሳል፡፡የፈሩት አልቀረም በድሉ ላይ ውሃ ለመቸለስ መንግስት እና ሚዲያዎቹ ያደረጉትን ሙከራ በስደት ሚገኙት ጋዜጠኞቹ አቤ ቶክቻው፣ መስፍን ነጋሽ እና ዘሪሁን ተስፋዬ ቅሬታቸውን እንዲህ ገልጸዋል፡፡
የወያኔ ካድሬዎችን ያህል በሕዝብ ደስታ የሚበሳጭ አንድ ፈልጎ ማግኘት ይቸግራል። ምነው ሸዋ፣ ዛሬኳ ቢተውን ምነው?! አሁን ማን ይሙት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኳሱ ምን አበርክተው ነው ይሄ ሁሉ የታሪክ ሽሚያ? ማስታወሻነቱማ የሚገባው ብርድና ሃሩር ሳይል ለኣመታት መከራውን የበላው ሕዝብ ነው።
Shame on you ETV Sport journalists for politicizing this national victory. Can't you give us few minutes and hours? You have the whole of your life to your political garbage. Ask the federation and your bosses to build a better studio and camera at this occasion than your politics. Why don't you go out and ask the people what do they feel about the game?
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስፖርት ይህን ብሔራዊ ድል ለፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ በመሞከራችኹ አፍሬያለው፡፡ ለዚህ ፓለቲካዊ ቆሻሻችኹ ሙሉ ህይወታችሁን መገበር እየቻላችሁ የተወሰኑ ሰዓታት እና ደቂቃዎች እንኳን አትሰጡንም? ይህን ክስተት ለፖለቲካ ከምትጠቀሙበት ይልቅ ፌደሬሽኑንና አለቆቻችኹን የተሻለ ስቱዲዮ እና ካሜራ እንዲያዘጋጁ ጠይቋቸው፡፡ ለምን ወደ ህዝቡ ሄዳችኹ ስለጨዋታው ምን እንደተሰማቸው አትጠይቋቸውም?
በደንብ እደግመዋለሁ….. በ21 አመት ቆይታቸው አንድ ስታድየም እንኳ ላልገነቡ ሰውዬ ይህንን ውጤት መታሰቢያ ማድረግ ምን ይሉታል… ወይስ “ይብላኝ ለርስዎ እኛስ አሸነፍን!” ማለት ይሆን!? ? ? ? ? ? በናታችሁ ጥያቄ ምልክት ጨምሩልኝ!
አጥናፉ ብርሃኔ ለዚህ የመንግስት ወስላታነት መፍትሔ አለኝ ባይ ነው ፡፡‹‹መታሰቢያነቱ ለቀድሞው ጠቅላያችን›› ምናምን ምናምን ምናምን….. የሚል ዲስኩር ከሚያሰራጩ ሰርጎ ገቦች እንደጠነቀቁ ወዳጆቹን መክሮ ለዚህ ጠቃሚ መፍትሄዎች ናቸው ያላቸውን ይዘረዝራል፡፡
- ከድል በኋላ ኢቴቪንና ኤፌሞችን አለመከታተል
- ትንቢት ተናጋሪው ሪፖርተር ‹‹ከድል በኋላ›› በሚል ርዕስ ውስጥ ‹‹አንዳንድ የአዲስ አባባ ነዋሪዎች የተገኘው ድል የሚያመላክተው የጠቅላያችን ራዕይ መሳካት መጀመሩን ነው፡፡›› የሚል ዘገባ ከጨዋታው በፊት ሰለሰራ እንዳላዩ ማለፍ፡፡
- የመጨረሻውና ዋነኛው መፍትሄ ‹‹ለካስ እስከዛሬ ጠቅላያችን ነበር የቋጠሩት›› ብሎ ማሰብ፡፡
ኢትዮጵያውያንም የ አጥናፉን ምክር የሰሙ ይመስላሉ፡፡ ከመንግስት ተጽእኖ ነጻ በሆኑት ማኀበራዊ ሚዲያዎች ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡
ደጀኔ ቀልቤሳ ይህንን ክስተት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ትንሳኤ ሲል ይጠራዋል፡፡
This is exactly the real renaissance for our football. both women and men national teams are qualified for African cup on nation. The youth team won strong Tunisian team by wide margin (3:0)….I am extremely happy, we are extremely happy and all Ethiopians are extremely happy……Addis is on fire……Thanks Team Ethiopia
ይህ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እውነተኛ ትንሳኤ ነው፤ ወንዶቹም ሴቶቹም ብሔራዊ ቡድናችን ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል፡፡የወጣቶች ቡድን ደግሞ የቱኒዚያ አቻውን በሰፊ ግብ ልዩነት አሸንፏል፡፡(3:0) ወደር የሌለው ደስታ ይሰማኛል እኛ እጅግ ደስተኞች ሆነናል፤ ኢትዮጵያውያንም እንዲሁ … አዲስ እየተንበለበለች ነው. . . የኢትዮጵያ ቡድን እናመሰግናለን፡፡
ብስራት ተሾመ ግን ከደስታው ብዛት እንደ ደጀኔ ቃላትን አሳክቶ መጻፍ አልቻለም፤ የማይሞከረውን ለመሞከር ጣረ እንጂ!
How do I describe this? I just have to keep silent and shout. Oooppps, I cant do that leka?!?!?
ይህን እንዴት እገልጸዋለው? በአንድ ጊዜ ዝም ማለት እና መጮኽ አለብኝ፡፡ እህሀህምምም ያን ማድረግ አልችልም ለካ?
1 አስተያየት
ብሄራዊ ቡድናችን ስላሸነፈልን ኢትጵያውያን እንዃን ደስ ያለን!!!!!!!!!
ኢትዮጵያ ትነሳለች ይህ የስኬታችን አንዱ ክፍል ነው
እማማ ኢትዮጵያ
ደስ ይበልሽ ዛሬ ሀዘንሽን እርሺ
ቃልኪዳን በመግባት ወጥተው ልጆችሽ
በቁጭት ተነስተው እስፖርተኞችሽ
ድል አስመዘገቡ በአገር በሜዳሽ
እሩጫው አይቆምም በመላው ህዝብሽ
ስምሽን ሊቀይር ከፍ ሊያደርግሽ
በሁሉም ስራ ዘርፍ ቆርጧል ወገንሽ
እማማ ኢትዮጵያ እንዃን ደስ ያለሽ