የጦማር የተግባር ቀን 2012፡ ‘የእኛ ኃይል’ በሚል መሪ ርዕስ ይከበራል

እንግዲህ ከ95 ሀገሮች የተውጣጡ ጦማሪያን በነዛ ብቁ እና ፈጣን እጆቻቸው ሊከትቡ ተዘጋጅተዋል፡፡ ለአንድ ቀን ሁሉም ስለ አንድ ተመሳሳይ ጉናይ ላይ በመፃፍና የሚያምር የታሪክ ፍሰት በመስራት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ተካታዮቻቸው ይጦምራሉ፡፡ ጥቅምት 15፣ 2012 – የጦማር የተግባር ቀን !

ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የጦማር የተግባር ቀን በጠቃሚ ጉዳዮች ላይ ንቃትን ለመፍጠር፤ የጦማር ጥቃት ለመፈሰፀም ያስተባብራል፡፡ ባለፉት ዓመታትም ክስተቱ በግሎባል ቮይስ ሽፋን አግኝቶ ነበር፡፡ ያለፉት ዓመታት መሪ ጉዳዮችም አካባቢድህነትየአየር ንብረት ለውጥውሃ እና ምግብ ነበሩ፡፡ የዘንድሮው ዓመት መሪ ርዕሰ ጉዳይም ‘የእኛ ኃይል’ ይሰኛል፡፡

ፎቶ በማሪያ ግራቦውስኪ

ስለ ‘የእኛ ኃይል’ እንዴት መፃፍ ይችላሉ?

በርግጥም አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት በጋራ መስራትን አስበዉት ያውቃሉ? ያገባኛል ስለሚሉት ጉዳይ መሟገት ወይም ስለ ወሳኝ እና አነሳሽ ቡድን – በአጭሩ፡ ለውጥ ለማምጣት ሰዎች ይሰባሰባሉ፡፡ እርስዎም በፈለጉት ቋንቋ፣ ከፈለጉት ሀገር ሆነው መፃፍ ይችላሉ፡፡

በጥቅምት 15/ 2012 ‘የእኛ ኃይል’ በሚል መሪ ርዕስ የሚካሄደውን የጦማር የተግባር ቀን 2012 እዚህ ላይ በመመዝገብ ይቀላቀሉ፤ ለሚሊዮኖችም ተደራሽ ይሁኑ፡፡ አዳዲስ ለውጦችንም ትዊተር ላይ #BAD12 ብለው ይከታተሉ፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.